2013-07-10 15:14:50

የላምፐዱዛ ከንቲባ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የላምፐዱዛ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሜዲትራኒያን የባህር ክልል የሚከሰተው አሰቃቂው ፍጻሜ ያለው የሰብአዊ አደጋ በዝምታ የመመልከቱ ልማድ የሚቀድ ተግባር ነው


RealAudioMP3 የሚከሰተው አሰቃቂው ፍጻሜ ያለው የሰብአዊ አደጋ በዝምታ የመመልከቱ ልማድ የሚቀድ ተግባር ነው
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ላምፐዱዛ የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ በደሴቲቱ የሚገኘው ነዋሪው ሕዝብ እዛው የሚገኙት ስደተኞች የክልሉ ምክር ቤት አባላት የተሳተፉበት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ የሜዲትራኒያን የባህር ክልል ከተለያየ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ኤክኖሚያዊ ችግር ገዛ እራሳቸውን ለማዳን ቤተ ሰቦቻቸውን ለመርዳት ዓልመው በተለያዩ ተናንሽ ባለ ሞተር ጀልባዎች በማቋረጥ ወደ ኤውሮጳ በኢጣሊያ የላምፐዱዛ የባህልር በር በኩል የሚገቡት ስደተኞች በዚህ ጉዞ በሚያጋጥማቸው የባህር አደጋ ሳቢያ እዛው በመዲትራኒያን የባህር ክልል ሰጥመው የሚቀሩት ሁሉ በማሰብ፣ እነዚህ ዜጎች በዝምታና በቸልተኝነት የመመልከቱ ልማድ ዓለማዊነት ትስስር ያለው ቸልተኝነት” በማለት እንደገለጡት የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው የስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ ብርቱ ቃላት በመጠቀም የሰነዘሩት ማሳሰቢያና ምክር፦ “በሜዲትራኒያን የባህር ክልል የሚከሰተው አሰቃቂው ፍጻሜ ያለው የሰብአዊ አደጋ በዝምታ የመመልከቱ ልማድ የሚቀድ ተግባር ነው” በማለት የላምፐዱዛ ከተማ ከንቲባ ጁሲ ኒኮሊኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ ገልጠው፦ በሕይወቴ አንድ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ ቀርቤ ስመለከትና ስገናኝ ባለኝ የከተማይቱ የከንትባነት ኃላፊነትም ቅዱስነታቸውን ተቀብየ ከጎናቸው ሆኜ ስወያይ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፣ ስለዚህ ጥልቅ ደስ የሚያሰኝ ስሜት ነው፣ በተለይ ደግሞ የደሴቲቱ ነዋሪ ሕዝብ በባህር ጉዞ ተሰደው ላምፐዲዛ ደሴት የሚገቡትን በመቀበል በማስተናገድ የሚሰጠው ሰብአዊ ድጋፍ ቅዱስነታቸው ያደንቁት ብቻ ሳይሆን መስተንግዶ አለ ምንም ልዩነት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ገልጠው ላምፐዱዛ የኤውሮጳና የሜዲትራኒያን ማእከል መሆንዋ የሰጡት ሃሳብ እውነት ነው፣ አለ ምንም ማመንታት በመዲትራኒያን የባህር ክልል የሚከሰተው ሰብአዊ ጉዳይ በመተንተን ያሰሙት ንግግር ቸልተኝነት ጥላቻ ስግብግብነት የሚቃወምና የዚህ አይነቱ ኢሰብአዊ ባህርይ ሰበብ ቀላል እንዳልሆነና እንደማይሆንም ነው ያሳሰቡት” ብለዋል።
ማንም ለኅትመት አብቅቶ ለማሰራጨት ያልደፈረው እጅግ የሚያስደነግጥ ሰብአዊ ሁነት የሚያወሳው በዚህ የባህር ጉዞ አማካኝነት ላምፐዱዛ እንደገቡ የነዚህ ስደተኞች ሁኔታ ምስል የሚገልጥ፣ ባህር የሚተፋው የብዙ ስደተኞች ሙት አካል አካቶ የተነሳ ምስል አዘል መጽሓፍ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መለገሳቸው ከንቲባ ኒኮሊኒ ገልጠው፣ ይኽ ዓይነቱ በተነሳ ስእል አማካኝነት የስደተኞች ጉዳይ እውነተኛ የሕይወት ገጠመኝ ለማሳተም ያስገደደውም ማንም ቀርቦ ሊያየው የማይፈልገው ሐቀኛው ሰብአዊ ክስተት ቅርብና ሩቅ ላለው ለማሳወቅና ጉዳይ መፍትሔ እንዲያገኝ የዓለም ማኅበረሰብ ቀልብ ለመሳብ መሆኑም አብራርተዋል።
የደሴቲቱ ነዋሪ ሕዝብ ከዚህ ቀደም የሚሰጠው ሰብአዊ አገልግሎት በቅዱስ አባታችን መሪ ቃልና ምዕዳን አማካኝነት በበለጠ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ በማረጋገጥ፣ የሰውን ልጅ ቤቱንና ልብረቱን ጥሎ ለስደት የሚዳርገው ችግር መፍትሔ ማፈላለግ የሁሉም ኃላፊነት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.