2013-07-08 16:14:01

ቅዱስ አባታችን፦ በሐዋርያነት ጥሪ ከወንጌል ጋር የተጋጠመና የሚጣጣም ሕይወት መኖር


RealAudioMP3 በዚህ እየተኖረ ባለው የእምነት ዓመት ምክንያት ባለፈው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከመላ ዓለም የተወጣጡት የዘርአ ክህነት፣ የመንፈሳዊ ማህበራት፣ የደናግል ማኅበራት ተማሪዎች እንዲሁም ተመካሪያን አገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የተካሄደው ጉባኤ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ አስታወቁ።
“ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ለተመለከተው መንገድ ታማኝ ለመሆን በምታደረገው ጉዞ አስተዋጽኦ አበርክቱ” በተሰኘ ሃሳብ ማእከል በማድረግ ባቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፦ “ያጋጣሚና የጊዚያዊነት ባህል፣ ጽናት የሌለው በአጋጣሚ የሚኮን፣ አመክንዮ የሌለው ግዚያዊነት ባህል እጅግ አደገኛ ነው። ቀን በቀን ይኽ ባህል ያሳድደናል፣ አንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ እንዳንኖር የሚገፋፋ አቢይ ችግር ነው። በእኔ የወጣትነት ጊዜ ሁሉ የተሻለ ነበር ለማለት እችላልሁ፣ ይኽም የነበረው ባህል ለክህንት ለገዳማዊ ጥሪ አቢይ ድጋፍ ነበር። በአሁኑ ወቅት ቁርጥ ያለ ውሳኔ መኖር አቢይ ችግር ሆኗል። የጊዚያዊነት ባህል ሰለባዎች ነን” እንዳሉ ካፐሊ ገለጡ።
“እንተ ለእኔ አስፈላጊ ነህ፣ በቃል ብቻ ሳይሆን በሕይወትም ጭምር የሚባል ቃል እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ያለው በተለያየ መልኩ የሚገልጠው ቃል ነው። እግዚአብሔር ለሚጠራቸው እወድሃለሁኝ እተማመንብሃለሁኝ ይላል፣ ስለዚህ ይህ እርሱ የሚለው ቃል የማዳመጡ ምሥጢር ነው ደስታችን፣ የተፈቀርክ መሆንህ፣ ለእርሱ ሰዎች እንጂ አኃዝ እይደለንም፣ እርሱ ሲጠራን ማዳመጥ፣ ካህን ገዳማዊ መናኝ መሆን የእኛ ምርጫ ሳይሆን ለሚጠራው የእግዚአብሔር ፍቅር የሚሰጥ መልስ ነው። መልስ እንጂ ምርጫ አይደለም” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ አክለውም፦ እናንተ የዘርአ ክህነት የገዳማት የመናንያን ማኅበር ተማሪዎች ተመካርያን ፍቅራችሁ ለኢየሱስ ፍቅር ሰዉ፣ ልብ ለኢየሱስ ከመስጠት የሚኖር የንጽህና ህይወት ቃለ መሓላ ሲፈጸም የሚኖር ሳይሆን ዕለት በዕለት በቀጣይነት የሚኖር ነው። አንድ ካህን የእርሱ ማኅበርሰብ አባል ብቻ ሲሆን፣ እጅግ ያሳዝናል፣ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት የሚያጋጥም ትካዜ መንስኤውም አባትነት ወይንም እናትነት መንፈስ አዛብቶ ከመኖር የሚመነጭ ነው። ስለዚህ አንድ ካህን ወይንም አንዲት ድንግል ፍርያማ እንጂ መሀን አይደለም፣ ይኽንን የማይገነዘብ ካቶሊክ ካቶሊክ ሊባል አይችልም፣ ሁሉም በተጠራበት ጥሪ ፍርያማ መህን ያስፈልጋል፣ ስለዚህ የሚሰዋ ሕይወት ውበት ፍርያማ መሆኑ ነው ትርጉም” እንዳሉ ገልጠዋል።
“እንድንዴ እኛ ካህናትና ደናግል የምናንጸባርቀው እውነተኛ ያልሆነ የተዛባ ሕይወት ስታዩ ያስጠላችኋላ ለዚህም ነው እውነተኛ ምስክርነት አስፈላጊ ነው የሚባለው። በጥሪያችሁ ሕንጸት ጎዳና የሚሰጣችሁ አራት የሕንጸት መንፈሳውያን አዕማዶች አሉ፣ መንፈሳዊ ሕንጸት፣ ሥነ ባህላዊ ሕንጸት፣ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሕንጸት፣ ሕንጸት ለማኅበራዊ ሕይወት፣ የተሰኙ ናቸው፣ በእነዚህ እራት ሕንጸቶች መታነጽ ይኖርባችኋል። በእውነቱ ብዙውን ጊዜ በሐሜትና በአሉ ባልተኝነት ተግባር ጊዚያችንን እናባክናል፣ ይኽ ለሁላችን የሚጋጥም ፈተና ነው። ብዙውን ጊዜ ሁላችን በዚህ ፈተና ተጠቅተናል፣ ለወንድማችን ለእህታችን የሚባል ካለን ፊት ለፊት የማለቱና የመናገሩ ብርታት ሊኖረን ይገባል እንጂ ከሌላ ጋር ሆኖ ማማት እንቅፋት ነው። ፊት ለፊት መናገር ስለዚህ ወድማችንንና እህታችንን ያበረታል ያግዛል፣ ስለዚህ ስም ከምጥፋት ከማጉደፍ እንቆጠብ” እንዳሉ የገለጡት ካፐሊ አያይዘውም፦ ኢየሱስ በመረጠው መንገድ ለምትጓዘው ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ አበርክቱ፣ የማጉረምረም ጸባይ አይኑራችሁ። ማጉረምረም ለገዛ እራሱ ጣዖት ነው። ስለዚህ ይኸንን ጣዖት ከማምለክ እንቆጠብ አወንታዊ እሳቤ ይኑራችሁ፣ መንፈሳዊ ሕይወት ገንቡ፣ ከሁሉም ጋር በተለይ ደግሞ ከተናቁት ከተገለሉት፣ በተጎሳቆለ ሕይወት ከሚኖሩት ጋር ለመገናኘት ንቁ። ወደዚህ የሕብረተሰብ ክፍል ለመሄድ አትፍሩ፣ ከገዛ እራስ ወጥቶ መጓዝ ሊያስፈራችሁ አይገባም። አስተንታኞችና ልኡካን ሁኑ፣ ቅድስት ማርያም ትደግፋችኋለጽ፣ የመቁጸሪያ ጸሎት ቀን በቀን አዘውትሩ፣ ማርያምን ዘወትር ልክ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ እንዳደረገው በሕይወታችሁና በቤታችህ እርሷን ቅድስት እናት አኑሩ፣ እርሷ ትሸኛችኋለች ትጠብቃችኋለችም፣ ስለ እኔ ጸልዩ ምስኪን ሐጢአተኛም ነኝና ስለ እኔም ጸልዩ አደራ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ካፐሊ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.