2013-07-17 16:01:34

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 የቫቲካን ረዲዮ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮዋልዝዪክ 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት በተከታታይ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ዙሪያ የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. “ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ነች፣ የምትባለበት ምክንያት አባላቷ ቅዱሳን ስለ ሆኑ ሳይሆን ርእሰ ቤተ ክርስቲያን የሆነው ክርስቶስ ቅዱስ በመሆኑ ላይ የጸና ነው” በሚል ቤተ ክርስቲያን ማእከል ያደረገ ባቀረቡት 35ኛው ክፍለ አስተምህሮ፦ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምናለሁ” ስንል ብዙዎች እንዴት ተኩኖ ነው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ኃጥአን እያሉ ቅድስት የምትባለው የሚል ጥያቄ በመደጋገም ሲቅርብ ይሰማል፣ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ተብላ ስትገለጥ፣ አባላቷ አለ ሐጢአት ናቸው ለማለት አይደለም፣ ባንጻሩ ኢየሱስ፦ “እኔ የመጣሁት ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት እንጂ ጻድቃንን ወደ ንስሓ ለመጥራት አይደለም፣ (ማቴ. 9.1)” በማለት የሰጠው ቃል ማእከል በማድረግ አብራርተዋል።
በቅድሚያ ቤተ ክርስቲያን የእርሷ እራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ በመሆኑ ነው ቅድስናዋ። በመቀጠልም በውስጧ የተለያዩ የድኅነት ማስተግበሪያ ቅዱሳት ምስጢራት ይኽም ለሰው ልጅ ቅድስና የሚበጅ የድኅነት ማስተግበሪያ ያላት በመሆኑ ነው። ቅዱስ ቁርባንና ሌሎች ቅዱሳት ምሥጢራት የእግዚአብሔር ቃል ይኽም ቅዱሳት መጻሕፍት የታደለችም ነቸ። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቅዱሳንና ብፁዓን ልጆች ያቀፈች ነች። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሠረት የምእመናን ተስፋን በማጽናት አብነትና አማላጅ የሆኑትን ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን ታቀርባለች፣ የሰው ልጅ ቅድስና በእግዚአብሔር ቅድስና ላይ ሱታፌ ያለው ዘወትር የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑ አብራርተው፣ አክለውም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቍ. 827፦ “ክርስቶስ ቅዱስ ንጹሕ እና ነውርም የሌለበት ኃጢአትን የማያውቅ ነገር ግን የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ሲል ብቻ የመጣ ነው። ሆኖም ቤተ ክርስቲያን ኃጢኣተኞችን በውስጧ የያዘች በመሆንዋ ቅድስትም ዘወትር ደግሞ የመንጻትን የምትሻ ናትና የንስሐና የተሐድሶን መንገድ ትከተላለች” የሚለው አስተምህሮ ጠቅሰው፦ በቤተ ክርስቲያን ኃጢአተኞች ለመኖራቸው ጌታን አመሰግነዋለሁ፣ ምክንያቱን በውስጧ ለእኔ ስፍራ አለኝ ማለት ነው” ብለው፣ ኢየሱስ የሰው ልጅ በኃጢአት ላይ እንዳይቀር ስለእኛ ሞቷል ሞትን አሸንፎም ተነስቷል፣ ቅድስ ጳውሎስ ለኤፈሶን በጻፈው መልእክቱ ምዕ. 1 ቍ. 4፦ እግዚአብሔር “ቅዱሳንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን በፊቱ እንድንገኝ ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ መረጠን” የሰው ልጅ የፍጻሜ ጥሪውም ቅዱስ ለመሆን ነው። “ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹሞች ሁኑ፣ (ማቴ. 5. 48)” በማለትም ክርስቶስ ያረጋግጥልናል ብለዋል።
ቤተ ክርስቲያን ከጅማሬዋ አንስታ ቅድስት ናት፣ አባላቷ ግን ፍጹም ቅድስናን ገና የሚያገኙ ይሆናሉ፣ የሚለው ቁጥር 825 ጠቅሰው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በጻፈው ቀዳሜ መልእክቱ 15 ቍ. 28 ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥልጣን ሥር ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር አብ በሁሉ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው ወልድ ራሱ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አደረገለት በእግዚአብሔር አብ ሥልጣን ሥር ይሆናል” በማለት ያቀረቡት አስተምህሮ አጠናቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.