2013-07-24 16:07:01

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ


RealAudioMP3 የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የብራዚል ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ጉብኝት በማስድገፍ ትላትና የቅዱስነታቸው በብራዚል የመጀመሪያው ቀን ቆይታ በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በቅድሚያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሪዮ ከተማ እንደደረሱ ከአየር ማረፊያ ተነስተው እስከ ጉዋንዳባራ ሕንፃ በተደረገው የመኪና ጉዞ ያጋጠመው የትራፊክ መጨናነቅ በርግጥ ሕዝቡ ቅዱስነታቸውን ለመቀበል ካለው ተስፈኛነት ባህርይ ተገፋፍቶ ወደ ክልሉ በመጉረፉ ምክንያት በርግጥ የመኪናው ጉዞ አስቸጋሪ መስሎ ነበር የታየው ሆኖም ግን ሕዝቡ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያለው ፍቅር ለመግታት አይቻልም ሆኖም ቀጥሎ ለሚከናወነው የጸጥታውና ደህንነት እቅድ ምንና እንዴት መሆን እንዳለበት ምልክት የሰጠ አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ብራዚላውያን በጠቅላላ ላቲን አመሪካ ቅዱስ አባታችን በቅርብ የሚያውቁትና ይኽ ክፍለ ዓለም እንግዳ ተቀባይነቱና ወዳጅነቱ የጎላበት ሁነት መሆኑ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን በመጀመሪያ ባሰሙት ይፋዊ መልእክት በተደጋጋሚ ልብ የሚል ቃል አስደምጠዋል፣ በእውነቱ የብራዚላውያንን ልባዊነትን የሚያጎላ መሆኑና በብራዚል መስተንግዶ እንዲደረግልኝ ይኸንን ልብ በትህትና አንኳኳለሁ በማለት የገለጡት ቤተ ሰብአዊ ሁኔታ ቅዱስነታቸው ቀደም ብለው ከሮማ ወደ ብራዚል ሲነሱ በሚበሩበት አየር ለነበሩት 70 ከተለያዩ አገሮች ለተወጣጡት የቲቪና የኅትመት ልኡካን ጋዜጠኞች ያሳዩት ቅርበት ጭምር የሚያስታውስ ነበር ስለዚህ ቅዱስነታቸው በሚያካሂዱት ግኑኝነት ሁሉ ሰብአዊነት የሚያጎሉ መሆናቸው አባ ሎምባርዲ አብራርተዋል።
በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና በብራዚል ርእሰ ብሔር ሩሰፍ መካከል የተካሄደው ግኑኝነትም፣ የወጣቶች ጉዳይ የዳሰሰ በጠቅላላ በዓለማችን ክልል የሚታየው ማኅበራዊ ሰብአዊ ችግር፣ ማኅበራዊ ፍትህ፣ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ገልጠው፣ የብራዚል ርእሰ ብሔር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ማኅበራዊ ፍትህ በተመለከተ የሚሰጡት ትኵረት በዚሁ ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰጡት አስተምህሮና አገልግሎት በማድነቅ፣ ለየት ባለ መልኩ በኢጣሊያ ላምፐዱዛ ደሴት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት መጥቀሳቸውንም አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ በዓለማችን የሚታየው ውድቅ የሚያደርግ ባህል በግኑኝነት ባህል እንዲተካ ተጠቅሞ መጣል የሚለው ባህል በሰብአዊ ላይ እንዳይከወን የሚያሳስብ የቅዱስ አባታችን መልእክት የብራዚል ርእሰ ብሔር ብቻ ሳይሆን በሁሉም ተደማጭነት ያገኘ ሃሳብ ነው በማለት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የብራዚሉ የመጀመሪያው ቀን ምን እንደሚመስል እንዲህ ባለ መልኩ በማብራራት የሰጡት መግለጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.