2013-07-15 16:05:58

ፈረንሳይ፦ ዝኽረ 50ኛ ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ላይ ያተኮረ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. መስከረም ወር በፈረንሳይ ዝክረ 50ኛ ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ላይ ያተኮረ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዙሪያ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ የፈረንሳይ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ሲያመለክት፣ ይኽ እ.ኤ.አ. ከመስከረ 18 ቀን እስከ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በፈረንሳይ ለ ማንስ ሰበካ የሚካሄደው ዓውደ ጥናት ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ለማክበር ያወጁት የእምነት ዓመት ምክንያት በማድረግ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የወጠነው ዓውደ ጥናት መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ሊካሄድ የተወሰነው ዓውደ ጥናቱም ያዘጋጀው የለ ማንስ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ለ ሱዋክስ በሚያሰሙት ንግግር የሚከፈት ሲሆን፣ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ፣ የሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ፣ የፓሪስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲንላ አንድረ ቪንግት ትሮይስ እንደሚሳተፉም የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።
ዓውደ ጥናት ወንጌላዊ ልኡክነት ለማነቃቃት በታይዘ ማኅበረሰብ የሚሰናዳ የጸሎት መርሃ ግብር ያካተተ እንደሚሆን ለማወቅ ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በለ ማንስ ካቴድራል አቢይ እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ውደደ አንድ ልጁን ሰጠ (ዮሐ. 3,16) ወንጌላዊ ቃል የተኖረበት መስቀል እንዲቆም ተደርጎ ሁሉም በመስቀለ ክርስቶስ የዳነ መሆኑ እንዲገነዘብ ለማድረግና በዚህ የእምነት ዓመት መንፈሳውያን ነጋድያን መስቀሉን እንዲጎበኙ የሚጋብዝ መሆኑ ያመለከተው የፈረሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ አክሎ፣ ዓውደ ጥናቱ እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ፓሪስ በሚገኘው በበርናርዲንስ ተቋም በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥበት ሲገለጥ፣ አውደ ጥናቱ ለመከታተልና ስለ አውደ ጥናቱ ማስታወቂያ ለማግኘት www.essentielmans.org ለመጎብኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.