2013-07-12 16:18:54

ዓለም አቀፍ የጎብኝዎች መስህብ ቀን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 27 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የመስህብ ቀን፦ “የመስህብ ባህልና የውኃ ሃብት፣ የአካባቢያችን መጻኢነት እንንከባከብ” በሚል ቃል ተመርቶ የሚከበር መሆኑ ሲገለጥ፣ የስደተኞችና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ቀኑን ምክንያት በማድረገ ከወዲሁ መስህብነት የውኃ ሃብት በጠቅላላ ተፈጥሮ መንከባከብ ሃላፊነትና ስነ ምግባራዊ ግዴታ መሆኑ በጥልቀት የሚያብራራ መልእክት ማስተላለፉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“አለ ውኃ ሕይወት አይኖርም” ከሚለው ቅዉም ሃሳብ የተንደረደረ የስደተኞችና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያስተላለፈው መልእክት የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮና የዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ካላታቲፓራምቢል ፊርማ የተኖረበት ሲሆን፣ በዚህ በተላለፈው መልእክት በውኃ ሃብት ላይ በማተኮር ከዓለም ሕዝብ በጠቅላላ አንድ ሦስተኛው በውኃ እጥረት የሚጠቃ መሆኑና ጉዳይ በእንዲህ ከቀጠለ እ.ኤ.አ. በ 2030 ዓ.ም. ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ ብዛት ውስጥ ግማሹን የሚያጠቃ ችግር እንደሚሆና በአሁኑ ወቅት አንድ ሚሊያርድ ሕዝብ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ የሌለው ሲሆን በእውነቱ የውኃ ሃብት የተስተናከለና ፍትሃዊ አጠቃቀም የሚያሻው ከመሆኑም ባሻገር ለሥነ ምኅዳር ባህል ማስፋፋትና አካባቢ ለማክበር የሚያስችል ባህል የማስፋፋቱ ረገድ አይሎ የመስህቦ ባህል በዚህ ክብር ላይ የጸና መሆን ይገባዋል የሚል የማሳሰቢያ ሃሳብ ያካተተ መልእክት መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
የመስህቦ ባህል የአረንጓዴው ኤክኖሚ አክባሪ ሆኖ እንዲስፋፋና ተፈጥሮ ለመንከባከብ የሚያስችለው መመዘኛ የሚኖር እንዲሆንም በተፈጥሮ ሃብት ትክክለኛና ተገቢ አጠቃቃም የተካነ ባህል መሆን እንደሚገባው ጥሪ ያቀረበው ይኽ መልእክት፣ ተፈጥሮ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው በማለት በሊጡርጊያና በውኃ መካከል ያለው ግኑንነት በማብራራት ይኽም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው የፍቅር መግለጫ መልእክት ያሚያበክር፣ ከፋሲካ ዋዜማ እስከ ጥምቀት እንዲሁም ውኃ በወንጌል ባህል መሠረት፣ ኵላዊ ማየ አይኂ፣ የቀይ ባህር መሻገርን ሕጽበተ እግር የመሳሰሉት ጥቅሶች በማካተት ውኃ በቲዮሎጊያ አገላለጥ፣ መንጻት ዳግመ መወለድና የሰቂለአዊ ሕይወትን ምልክት መሆኑ ገልጦ ኢየሱስ ህያው ዘለአለማዊ ምንጭ ውኃ፣ ጥልቅ መሆናዊ ሰብአዊ ጥማት፣ ጥምን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቆርጥ መሆኑ የተብራራበት መልእክት እንደሆነም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
በመጨረሻም መልእክቱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከጠመረጡ በኋላ ጴጥሮሳዊ ተልእኮአቸው በይፍ ለመጀመር እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት የተጠቀሙበት እቃቤ የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ በሚደግሙት ቃል ሲሆን ሆኖም ማቀብ ማለት መቅበር ማለት ሳይሆን በሚገባ ለሰብአዊ ክብር ጥቅም ማዋልና ተፈጥሮና ተጠቃሚው ፍጡር የሚያክበር የሚንከባከብ ማለት መሆኑ የስደተኞችና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ባስተላለፈው መልእክት በማብራራት፣ ተፈጥሮን መንከባከ የሰው ዘር ጥሪያዊ ኃላፊነት ነው በሚል ሃሳብ መልእክቱን ማጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስትታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.