2013-07-29 16:19:10

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ የግኑኝነት ባህል ማነቃቃት የከተሞች ውጫዊ ክልል ቀዳሚ ምርጫችን ይሁን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በብራዚል ሪዮ ከተማ በሚገኘው ካቴድራል በዚህ 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የተገኙት ከመላ አገሮች የተወጣጡ ብፁዓን ካርዲናሎች ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን የተሳተፉበት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታጅበው በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ የሚያገል ባህል የሚያነቃቃው የሃሰት ሰብአዊ ኤኮኖሚያዊ ሂደት መመሪያ መቃወም የግኑኝነት ባህል ማነቃቃት እንዲሁም በከተሞቻችን ውጫዊ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል እናስቀድም በማለት ወጣት ትውልድ በግኑኝነት ባህል ማነጽ ይጠበቅብናል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሮበርቶ ፒየርማሪኒ ገለጡ።
ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በጠቅላላ ወንጌልን እንዲያበስሩና የሱታፌና የግኑኝነት ባህል አገልጋዮች እንዲሆኑ የተጠራችሁ ናችሁ በማለት የምንኖርበት ወቅታዊው ዓለም መተባበር መደጋገፍ የሚለው ስለ ሌላው የማሰብ ባህል እንደ ኋላ ቀርነት ወይንም ስድብ የሚመመለከት ባህል የሱታፌና የግንኙነት ባህል በማነቃቃት መቃወም ይገባናል፣ የሐዋርያዊ አገልግሎታችን ፍርያማነትና ቅልጣፌ ዋስትና በክርስቶስ የሚኖር ህይወት ነው እንዳሉ ፒየርማሪኒ አስታወቁ።
የወንጌላዊ አገልግሎታችን ፍርያማነት የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ፈጠራነት ወይንም የሚካሄዱት ስብሰባዎችና ግኑኝነቶች የምንወጥነው የሐዋርያዊ ግብረ ኖልው አገልግሎት ሳይሆን ለክርስቶስ ታምኝ መሆን ነው በማለት በዕለታዊ ጸሎት ዕለታዊ ከቅዱስ ቁርባን ጋር የምንፈጽመው ግኑኝነት አማካኝነት የተናቁት የተነጠሉት ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል በማስቀደም ለማገልገል ይኸንን ለማስተንተን ለመጸለይ እና ለመኖር የተጠራን ነን ካሉ በኋላ ከክርስቶስ ጋር መሆን ተነጥሎ መኖር ማለት ሳይሆን ከሌላው ጋር ለመገናኘት መነሣት ማለት ነው ብለው እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታ “በድኾች ክርስቶስን ለማገልገል ዕድል የሚሰጥ ጥሪ በመቀባላችን ኩራት ሊሰማን ይገባል” ያሉትን ሃሳብ ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ ክርስቶስን በድኾች ለማገልገል የተጠራን ነን፣ ወንጌላዊ ልኡክነት የክርስትና ሕይወት መሠረት የሆነው የተቀበልነው የምሥጢረ ጥምቀት ውጤት ነው። በመሆኑም በቅድሚያ በቤታችን ዕለታዊ ሕይወታችን በምንመራበት ሥፍራ ሁሉ ወንጌል በማበሰር የሚኖር ሕይወት በወጣቱ ትውልድ እውቅና አግኝቶ በዚሁ ተልእኮ ንቁ ተሳታፊ ለማድረግ ለዚህ የህብረተሰብ ክፍል መደገፍ ያለው አስፈላጊነት ቅዱስ አባታችን አብራርተው፣ ወጣቱ ትውልድ ማዳመጥ ችግሩን ቀርቦ መረዳት አብሮ ከእነርሱ ጋር መጓዝ ያለው አስፈላጊነው እንዳሰመሩበት የቫቲካን ልኡክ ጋዜጠኛ ፒየርማሪኒ ገለጡ።
የምናነቃቃው የምንከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ከከተሞቻችን ውጫዊ ክፍል የሚጀምር በማድረግ ሩቃ ካሉት ከተናቁት ከተገለሉት የሚጀምር ግብረ ኖልዎ መሆን እንዳለበትና የተናቀው ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ነው የጌታችን የክብር እንድግዳ፣ እነርሱን የትም በመሄድ መፈለግ ይገባናል ካሉ በኋላ ሌላውን የሚያገል የሚነጥል ተጠቅሞ መጣል የሚለውን ባህል ለአረጋውያን ለድኾች ሳይታሰብ የተጸነሰ ነው የሚለው አመለካከትና ተግባር የሚያስፋፋው ነጣይ ባህል እንቃወም፣ ስለዚህ ቆም ብለን በመንገዶቻችን ዳር ወድቀው ለሚገኙት ድኾች ጎንበስ በማለት፣ አምራችነትና ግብረአዊነት የሚለው ዘመናዊው ባህል ያለው አደጋኛነቱንም ጠቅሰው፣ እነዚህ ሁለት መሠረታዊ መመሪያዎች የሰው ልጅ ክብር መመዘኛ እየሆኑ ሕጻናት አረጋውያን ህሙማን እየተገለሉ ናቸው፣ ስለዚህ የተቀበልነው የምንከተለው ክርስቶስን በመምሰል ስንኖር ብቻ ነው በክርስቶስ የተናቁት የተነጠሉን በማገልገል ሌላው እንዲለወጥ የምናነቃቃው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፒየርማሪኒ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.