2013-08-01 08:50:53

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የትዊተር መልእክት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በብራዚል የተከበረው 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መንፈስ የሚያጎላ መልእክት @Pontifex በተሰየመው በትዊተር የማኅበራዊ ማገናኛ ድረ ገጽ ባለው የግል አድራሻቸው አማካኘነት፦ በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በአንድነት አሜን ያልነውን እምነት ዕለት በዕለት በመኖር እንቀጥልበት” የሚል የምክር ቃል እንዳስተላለፉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስነታቸው በዚያኑ በትላንትናው ዕለት የምስጋና መንፈስ የተሞላው፦ “በሪዮ የተኖረው ሳምንት ፈጽሞ የማይረሳ ተመክሮ ነው፣ ለሁላችሁ ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ፣ ስለ እኔ ጸልዩ” የሚል መልእክት ማስተላለፋቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.