2013-07-19 16:52:48

8ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሪዮ ዲ ጃነሮ ከሓምሌ 23 ቀን እስከ 28 2013፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሶስት ቀናት በኋላ 28ኛውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመምራት መጀመርያውን ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳሉ እንዲሁም በሪዮ ዲ ጃነሮ የሚገኙ የሥርዓቱ አዘጋጆች እንደሚያመለክቱት ወጣቶች ከመላው ዓለም እየተሰበሰቡ መሆናቸው በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የቦታው ወጣቶችም ሁሉን እያዘጋጁ መሆናቸው ተመልክተዋል፣
ባለፈው በዓለ ሆሳዕና ቅዱስነታቸው ሥልጣን ከያዙ ጥቂት ቀኖች ባስቆጠሩት ወቅት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተሰብስበው ለነበሩ ከ200 ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ስለዚሁ ከሶስት ቀናት በኋላ ሊካሄድ እየተዘጋጁ ያሉት 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አስመልክተው እንዲህ ብለው ነበር፣
“የተከበራችሁ ወጣቶች በሕዝቡ መካከል ሳልፍ ብዙ ወጣቶች በአደባባይ ስትገቡ አየሁ፤ በኢየሱስ አከባቢ የሆሳዕና ቅርጫፎች እያወዛወዛችሁ ትታዩኛላችሁ! በታላቅ ድምጽ ስሙን ስትጠሩና ከእርሱ ጋር በመሆናችሁ በደስታ ስትፈነጥቁ ትታዩኛላችሁ! በእምነት በዓሉ እናንተ ልዩ ቦታ አላችሁ! እናንተ የእምነት ደስታን ትሰጡናላችሁ! እምነትን ዘወትር ወጣት በሆነ ልብ እንኑረው ትሉኛላችሁ! በሰባና ሰማንያ የዕድሜ ዓመታትም ሳይቀር ወጣት ልብ ሊኖረን ይችላል! ከክርስቶስ ጋር ልባችን ፈጽሞ ሊያረጅ አይጭልም! ሁሌ ወጣት ነው! እኛ ሁላችን እንደምናውቀው እናንተም እንደምታውቁት ይህ የምንከተለው ንጉሥ ሁሌ ይሸኘናል! ሽኝቱም ልዩ ሽኝት ነው! ንጉሱ እስከ መስቀል የሚያፈቅር ንጉሥ ነው፤ ሰዎችን እንድናገልግልና እንድናፈቅርም ያስተምረናል፣” ብለው ነበር፣
ወጣቶ ዘወትር ደስታ ያመጣሉ ኢየሱስን ወጣት በሆነ ልብ እንድናፈቅረውም ያስተምሩናል፣ ሆኖም ግን ይህ ቅዱስነታቸው የሚገልጡት ደስታ ለየት ያለ ነው፣
“ደስታችን ብዙ ነገሮች ከማግኘት የሚወለድ ዳስታ አይደለም ነገር ግን አንድ ሰውን በማግኘት እርሱም ዘወትር በመካከላችን የሚገኝ ኢየሱስ ክርስቶስን በማግኘት የሚወለድ ደስታ ነው፣ ከእርሱ ጋር መሆናችን በማወቅ ደግሞ ፈጽሞ ብቻችን ለመሆን እንደማንችል በማወቅ ደግሞ ደስታችን ይልቃል፣ ይህም ደስታ በአስቸጋሪ ወቅትም በሕይወታችን ጉዞ ፈተናና ችግር በሚገጥመን ጊዜ ምናልባትም እንቅፋቶቹ የማይሸገሩ በሚመስሉን ጊዜም ሳይቀር እርሱ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላለ ደስታችን ህያው ነው፣” ሲሉ የክርስትያን ደስታ ጌታ ከእርሱ ጋር መሆኑን በማወቅና ብቻው እንዳልሆነ በማወቅ እንደሚወለድ ገልጠዋል፣
ሆኖም ግን ይህ ጉዞ ቀላል እንዳልሆነና ዘወትር ፈተና እንደሚያጋጥም በተለይ ደግሞ ጥንተ ጠላታችን የሆነ ዲያብሎስ አንዳንድ ጊዜ እንደ መል አከ ብርሃን ሆኖም ሊፈትነን ይችላል፣ ከዚህ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግና ወዲያው እምቢ ማለት እንዳለብን እንዲህ ሲሉ ገልጠው ነበር፣
“አትስሙት! ኢየሱስን እንከተል! እኛ ኢየሱስን እንከተላለን ከሁሉ በላይ ግን እርሱ እንደሚሸኘንና በትከሻውም እንደሚሸከመን እናውቃለን፣ የደስታችን ምስጢርም እዚህ ላይ ነው፣ በዚህ ዓለም እስካለን ደረስ ደግሞ ይህንን ተስፋ ይዘን መጓዝ አለብን፣ እባካችሁ ተስፋችሁን ማንም እንዳይሰርቅባችሁ ተጠንቀቁ! ተስፋችሁ እንዲሰርቁ ማንንም አትፍቀዱ! ይህ ተስፋም ኢየሱስ የሚሰጠን ተስፋ ነው፣” ብለው ካስተማሩ በኋላ ለ28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንዲህ ሲሉ ቀጥርዋቸው፣
“በታላቁ የብራዚል ከተማ እቀጥራችኋለሁ በደንብ ተዘጋጁ! ከሁሉ በላይ ደግሞ በማኅበሮቻችሁ ጥሩ ዝግጅት አድርጉ ምክንያቱም ይህ ግኑኝነት ለመላው ዓለም የእምነት ምልክት እንዲሆን ነው፣ ወጣትች ለዓለም ክርስቶስን መከተል መልካም ነገር ነው! ከክርስቶስ ጋር መለካም ነው! የኢየሱስ መል እክት መልካም ነው! ከገዛ ራስ ወጥቶ ኢየሱስን በዓለምና በኑሮ ተገለው ለሚገኙ ማብሰር መልካም ነው! ሶስት ቃላት አስታውሱ ደስታ መስቀል ወጣቶች! ብለው ነበር፣

ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በሚባለው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን እምነት የግላችን አይደለም ከሌሎች ጋር መካፈል ያለበት ጉዳይ መሆኑን የሚገልጥ አጭር መልእክት “በዚሁ የእምነት ዓመት እምነት የግላችን ንብረት አለመሆኑን እናስታውስ፣ ከሌሎች ጋር እንከፋፈለው፤ እያንዳንዱ ክርስትያን የኢየሱስ ሐዋርያ ነው፣” ብለው ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.