2013-08-07 15:46:28

ናይጀሪያ፦ ጸረ ሰብአዊ ጥቃት


RealAudioMP3 ባለፉት ቀናት በናይጀሪያ ገዛ እራሱ ቦኮ ሃራም በማለት የሰየመው በአገሪቱ ሰሜናዊ ክልል በስፋት የሚንቀሳቀሰው አክራሪው እስላማዊ ታጣቂ ኅይልና በአገሪቱ መደበኛ ሠራዊት መካከል በተካሄደው ውጊያ 35 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ፣ ናይጀሪያ ከካሜሩን ጋር በሚያዋስነው ክልል በተካሄደው ውጊያ ጭምር አንድ የጸጥታ ኃይል አባልና 17 የአክራሪው እስላማዊ ኃይል አባላት ሕይወታቸው ሲያጡ፣ በማላም ፋቶር ክልል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ 19 ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸው ከአገሪቱ የሚሰራጩት ዜናዎች ያመለክታሉ።
ዓለም አቀፍ የጸረ ሰብአዊ ወንጀል መቅጫ ፍርድ ቤት አቃቤ ዳኛ ፋቱ በንሱዋድ በናይጀሪያ የሚንቀሳቀሰው ቦኮ ሃራም የተሰየመው አክራሪው እስላማዊ ኃይል በተመለከተ ባወጡት ይፋዊ ሰነድ፣ አክራሪው ታጣቂ ኃይል በጸረ ሰብአዊ ወንጀል የመቅጫ ህግ መሠረት የክስ መዝገብ ለመክፈት እቅድ ያላቸው እንደሚመስል ካሰራጩት ሰነድ ለመረዳት ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2009 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም. ባለው የዓመታት ገደብ ውስጥ አክራሪው እሳላምዊ ኃይል 1,200 ንጹሓን ዜጎች ለሞት መዳረጋቸውንም ሰነዱ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.