2013-07-15 16:03:16

ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን ገጠመኝ Pope2you በተሰኘው ድረ ገጽ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ሕዝብን ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው (ማቴ. 28.19)” በሚል ወንጌላዊ ቃል ተመርቶ በብራዚል ሪዮ ደጃነይሮ ከተማ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ገጠመኝ ሁሉ የሚያወሳ በስዕልና በጽሑፍ የተደገፈ የእምነት ገጠመኝ Pope2you በተሰየመው የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሚተዳደረው ድረ ገጽ አማካኝነት እንደሚቀርብና የዚያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መላ ሂደቱና ወጣት ተሳታፊው የሚኖረው ገጠመኝ ለመከታተል እንደሚቻል ምክር ቤቱ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ የዚህ Pope2you የተሰየመው ድረ ገጽ አቀነባባሪ አባ ፓውሎ ፓድሪኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “በዚህ Pope2you በተሰየመው ድረ ገጽ በብራዚል የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መላ ሂደቱን ለመከታተል እንደሚቻልና በተለይ ደግሞ የዚያኑ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የሚያወሳ በድምጽና ምስል የሚቀረጹ መልእክቶች እንደሚተላለፍ ነው ካሉ በኋላ ወጣቱ ትውልድ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው አዲስ የመገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚ በመሆኑም ይኸንን ያለው ብቃት ግምት በመስጠት በተለያየ አገርና ሥፍራ ከሚገኝበት ሆኖ ይኸንን የወጣቶች ቀን እንዲከታተል ለመደገፍ ያለመ መሆኑ አብራርተው፣ የዚያ የወጣቶች ቀን ተሳታፊ ወጣቶች የሚያኖሩት ዜና መዋዕል በቀጥታ የሚተላለፍበት መሆኑ ገልጠዋል።
ገና ከወዲሁ የተለያዩ የተቀረጹ ስዕሎች በዚህ ድረ ገጽ በቅረባቸውንም ገልጠው በዚያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በአካል ለመገኘት የማይችሉ ሁሉ በመንፈስ የሚያሳትፍ እንደሚሆንና ይኸንን ድረ ገጽ በመጠቀም ቅርበቱናን መንፍሳዊ ሱታፌውን ለማረጋገጥ እንደሚችል ነው። ሁሉም ቁምስናዎች በዚሁ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ የማይችሉ ወጣቶች ግምት በመስጠት የሪዮ ደጃነይሮ የወጣቶች ቀን ላይ ያተኮረ አስተምህሮ ያቀርቡ ዘንድ ተስፋ አለኝ በማለት ያካሄዱት ቃል ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.