2013-07-30 08:58:24

የሪዮ 28ኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተፈጸመ ፡


በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ላይ ሲካሄድ የሰነበተው ዓለም አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተጠናቅቀዋል ።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ መንበረ ሐዋርያቸው ብሰላም ተመልሰዋል ።ከዚህ ቀጥለን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥናትና ሰንበት በሪዮ ደ ጃነይሮ ላይ ያካሄድዋቸው ሐዋርያዊ ፍጻሜዎች እንመለከታለን ፡ ጥዋት በሪዮ ሰዓት አቆጣጠር ስምንት ሰዓት ከሀያ ወደ ኮፓ ካባና ባሕር ተጉዘዋል ።በፕርግራሙ መሠረት ሥርዓተ ቅዳሴው ካምፑስ ፊደይ ዘ ጓራቲባ በተባለ መካን ለማከናወን ብታቀድም በመጥፎ የአየር ጸባይ መለወጡ ተመልክተዋል ።ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኮፓካባና እንደ ደረሱ የሪዮ ደ ጃይነሮ ሊቀ ጳጳስ በብጹዕ አቡነ ጅዋው የሚመሩ ካርዲናላት ጳጳሳት ካህናት ደናግላን እና በዚሁ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊ ወጣቶች ምእመናት እና ምእመናን ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል ። በዚሁ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የተመራ 28ኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፍጻሜ ሥርዓተ ቅድሴ ሶውስት ሚልዮን ህዝብ መገኘቱ ከቦታው የደረሰን ዜና አመልክተዋል።በዚሁ 28ኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ከዓለም ዙርያ ሪዮ ደ ጃነይሮ የገቡ ወጣቶች በሁለት ሚልዮን እንደሚገመቱ የተመለከተ ሲሆን ሶስት ሚልዮን ህዝብ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ መሳተፉ ተገልጠዋል።የብራዚል እና አረጀንቲና መራኅያነ መንግስታት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች በዚሁ የወጣቶች ዓለም አቀፍ ቀን ፍጻሜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ መሆናቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ፡ የተወደዳችሁ እኅቶቼ ወንድሞቼ እና ወጣቶች ሂዱ እና የሁላቸውንም ሐዋርያት እንዲሆኑ አድርጉ በማለት ነፍስ ወከፋችሁን ይጠይቃል ። ከዓለም ዙርያ ከመጡ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማሳለፍ እጂድ ደስ ይላል እዚህ ሪዮ ላይ ያደረግነው ተመኩሮ ለሌሎች ማሳለፍ አለብን ያሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት እንድንሆን እና ለዓለም ህዝቦች ቃላ ሰናየ ቅዱስ መጽሐፍ እንድንሰብክ ይጠይቀናል ብለውል።በማያያዝም የዕለቱ ቃለ ወንጌል ለማገልገል ሂዱ እና አትፍሩ ይለናል ብለዋል ቅድስነታቸው ።እዚህ ሪዮ ደ ጃነይሮ ላይ በጋራ ሆነን የሃይማኖታችን እምነትን አሳድሰናል ጸልየናል አስተንትናነናል ግሮም ቀናት አሳልፈናል ።
እምነት ህያው የሚሆነው በግብር ሲተረጐም መሆኑ ያወሱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወታችን ጌታ መሆኑ ዘወትር ማሰብ ማስተንተን እና መጸለይ ይገባናል በማለት ሰብከዋል ።ኢየሱስ ክርስቶስ ከፈለገችሁ ግዜ ካላችሁ ሄዱ እና የዓለም ህዝቦችን ሐዋርያት አድርጉ ሳይሆን ሄዱ እና ሐዋርያት አድርጉ ነው ያለው እና ግዴታችን መሆኑ መገንዘብ አለብን ብለዋል ቅድስነታቸው ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በኮፓካባና ብራዚል ባሕር ዳርቻ በመሩት ሥርዓተ ቅዳሴ ያሰሙ ስብከት በማያያዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍጥረት አዳም ስለሚያፈቅረው እና የእግዚአብሔር ምሕረት ለመግለጽ እኛን ለማዳን ሕይወቱ አሳልፎ ሰጥተዋል እና መድኅን ዓለምን መውደድ እና መከተል አለብን ብለዋል።ቃለ እግዚአብሔር ለማብሰር በምንጓዝበት ግዜ እሱ ዘወትር ከኛ ይጓዛል ብቻችንን አይተወንም እና ፍራቻ ማስወገድ አለብን ያሉት ቅድስነታቸው የተወደዳችሁ ወጣቶች ሳትፈሩ ሐዋርያት ሁኑ እና ለዓለም ቃለ ሰናየ አብስሩ
ካሉ በኃላ በሥርዓተ ቅዳሴ ከተሳታተፉ በወል መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል። በሥርዓተ ቅድሴ ለተሳተፉ ሁሉ አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።ፓፓ ፍራንቸስኮ ሶውስት ሚልዮን ህዝብ የተገኘበት ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተጠናቀቀ ወደ ቤተ ሊቃነ ጵጵስና ሱማሬ ተመልሰዋል። ከቀትር በኃላም በሪዮ ሰዓት አቆጣጠር 16 ሰዓት ላይ በሱማሬ የጥናት ማእከል በአኅጽሮቱ ቸላም ከሚጠራው የላቲን አመሪካ ረኪበ ጳጳሳት ምክር ቤት አባላት ጋር መገኛኘታቸው ተመልክተዋል።ከየላቲን አመሪካ ረኪበ ጳጳሳት ምክር ቤት አባላት የተካሄደው ግንኙነት እንደተጠናቀቀም ወደ ሪዮ ማእከል ተጉዘው በዚሁ ለዓለም አቀፍ የወጣቶች
ቀን በገዛ ፈቃዳቸው ካግለገሉ ተናንኝተው የምስጋና ቃል አሰምተዋል።
በሪዮ ሰዓት አቆጣጠር 18 ሰዓት እዚህ ሮም ሌሊት 23 ሰዓት መሆኑ ነው ወደ ሪዮ ደጃነይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተጋዙ ሲሆን በየከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ የሚመሩ ውሉደ ክህነት ምክትል መራሄተ መንግስት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቅድስነታቸውን ለመሸኘት በአውርፕላን ማረፊያ መገኘታቸው ይታወቃል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ ሮም ከመነሳታቸው በፊት አሁን ከትንሽ ግዜ በኃላ ብራዚልን ትቼ ወደ ሮም አቀናለሁ ፡ በብራዚል ቆይታየ ለተደረገልኝ ፍቅር የተላበሰ መስተንግዶ አመስግናለሁ ።ትልቅ የብራዚል ህዝብ ትልቅ ሰብአዊ ልብ እንዳለው ለመረዳት ችያለሁ ያሉት ፓፓ ፍራንቸስኮ ፡ ብራዚል የሚናፈቅ ሀገር መሆኑ ጠቅሰው እግዚአብሔር ይስጣችሁ ይባርካችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን በማለት የሃይማኖት እና መንግስት ከፍተኘ ባለስልጥናትን ተሰናብተብተዋል ። ዛሬ ረፋድ ላይ ከቀትር በፊት በሮም ሰዓት አቆጣጠር አስራ ሀንድ ሰዓት ተኩል በሰላም ተመልሰዋል። ይህ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ላይ የተካሄደው ሐዋርያዊ ጉብኝት ከጣልን ውጪ 138ኛ የአርእሰተ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ይታወቃል።ቀጣዩ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በ2016 በክራኾቪያ ፖላን ላይ እንዲከናወን መወሰኑም ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.