2013-08-05 16:21:32

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞቻና እኅቶች! ባለፈው እሁድ በሪዮ ዲ ጃነሮ ነበርኩኝ፣ የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መዝግያ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳረግሁ፣ እንደሚመስለኝ ሁላችን ጌታችንን በዚሁ ፍጻሜ ስለሰጠን ታላቅ ጸጋ ልናመሰግነው ይገባናል፣ ይህ ጸጋ ለብራዚል እና ለደቡብ አሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የተሰጠ ጸጋ ነው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ይዘው መንፈሳዊ ንግደት ለሚያደርጉ ወጣቶች አዲስ እርምጃ ነበር፣ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀኖች ለጊዜው ብቻ ብቅ ብለው የሚጠፉ ስሜቶችና ለበዓሉ ብቻ ተብሎ የሚደረጉ ፍጻሜዎች እንዳልሆኑ መረዳት ያስፈልጋል፣ እነኚህ ቀኖች የረዥም መንፈሳዊ ጉዞ የተደላያዩ ደረጃዎች ናቸው፣ የጀመሩትም በስመ ጥር ር.ሊ.ጳ የሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1985 ዓም ነበር፣ ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለወጣቶቹ የጌታ መስቀልን አስረከባቸው፣ ሂዱ እኔም ከእናንተ ጋር እጓዛለሁም አላቸው፣ ይህ የወጣቶች መንፈሳዊ ንግደት ከር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛም ቀጥለዋል፣ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው እነሆ እኔም ደርሼበት በብራዚል አስደናቂ መንፈሳዊ ንግደት አደረግሁ፣ ወጣቶቹ ር.ሊ.ጳጳሳትን አይደለም የሚከተሉት፤ መስቀሉን በመሸከም ኢየሱስ ክርስቶስን ነው የሚከተሉት፣ ር.ሊ.ጳ ይመራቸዋል በዚሁ የእምነትና የተስፋ ጉዞም ይሸኛቸዋል፣ በዘንድሮው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለተሳተፉት ሁሉ በብዙ መስዋዕትነትም ሳይቀር ላደረጉት ተሳትሮ አመስግናቸዋለሁ፣ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ስላደረግሁት ግኑኝነትም እግዚአብሔርን አመስግናለሁ፣ የብራዚል መፈሳዊ እረኞችንና ሕዝበ እግዚአብሔርን እንዲሁም ከትለያዩ ባለሥልጣናትና በበጎ ፈቃድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ሰዎች ጋር በመገናኘቴም ጌታን አመስግናለሁ፣ ለዚሁ ታላቅ የእምነት በዓል ለሰሩትና ላበረከቱት ሁሉ እግዜብሔር ይባርካቸው፣ በተለይ ደግሞ ለብራዚላውያን ያለኝን ምስጋና ላስምርበት እወዳለሁ፣ ለሁሉም ብራዚላውያን ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ፣ ጅግና ሕዝብ ልበ ሙሉ የሆነ ሕዝብ ስለሆነ በሰላማታቸውና በብሩህ ፊታቸው እንዲሁም በታላቅ ደስታ ያደረጉልኝ ደማቅ አቀባበል አልረሳውም፣ ይህንን ለጋስ ሕዝብ እግዚአብሔር እንዲባርከው እለምናለሁ፣
በዚሁ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የተሳተፉ ወጣቶች ሁላቸው ይህንን ተመኵሮ በዕለታዊ የሕይወት ጉዞአቸው በተግባር እንዲተረጕሙት በየዕለቱ በሚያሳይዋቸው ጠባዮቻቸው እንዲኖሩት በሕይወታቸውም የጌታን ጥሪ ባማዳመጥ ትርጉም ያላቸው የሕይወት ምርጫዎች በማድረግ መልስ እንዲሰጡት ሁላችሁ ከእኔ ጋር አብራችሁ እንድትጸልዩ እሻለሁ፣ በዛሬው እሁድ ሥርዓተ አምልኮ “ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው” (መክ 1፤2) ነው የሚለው አሳሳቢ ቃል እናነባለን፣ በዘመናችን ወጣቶች ከበዋቸው ላሉ ትርጉም አልባና ዋጋ ቢስ ነገሮች ያተኵራሉ፣ በዚህም ሳቢያ ብዙ ይሰቃያሉ፣ በተቃራኒው መንገድ ሕያው ከሆነው ኢየሱስ ጋር መገናኘት ታላቅ ቤተ ሰብ በሆነችው ቤተክርስትያን ሲያገኙት ልብን በደስታ ይሞላል ምክንያቱም በማያልፈውና በማይበላሸው በእውነተኛ ሕይወት እና ጥልቅ በሆነ በጎ ነገር ስለሚሞላው ነው፣ ይህንን በሪዮ ዲ ጃነሮ በወጣቶቹ ገጽ አየነው፣ ይህ ተመኵሮ በዘመናችን ያለውን ከንቱነት አይቶ ለማቋቋም ማስቻል አለበት፣ ይህ ከንቱነት ትርፍ ለማግኘትና ሁሉን ለመጨበጥ በሚያስጓጓ ስሜት ወጣቶችን እያደናገረ ነው፣ የዛሬው ወንጌልም ደስታህን በአላፊ ነገሮች ላይ መመስረት እንዴት አደገኛ መሆኑን ያመለክተናል፣ ሃብታሙ ሰውየ ነፍሴ ሆይ ደስ ይበልሽ! እረፊ! ለሁል ጊዜ የሚሆን ሃብት አከማቻለሁን፣ አርፈሽ ተቀመጪ ብዪ ጠጪ ደስ ይበልሽ ይላታል፣ እግዚአብሔር ግን! አንተ ሞኝ ሆይ! ዛሬ ሌሊት ነፍስህን ይወስድዋታል! ይህ ሁሉ ያካማችሀው ለማን ይሆናል? ይለዋል (ሉቃ 12፤19-20)፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እውነተኛው ሃብት ከወንድማሞች ጋር የምትካፈለው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ይህ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ፍቅር እርስ በእርሳችን እንድንከፋፈለውና እርስ በእርሳችን እንድንረዳዳ ያደርገናል፣ ይህ እተግባር ላይ የሚያውል ሰው ሞትን አይፈራም በልቡም ሰላምን ያገኛል፣ ይህንን ስለት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም እናማጥነው፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድንቀበልና ከወንድማሞቻችን ጋር እንድንካፈለው እመቤታችን ድንግል ማርያም ታማጥንልን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.