2013-07-15 16:08:19

ሰነጋል፦ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሱታፌ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 23 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ከተማ በሚካሄደው 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሊሳተፉ ለተመረጡ የሰነጋል ወጣቶች ልኡካን የአገሪቱ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በይፋ መሰጠቱ ሲገለጥ። ከሰነጋል ካቶሊካውያን ወጣቶች በጠቅላላ በአገሪቱ የወጣቶች ጉዳይ ሚኒ. በኖይት ሳምቡ በኮልዳ ሰበካ የሰበካ ተግባር ዋና አስተዳዳሪ አባ አላይን ዳይድሂዩ የተመሩ 20 ወጣቶች መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የሰነጋል መንግሥት እነዚህ ወታቶች ወደ ብራዚል የሚያደርጉት ጉዞ ወጪ ለመሸፈን 37 ሺሕ ኤውሮ መለገሱና ለሰነጋል ተሳታፊ ወጣቶች የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ በይፋ ለማስረከብ በተካሄደው ሥነ ሥርዓ ንግግር ያሰሙት ሚኒ. ሳብሙ፦ መንፈሳዊ ሕንጸት ለወጣት ትውልድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑና በሕዝቦች መካከል ትብብርና መከባበር ብሎም ሰላም ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት አቢይ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑ” እንዳሰመሩበት ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.