2013-07-15 15:59:30

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ ባለው @Pontifex በተሰየመው የግል አድራሻቸው አማካይነት፦ በዚህ የእምነት ዓመት ዕለት በዕለት ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ የሚረዳን ተጨባጭ ተግባር ለመፈጸም እንጣጣጣር” የሚል መልእክት እንዳስተላለፉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በዚሁ የማኅበራዊ ድረ ገጽ በኩል ሕይወት የፍቅር ውጤት መሆኑ የሚያብራራ “ለአንድ ክርስቲያን ሕይወት አንድ አጋጣሚ ውጤት ሳይሆን የአንድ ግላዊ ጥሪና ፍቅር ውጤት ነው” የሚል መልእክት ማስተላለፋቸው አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.