2013-08-05 16:08:53

ብፁዕ ካርዲናትል ቱርክሶን በጃፓን


RealAudioMP3 የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶን በጃፓን እ.ኤ.አ. እስከ ነሐሴ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚቀጥል ሐዋርያዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. መጀመራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የዚህ ይፋዊ ጉብኝት መሠረታዊ ምክንያትም በሂሮሺማና ናጋሳኪ በ 1945 ዓ.ም. የተጣለው የአቶሚክ ቦምብ ፍንዳታ ያስከተለው እልቂት መታሰቢያ ምክንያት ሲሆን፣ የጃፓን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አሥር ቀናት ስለ ሰላም በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 6 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የአቶሚክ ቦምብ ሰለባ የሆኑትን ለማስታወስ ልዩ የጸሎት የባህል መርሃ ግብር መወጠኑም አስታውቀዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን ነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ሂሮሺማ በሚገኘው ካቴድራል ስለ ሰላም የረርገው መሥዋዕተ ቀዳሴ መምራታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ነሐሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገሪቱ ከሚገኙት ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ማለትም የቡድሃ የሺንቶይና የፕሮተስታንት ሃይማኖት የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያካሂዱና እ.ኤ.አ. ነሐሴ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ብፁዕነታቸው ወደ ናጋሳኪ በመሄድ እዛው በሚገኘው የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ማእከል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሰላም ውይይት መርሃ ግብር ተሳትፈው እዛው በሚገኘው በከተማይቱ የተዘክሮ አደባባይ በሚከናወነው የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ከተሳተፉ በኋላ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ናጋሳኪ ስለ ዓለም ሰላም የሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.