2013-08-02 15:18:50

ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገው በቤተ ክርስቲያን የጸኑና የተመሠረቱ ሰዎች እንድንሆን ነው


RealAudioMP3 ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከትላትና በስትያ ዓመታዊ የኢየሱሳውያን ማኅበር መሥራች ቅድስ ኢግናዚዮኡስ ዘሎዮላ በዓል ምክንያት ሮማ በሚገኘው በቤተ ክርስቲያን ዘኢየሱስ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፦ “ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገው በቤተ ክርስቲያን ላይ የጸኑና የተመሠረቱ ሰዎች እንድንሆን ነው” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያተኮረ ሥልጣናዊ ስብከት እንዳሰሙ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አንቶነላ ፓለርሞ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የመጀመሪያ ኢየሱሳዊ ር.ሊ.ጳ. መሆናቸውም ሲታወቅ፣ ልእክት ጋዜጠኛ ፓለርሞ ለኢየሱሳውያን ማኅበር በኢጣሊያ ጠቅላይ አለቃ አባ ካርሎ ካሳሎነ ላቀረቡላቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኢየሱሳውያን ማኅበር ተማሪ ቀጥለውም በዚሁ ማኅበር ሰብአዊ መንፈሳዊ ብሎም ባህልዊ ሕንጸት ቀስመው የታነጹ፣ የኢየሱሳውያን ማኅበር ተመካሪ ካህን በዚህ ማህበር ወስጥ በተለያየ ኃላፊነት ያገለገሉ ናቸው፣ የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ አባ አዶልፎ ኒኮላስ ስለ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሲናገሩ፣ ኢየሱሳዊነት የሚሰማቸው እንደ ኢየሱሳዊ የሚያስቡ ናቸው” ብለዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ባስተላለፉት መልእክት ወደ ከተሞች ኅብረተሰብ ውጫዊ ክፍል ወይንም ወሰን ሂዱ ወንጌል አድርሱ በማለት ያሰሙት ቃል አባ ካሳሎነ አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ይኸንን ጥሪ ዘወትር በመደጋገም የሚያስተጋቡ ናቸው፣ ስለዚህ ውጫዊው ክፍል ሲባል የባህል የኤኮኖሚ ድኽነት ያጠቃቸው በተለያዩ ሰብአዊ ማኅበራዊና ኤክኖሚያዊ ችግር ምክንያት ተገደው በተነጠለ ሕይወት ወደ ሚኖሩት ሁሉ ወንጌል አድርሱ የሚሉ መሆናቸውና፣ እንዲህ ባለ መልእክት አዲሱ አስፍሆተ ወንጌል ሊከተለው ከሚገባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱን ያብራሩታል ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ብዙዉን ጊዜ በኃጢአት በሚፈጸውም ጸረ ሰብአዊ ተግባር ምክንያት ሁሉ ኃፍረት የማይሰማው፣ በእኔ ክፍት የማለቱ ጥልቅ ክርስቲያናዊ መንፈሳዊነት የዘነጋው ወቅታዊው ሰውና ባህል በተመለከተ የሚሰጡት አስተምህሮ ቅዱስነታቸው እንደ የቅዱስ ኢግናዚዮስ ዘሎዮላ ልጅ የቅዱስ ኢግናዚዮ በመንፈሳዊ ሱባኤ ጽሑፎቹ ዘንድ ያሉትን ቃላቶች ብዙውን ጊዜ ሲጠቀሙበት ይታይል፣ ስለዚህ በሰብአዊው ድካምነት ምክንያት በሚፈጸመው በደልና ኃጢአት አለ መጸጸት እጅግ የከፋና ለገዛ እራሱ ትልቅ ኃጢአት መሆኑ ያሚያሳስብ ቃል መሆኑ አብራርተው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሁለ መናዊ ኅዳሴ ቤተ ክርስቲያን እግብር ላይ ለማዋል የጀመሩት ሂደት በእውነቱ የሚደነቅ ነው። ሆኖም በመተባበር በማማከር በመወያየት የሚፈጽሙት ተግባር ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.