2013-07-10 15:19:59

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮዋልዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ባቀረቡት 34ኛው ክፍለ አስተምህሮ፦ አንዲት ቅድስት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን” የሚል በተአምኖተ እምነት ክፍለ አንቀጽ ላይ በማተኮር፦ ተአምኖተ እምነት ስንደግም ቤተ ክርስቲያን አንዲት ቅድስትና ሐዋርያዊት መሆንዋ እንናዘዛለን፣ የክቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 811 “…ይኽ የምንመሰክርላት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ይችን ናት…እነዚህ የማይነጣጠሉና በእርስ በርሳችው የተያያዙ አራት ባህርያት አቋማንና ተልዕኮዋን የሚያመለክቱ ናቸው፣ ቤተ ክርስቲያን ከራሷ ያፈለቀቻቸው ባሕርያት አይደሉም፣ ክርስቶስ ነው። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አንዲት ቅድስት ካቶሊካዊትና ሐዋርያዊት ያደረጋት እነዚህም ባሕርያት እያንዳንዳቸው እውን እንድታደርግ የጠራትም እርሱ ነው” በማለት በማያሻመ መልኩ አብራርተዋል።
ቤተ ክርስቲያን አንድ የሚያደርጋትም አናስርዋ ነው። ይኽም በምንጭዋ ምክንያት ሲሆን “…በመሥራችዋ ምክንያት አንዲት ናት፣ ‘ሥጋ የሆነው ቃል የሰላሙ ልዑል የአንድ ሕዝብና አንድ አካል አንድነትን በማስፈን በመስቀሉ ሰዎችን ሁሉ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አስታርቀዋል’ ቍ.813።”፣ በቍ. 815 የአንድነቱ መስተሳስር ለይቶ ይገልጥልናል፦ “…ከዚህ ሁሉ በላይ ሁሉንም አስሮ ፍጹም አንድነትን የሚያስገኘውን ፍቅርን ልበሱ” የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ መስተሳስሮቹ አንድ እምነት የሚል ኑዛዜ፣ በሁባሬ የሚከበሩት ቅዱሳት ምስጢራት፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ወንድማዊ መግባባትና የደቀመዛሙርት ተከታይነት ወይንም ተተኪነት እርሱም ምስጢረ ክህነት የተሰኙት የሱታፌ መስተሳስሮች መሆናቸው ያመለክትልናል። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ብቸኛዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና (ውሳኔ ብርሃን አሕዛብ ቍ.8 ተመልከት) በሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት ሱታፌና አንድነት በምትተዳደር በካቶልካዊት ቤተ ክርስቲያን የጸና መሆኑ እንደሚያረጋግጠውም አባ ኮውላዝይክ አብራርተውዋ።
እውነቱ ይኽ ሆኖ እያለ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ብዙ የመከፋፈል አደጋ አጋጥሟታል፣ በቤተ ክርስቲያን የተከስተው መከፋፈል በክርስቲያን ምእመናን መካከልም የመከፋፈል አደጋ አስከትሎ ይኸውም ካቶሊካውያን ኦርቶዶክሳውያን ሉተራውያን የሚል አገላለጥ ያለው መሆኑ አባ ኮዋልዝይክ ገልጠው፣ የካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 819 አንድነትን ማስፈን በሚል ንኡስ ርእስ ሥር፦ …ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ ዘወትር የአንድነት ስጦታን ይሰጣታል፣ ነገር ግን ክርስቶስ የፈቀደላትን ለመጠበቅ ለማጠናከር ፍጹም ለማድረግ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር መጸለይና መሥራት አለባት፣….ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ ሲል የጸለየው የክርስቶስ መንፈስ…ለድኅነት መሣሪያ የሚገለገልባት ቤተ ክርስቲያንና የሚገለገልበት ማኅበረ ክርስቲያን…” በማለት ይገልጥልናል፣ ስለዚህ የነዚህ የድህነት መሣሪያ ኃይል ክርስቶስ ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ከሚሰጠው ጸጋ ሙላት የሚመነጭ መሆኑ በዚሁ ቍ. 819 ተመልክቶ ይገኛል ካሉ በኋላ አክለው የገዛ እራስ መለያ ሳታዳክም የጠፋውን አድነት እንዴት ዳግም ለመፈለግ ይቻላል? ሙሉ አንድነት ወደ አብ አንድ እንዲሆኑ በማለት የሚጸልየው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ነው። አንድ መሆን ማለት የተለያዩ ማኅበረ ክርስቲያን የሚያሰባስብ ትልቅ ማኅበር ማለት አይደለም፣ ስለዚህ ወደ ተዛማጅ ባህል የሚያዘልቀው ርእዮተ ዓለም የሚያስገኘው ሳይሆን በእያንዳንዱ ክርስቲያን ልብ መለወጥ ላይ ያለ መሆኑ ገልጠው ያቀረቡትን አስተምህሮ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.