2013-07-18 10:46:49

ለተቸግሩትና ለደከሙት ከፍ ያለ ርኅራኄና እርዳታ ማድረግ የቤተ ክርስትያንን በሮች ይከፍታሉ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከትናንትና ወዲያ በላምፐዱሳ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ባለነው ዘመን የሚታየውን ግድየለሽነት ለማሸነፍ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተቸግሩትና ለደከሙት ከፍ ያለ ርኅራኄና እርዳታ ማድረግ የቤተ ክርስትያንን በሮች ይከፍታሉ፣ ሲሉ የዕለቱን ወንጌል በመጥቀስ ኃይለኛ መልእክት አስተላልፈዋል፣ ይህን መልእክት ከትናንትና ወዲያ ብቻ ሳይሆን በአስተምህሮቻቸውና በስብከቶቻቸው ደጋግመው አስመረውበት ነበር፣
“ይህ ኢየሱስ ያሳየው ከፍ ያለ ርኅራኄ የሚገልጠው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚያሳይ የእርሱ ምሕረት ማለትም እግዚአብሔር የሰው ልጆች መስኪንነት ሥቃይና ችግር ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ከፍ ያለ ርኅራኄ የሚለው የቅዱስ መጽሓፍ ቃል የእናት ሆድን ማለት ሆደ ባባነትን ያመለክታል፣ እናት ሁሌ በልጆችዋ ሥቃይ ለየት ያለ ርኅራኄ ታሳያለች፣ እግዚአብሔርም ለልጆቹ እንደዛ እንደሚያፈቅራቸው ቅዱስ መጽሓፍ ያረጋግጥልናል፣ የዚህ የምሕረትና ይቅር ባይነት ፍቅር ፍሬ ምን ይሆን! ሕይወት ነው ሲሉ ባለፈው ወርኃ ሰኔ ባስተማሩት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ አሳስበው ነበር፣ እንዲሁም ይህ ፍቅር ጽኑ መሆኑንም በቅድስት ማርታ ቤተ መቅደስ ሰኔ 7 ቀን ባደረጉት ስብከት ገልጠው ነበር፣ በዚሁ ስብከት ቅዱስነታቸው የእግዚአብሔር ፍቅር በቃላት ብቻ የሚገለጥ ሳይሆን በምንገንበት ቦታና ሁኔታ ተገኝቶ ቅርባችን ሆኖ ፍቅሩን እንደሚገልጥልን እንደሚያቅፈንና እንደሚሻሻን ገልጠው ነበር፣ እስከ መጨርሻ ፍርድም እንደዛ እንደሚቀጥልና የመጨረሻው ፍርድ ሊያስፈራን እንደማይገባ ምክንያቱም እኛ ፍቅሩን እስከምንማር ድረስ በት ዕግሥትና በምሕረት እንደሚጠባበቀን አሳስበው ነበር፣ እንዲሁም በግንቦት 25 ቀን በቅድስት ማርታ ቤተ መቅደስ ባደረጉት ስብከት፣
“ዛሬ ኢየሱስን እንሰብ፤ እርሱ ዘወትር ሁላችን እንድንቀርበው ይፈልጋል፣ የዋህ የሆነውን የእግዚአብሔር ሕዝብን እንሰብ፣ ሕዝቡ ወደ ኢየሱስ ሊቀርብ ይሽቀዳደም ነበር፤ በሌላው በኩል ደግሞ ባለበጎ ፈቃድ የሆኑ ክርስትያኖችን እንሰብ እነኚህ ሁሌ ልቦቻቸውን ለእርሱ ከመክፈት ይልቅ እየዘጉዋቸው ስሕተት ሲፈጽሙ እናያለን፣ ስለዚህ ጌታን ወደ ቤተ ክርስትያን የሚቀርቡ ሁላቸው የዚሁ የኢየሱስ ፍቅርን ለማግኘት ወደ ቤተ ክርስትያን እንዲቀቡና የቤተ ክርስትያኑም በሮች ዘወትር ክፍት ሆነው እንዲያገኝዋቸው እንለምነው ብለው ነበር፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ አት ፖንቲፊከስ በሚለው በዘመናችን መገናኛ ብዙኃን ትዊተር በሚባለው የኢንተርነት መል እክታቸውም “ክርስትያን ሁሌ በተስፋ የተሞላ ነው! በምንም ተአምር ተስፋ መቍረጥ የለበትም፣” ብለው እንደላኩ ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.