2013-07-24 16:02:35

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በማስደገፍ የቫቲካን ረዲዮ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮዋልዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. “ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሰጠው የድኅነት ሥፍራ ነች” በሚል ቤተ ክርስቲያንን በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ያላት ተልእኮ የሚተነትን ባቀረቡት 36ኛው አስተምህሮ፦ የክርስቶስ ድኅነት ሥፍራ ነች የሚለው ቃል ክርስቲያን ያልሆነውን ከዚህ የክርስቶስ ድኅነት የሚያገል ነው ማለት ሳይሆን ሁሉም የሰው ልጅ ከኢየሱስ ጋር ግኑኝነት እንዲኖረው ለማድረግ የምትጠመድ መሆንዋ የሚገልጥ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን እንናዘዛለን፣ ካቶሊክ ማለት ኵላዊነት ማለት ነው፣ ይኽም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 830፦ “ቤተ ክርስቲያን ካቶሊካዊት ናት፦ ካቶሊክ የሚለው ቃል….ኩላዊ ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን በሁለት ትርጉም ካቶሊክ ናት፣ አንደኛው ቤተ ክርስቲያን ካቶሊካዊት ናት ምክንያቱም ክርስቶስ በውስጧ አለና። ኢየሱስ ክርስቶስ ባለበት ሁሉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አለች” በማያያዝም በቁ. 831፦ በሁለተኛ ደረጃ ካቶሊካዊነቷ፣ “…ምክንያቱ ለመላ ሰው ዘር የሚበጅ ተልእኮ ለመፈጸም ከክርስቶስ የተላከች በመሆኗ ነው” በማለት አብራርተው፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባል የሚሆነው ማን ነው ወይንም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወገን ማን ነው? የሚለው ጥያቄ ማንሣት ግድ ይሆናል፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትህርተ ክርስቶስ መዝገብ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ በመጥቀስ፣ ሕዝበ እግዚአብሔር፦ ሰዎች ሁሉ ወደዚህች የሕዝበ እግዚአብሔር ካቶሊካዊት አንድነት ተጠርተዋል…በተለያዩ መንገዶች የተጠሩት ወይም እንዲመጡ የታዘዙት የካቶሊክ ምእነናን ሊሎች በክርስቶስ የሚያምኑና በመጨረሻም የሰው ልጆች ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋ ለድኅነት ተጠርተዋል” ሲል በቁጥር 836 ያለውን ጥቅሰ አማካኝነት ተንትነው፣ የቤተ ክርስቲያን አበው፣ ብዙውን ጊዜ በመደጋገም ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መዳን/ድኅነት የለም” ይኽ ማለት ግን የሚድኑት ካቶሊካውያን ብቻ ናቸው ማለት አይደለም፣ ቤተ ክርስቲያን ከድኅነት ምሥጢር የምታገል ሳይሆን የምታጠቃልል የምታቀርብ ነች፣ ሆኖም እያንዳንዱ መዳን የቤተ ክርስቲያን እራስ ከሆነው ከክርስቶስ የሚመነጭ ሲሆን ይኽ ማለት ደግሞ እያንዳንዱ የመዳን ጸጋ በቤተ ክርስቲያን የሚያልፍ መሆኑ የሚያመለክት ነው ካሉ በኋላ የሌላ ኃይማኖት ተከታይ ምንም’ኳ የኢየሱስ አዳኝነት ላይ የማያምን ቢሆንም ቅሉ ይድናል ስንል ከኢየሱስ ተልእኮና ከእርሱ ቤተ ክርስቲያን ጋር ጥልቅ ትስስር ሊኖረው ያስፈልጋል ብለዋል።
ካቶሊካዊነትት በኢየሱስ በሚሰጠው ጥሪ የሚገለጥ መሆኑ ማቴዎ ወንጌል ምዕ. 28 ቁ. 19፦ “…እንግዲህ ወደ ዓለም ሕዝብ ሁሉ ሂዱ በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርግአቸው” የሚለው ቃል መሠረት አብራርተው፣ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በባህርይዋ ልእክት ነች፣ የእርሷ ተልእኮ ልኡክነት ጥልቅ ግፊትም እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ዘር ያለው ፍቅር ነው (ቍ.851 ተመልክተ)።
ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለውም “…የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን እንዲያውቁ ነው” (1ጢሞ. 2.4) ለዚህም ነው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፍርዱ ለእግዚአብሔር በመተው ወንጌልን ለሁሉም ሰው ዘር የምታበስረው፣ ስለ ሁሉም የምትጸልየው በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.