2013-08-01 08:54:32

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በማስደገፍ የቫቲካን ረዲዮ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮዋልዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. “ቤተ ክርስቲያን፦ ሃዋርያዊት ነች” በሚል ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስና በሐዋርያት የጸናች ስለ ሆነች ብቻ ሳይሆን ወደ ዓለም ሁሉ ወንጌል ለማበሰር የተላከች ስለ ሆነችም ነው። በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ በማተኮር ባቀረቡት 37ኛው ክፍለ አስተምህሮ፣ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ነች የሚለው በተአምኖተ እምነት ዘንድ አሜን በማለት የምንናዘው ቃል የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያነት በሦስት አመክንዮ ይገልጠዋል። ሐዋርያዊት፦ “የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ሞቱና ትንሣኤው መስካሪያን በሆኑት በሐዋርያት ላይ መሠረቷ የጸና በመሆኑ ነው” በሁለተኛ ደረጃ፦ “ቤተ ክርስትያን የሐዋርያት እቃቤ/አደራ/ሓላፍነት በተራዋ አቅባ የምታስተላልፍ በመሆንዋ ነው” ካሉ በኋላ በሦስተኛ ደረጃ፦ “ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ውህደትና ህብረት ካላቸው በካህናት እየተረዱ የሚያገለግሉት የሃዋርያት ተከታዮች/ተተኪዎች በሆኑት ማለትም በብፁዓን ጳጳሳት የምትመራ ስለ ሆነችም ነው” (ቍ. 857 ተመልክት) ብለዋል።
“ሐዋርያ” የሚል ቃል መሠረቱ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን፣ ትርጉሙም “ልኡክ” ማለት ነው። ኢየሱስ ወንጌል እንዲሰብኩ 12 ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ አብ እኔን እንደላከኝ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ…” (ዮሐ. 20.12) በማለት ይጠራቸዋል ይልካቸዋልም። ሐዋርያት በተራቸውም ተከታዮቻቸውን ይጠራሉ፣ ስለዚህ የሐዋርያት ተተኪነት ወይንም ተከታይነት እንደ ሰንሰለት የተያያዘ ቀለበት ሆኖ ካለ ማቋረጥ የሚቀጥል ነው ብፁዓን ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን የተሰጣቸው የሐዋርያት ተተኪዎች ናቸው። እነሱ በየቤተ ክርስቲያናቸው ጉልህ የአንድነት ምንጭና መሠረት ናቸው (ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ብርሃነ አሕዛብ ውሳኔ ቍ. 23” ያለውን ጠቅሰው፣ ብፁዓን አቡናት በተባባሪዎቻቸው ካህናትና ዲያቆናት የሚደገፉ ናቸው (ቍ. 938 ተመልከት) ሆኖም የሐዋርያት ተመክሮ ሆኖ ብቻ የሚቀረው ማንም ለማስተላለፍ የማይቻለው ይኽም የእነርሱ የትንሣኤ የዐይን ምስክርነት መሆናቸው ነው። ይኸንን አንደኛይቱ የዮሐንስ መልእክት ምዕ. 1 ቍ.1፦ “ከመጀመሪያው ስለ ነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይናችን ያየነው የተመለከትነው በእጆቻችን የዳሰስነው ነው” በማለት ያረጋግጥልናል ብለዋል።
የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አድማስነት በሐዋርያት ላይና በእነሱ ተከታዮች ላይ ተወስኖ የሚቀር አይደለም። የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ “መላ ቤተ ክርስቲያን ወደ ዓለም ሁሉ የተላከች በመሆንዋ ሐዋርያዊት ነች፣ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አባላት (ክፍለ አካል) የዚህ ተልእኮ ተሳታፊዎች ናቸው በ ቍ. 863 ተብራርቶ ይገኛል” በማለት ያረጋግጥልና። ሐዋርያዊነት የተለያየ ቅርጽ (በመንፈስ ቅዱስ ስጦታችዎና ጥሪ) የሚላበስ ቢሆንም ቅሉ ከቅዱስ ቁርባን የሚፈልቀው የሚሠዋ ፍቅር ዘወትር የሐዋርያዊነት ነፍስ ነው” (ቍ. 684 ተመልከት)።
የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የዓለማውያን ምእመናን ሱታፌ አቢይ ግምት በሚሰጥ አገላለጥ ያስተጋባዋል፣ ምክንያቱም በክርስቶስ የክህነት የነቢያዊ የንጉሣዊ ተልእኮ ሱታፌ ያላቸው በመሆኑም ነው። ስለዚህ ዓለም እንዲቀደስ በሚኖሩበት ሕብረተሰብ ዘንድ እግዚአብሔርን እንዲመሰክሩና በራሳቸው ውስጥና በዓለም ላይ ያለውን የኃጢአት ባርነት መንግለው ለመጣል ኃይል አላቸው (ቍ. 941-943 ተመልከት) በማለት ያቀረቡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.