2013-07-17 16:06:33

አመጽና ቀውስ በአገረ ማእከላዊት አፍሪቃ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከባለፈው መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ወዲህ በአገረ ማእከላዊ አፍሪቃ የተቀሰቀሰው ውጥረት አለ መረጋጋት አሁንም እልባት ያጣ ሆኖ አገሪቱና ሕዝቧም ጭምር ጠፍሮ በመያስ በሰላም እጦት ሁነት ባለበት እንዲራመደ እያደረገው መሆኑ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት በኢጣሊያ ሊጉርያ ክፍለ ሃገር በምትገኘው የአረዛኖ የልኡካነ ወንጌል ዋና ገዳም በአገሪቱ ሰላም እንዲረጋገጥ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ያነቃቃው የጸሎት ቀን፣ በናጉዪ የሚገኘው የቀርመሌው ገዳም በመተባበር በመላ ዓለም በሚገኙት በቀርመሌሳውያን ገዳማት ጭምር እግዚአብሔር ለመካከለኛይቱ አፍሪቃ ሰላሙን እንዲለግስ የጸሎት ቀን እንዲሚከበር ተገልጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም አገሪቱ በሰለካ አማጽያን ኃይል ቍጥጥር እጅ ከዋለችበት ዕለት ጀምሮ ያለው ሁኔታ አጅግ አሳሳቢ አመጽ የተሞላው መሆኑ ሲነገር፣ የሰብአዊ ችግር እጅግ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መምጣቱንም በአንቲዳ ቱረት በልኡካነ ወንጌል አገልግሎት ከተሰማሩ 21ኛ ዓመታቸውን ያስቆጠሩት የልኡካነ ወንጌል ደናግል ማኅበረ አባል እናቴ ኤልቪራ ቱቶሎ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.