2013-07-22 15:58:30

28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


RealAudioMP3 የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ በሚካሄደው 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለሚሳተፉት ከኢጣሊያ ሰበካዎች የተወጣጡት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የበጎ ፈቃድ ግብረ ሠናይ ተጠምደው ለሚያገለግሉት ወጣቶችን በሪዮ ከተማ ቆይታ የሚያደርጉበት ቤተ ኢጣሊያ” የተሰየመው የእንግዳ መቀበያ ሕንጻ መርቀው በከፈቱበት ዕለት እዛው ለሚገኙትን በዚሁ ዓቢይ የቤተ ክርስቲያን ሁነት በተለያየ መስክ አገልግሎት ለሚሰጡት ከኢጣሊያ ሰበካዎች ለተወጣጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አባላት ባሰሙት ቃል፣ “በዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለሚሳተፉት ሁሉ ወጣቶች ብርታትና ድጋፍ ሁኑ፣ በፊታችሁ የሚንጸባረቀው ፈገግታ ለወጣቱ ብርታትና ምስክርነት ሆኖ ድካም ፍጻሜ እንዳለው የሚመሰክር ኢየሱስ ወደ ሚጠብቀን መንገድ የሚመራ ይሁን” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ እዛው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ እነዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አባላት ካቶሊክ ወጣቶች በዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለሚሳተፉት ከመላ ዓለም ለተወጣጡት ተሳታፊ ወጣቶች ቅርብ በመሆኑ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። በዚህ አገልግሎት የኢጣሊያ ወጣቶች ሱታፌ በኢጣሊያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለወጣቱ ትውልድ ምንኛ ቅርብ መሆንዋ የሚመስከር ሠናይ ተግባር ነው ብለዋል።
በኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የወጣቶች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ተጠሪ ክቡር አባ ሚካኤል ፋላብረቲ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የኢጣሊያ ወጣቶች በተለያዩ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማለትም በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በሚሰናዳው መርሃ ግብር ከተጀመረበት ዕለት ጀምሮ ካለ ማቋረጥ በመሳተፍ ላይ ናቸው፣ ስለዚህ ልምድ ያካበቱ በመሆናቸው የሚሰጡት አገልግሎትና ሱታፌአቸው በእግዚአብሔር ድጋፍ የተዋጣለት መሆኑ ገልጠው፣ የብራዚሉ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለየት የሚያደረገውም ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው የተመረጡት የላቲን አመሪካ ተወላጅ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉበት ብሎም በተወለዱበት ክፍለ ዓለም የሚካሄድ በመሆኑ በተሳታፊ ወጣቱ ቁጥር ብዛትም እጅግ ከፍ ያለ እንደሚሆን የሚነገረለት ዓለም አቀፍ የወጣቶ ቀን ነው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.