2013-08-05 16:07:14

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በክርስቲያኖችና ሙስሊሞች መካከል ለአንድ አዲስ ለጋራው ውይይት ኃይል ናቸው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ባለፈው ቅዳሜ የረማዳን ፍጻሜ ምክንያት ለመላ ሙስሊሞች ያስተላለፉት መልእክት በማስደገፍ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ የቲዮሎጊያ ሊቅ አድናነ ሞክራኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የዚህ ዓይነት የመልካም ምኞች መግለጫ መልእክት ከአንድ ታላቅ ር.ሊ.ጳ. መቀበል እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው። ቅዱስነታቸው ልክ እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮ በውይይት የሚያምኑ ከሙስሊሞች ጋር የጋራ ውይይት የሚያነቃቁ ናቸው፣ ስለዚህ የመረጡት የር.ሊ.ጳ. ስም ለገዛ እራሱ አለ ምክንያት አይደለም ካሉ በኋላ፣ ባስተላለፉት መልእት ሁሉም በተለይ ደግሞ ወጣት ትውልድ በሁሉ ሃይማኖቶች የመካባበር ባህል እንዲታነጹና ለሁሉ ለተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች የማክበር ግብረ ገብ እንዲኖራቸው የገለጡት ማሳሰቢያ ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ መሰረት ነው።
ወጣት ትውልድ የጋራ አካፋይ የሆነውን እሴት እንዲኖሩና እንዲያነቃቃ ሰላም መግባባትና ውይይት የሚኖር ማኅበርሰብ በማረጋገጡ ረገድ ያላቸው አቢይ ሚና በማብራራትም በእውነት ውይይት በሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ላንድ ሰላማዊ ኅብረተሰብ መሠረት መሆኑ የሚያብራራ መልእክት መሆኑ ገልጠው በግብጽ በቱኒዚያ በሶሪያ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ የሚያባብሰው የውይይት ባህል እጦት ነው። ስለዚህ በሁሉም መስክ ውይይት የሚያነቃቃና የተለይዩ ውጥረቶችና ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አልሞ የጋራ ውይይት ለሚያነቃቃ ሁሉ አቢይ ድጋፍ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.