2013-07-18 10:32:46

28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሪዮ ዲ ጃነሮ ከሓምሌ 23 ቀን እስከ 28 2013፣


የመላው ዓለም ካቶሊካውያን ወጣቶች በታላቅ ጉጕት የሪዮ ዲ ጃነሮ 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለማክበር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ቅዱስነታቸው እ.አ.አ ሓምሌ 24 ቀን በአፓረሲዳ እንደሚገኙና በጥቍር ድንግል የምትታወቀው እመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር ታላቅ ትስስር እንዳላቸው ተገልጠዋል፣ ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ ከተመረጡ ወዲህ ይሄው የመጀመርያዊ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞ መሆኑና አፓረሲዳን ሲጐበኙ ተል እኮ አቸውን ለእመቤታችን ድንግል ማርያም እንደሚያማጥኑም ተመልክተዋል፣ ተደጋግሞ እንደተገለጠው የዘንድሮው ዓለም አቀፍ ወጣቶች ቀን ከሓምሌ 23 እስከ 28 ቀን እንደሚካሄድና እንደ መሪ ቃል የሚጠቀመዉም ጌታ ለሐዋርያቱ ያዘዘው “ሂዱ አህዛብን ሁሉ የኔ ደቀ መዛሙርት አድግርዋቸው” የሚል ነው፣
ዘንድሮ ብዙ ነገሮች ባልታሰበ ሁኔታ እየተካሄዱ ቢሆኑም የደቡብ አመሪካ የመጀመርያ ር.ሊ.ጳ ዓለም አቀፍ የመጀመርያ ሐዋርያዊ ጉዞው በትውልድ አገሩ በደቡብ አመሪካ ማካሄዱ ግን በአስገራሚ ሁኔታ ከቅዱስነታቸው በፊት የነበሩ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛም ለር.ሊ.ጵጵስና በተመረጡበት ዘመን የመጀመርያዊ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞ አቸው ትውልድ አገራቸው ጀርመን ነበር፤ አጋጣሚውም ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ነበር፣
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የቦነስ አየርስ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት እምብዛም ከሥራቸው የማይንቀሳቀሱ ስለነበር በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳትፈው አያውቁም፤ ዘንድሮ ለመጀመርያ ግዝያቸው ነው በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሲሳተፉ፣
የደቡብ አመሪካ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በእድገት ውስጥ የምትገኝና ብዙ ጥረት እያደረገች ናት፣ ረኪበ ጳጳሳቱም ሁሌ በብርቱ ሥራ ይገኛል፣ የተለያዩ ሰነዶችም ያዘጋጃል፣ ታላቅ እውቅና ካላቸው የደቡብ አመሪካ ረኪበ ጳጳሳት ሰንዶች አንዱ በአፓረሲዳ ሰነድ የሚታወቀው መምርያ ደንብ ነው፣ ይህ ሰነድ አጋጣሚ ሆኖ በ2007 ዓም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ብራዚልን ከጐበኙ በኋላ ነው የተደመደመው፣ ሌላው አጋጣሚ ደግሞ ይህንን ሰነድ ያዘጋጀው በአምስተኛው አጠቃላይ የላቲን አመሪካ የጳጳሳት ጉባኤ የተመረጠ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢና የሰነዱ አዘጋጅ ያኔ ካርዲናል በርጎልዮ የቦነስ አየርስ ሊቀ ጳጳስ የነበሩ ቅዱስነታቸው ነበሩ፣
አፓረሲዳ የደቡብ አመሪካ የእመቤታችን መካነ ንግደት የሚገኝበትና በየዓመቱ ከስምንት ሚልዮን በላይ ነጋድያን የሚጸልዩበት የእመቤታችን ድንግል ማርያም ታናሽ ጥቁር ሓውልት የሚገኝበት ነው፣ ይህች ታናሽ ጥቁር ሓውልት ረዥም ታሪክ ያላት ሆኖ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ሕዝቡ በባርነት ሲሰቃይ ሓውልትዋም ጠፍታ ኖራ በ1717 በርዮ ፓራይባ ወንዝ በዓሣ አጥማጆች ተገኘች፣ ለብራዚላውያን እናትና ተስፋ የሆነችው የዚች እመቤታችን መንፈሳዊ ንግደት ብዙ ሰዎች ያዘወተሩት ነው፣ በዘመናችን በዚሁ መካነ ንግደት በታላቅ መንፈሳውነት በቦታው የተገኙ ሁለት ር.ሊ.ጳ ብፁዕ የውሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1980 ዓም እንዲሁም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በ2007 ዓም ነበሩ፣
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስም ባለፈው እሁድ በካስተል ጋንደልፎ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካሳረጉ በኋላ በቦታው ለነበሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ም እመናንና ነጋድያን ስለ የመጀመርያዊ ሐዋርያዊ ጉዞ አቸው እንዲህ ብለው ነበር፣
“ከስምንት ቀናት በኋላ ወደ ብራዚል እጓዛለሁ ሆኖም ግን ብዙ ወጣቶች ቀድመውኝ ይሄዳሉ፣ የብራዚል ጠባቂ የሆነችው የአፓረሲዳ እመቤታችን ድንግል ማርያም የዚሁ መንፈሳዊ ንግደት ተሳታፊዎች እንድትመራና ልቦቻቸው ክርስቶስ ለሚሰጣቸው ሐዋርያዊ ተል እኮ እንድትከፍት ስለዚሁ ታላቅ መንፈሳዊ ንግደት እንጸልይ ሲሉ አሳስበዋል፣
ቅዱስነታቸው ስለ አፓረሲዳው ሰነድ አንድ ጊዜ “የአፓረሲዳ የደቡብ አመሪካ ረኪበ ጳጳሳት ጉባኤ ለደቢብ አመሪካ ቤተ ክርስትያን የጸጋ ጊዜ ነበር” ብለው እንደገለጡትና ሰነዱንም ለደቡብ አመሪካ ቤተ ክርስትያን እንድ ኢቫንጀሊ ኑንስያንዲ እንደሆነላት አውክተው ነበር፣
ሰነዱን የተመለክትን እንደሆነ ቅዱስነታቸው የሚከተልዋቸው ብዙ ነገሮች ይገኙበታል፣ ለምሳሌ ያህል የቤተ ክርስትያንና የመላው ሕዝበ እግዚአብሔር ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲሁም ወደ እውነተኛ ሕይወት መጠቀም ያለንበት መምርያ ወንጌል መሆኑን የሚያመለክትና የስብከተ ወንጌል ጣዕምና መጽናናት ይገኙበታል፣ ያኔ ቅዱስነታቸው በግንቦት 16 ቀን 2007 ዓም በጉባኤው ባደረጉት ስብከት “ከገዛ ራሳችን ወጥተን ወደ ተገለሉና ከመካከል ወደ ወሰን ለተገፉ ሰዎች ወንጌልን መስበክ እንደሚያስፈልግና የሚፈጸሙትን ኢፍትሃዊ ተግባሮች በማውገዝ ብቸኝነትና ችግር ያጎሳቆላቸውን ሰዎች ማጽናናትና ወንጌል መስበክ ያስፈልጋል” ብለው ነበር፣








All the contents on this site are copyrighted ©.