2013-07-08 16:17:36

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የደሴት ትሪኒዳድና ቶቦጋ ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአገረ ቫቲካን የትሪኒዳድና ቶቦጋ ደሴት ርእሰ ብሔር አንቶንይ ቶማስ አኵይናስ ካሮናን ተቀብለ ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
በተካሄደው ግኑኝነትም ቤተ ክርስቲያን በአገረ ትሪኒዳድና ቶባጎ በሕንጸት በጤና ጥበቃ አግልግሎት በድኽነት ለተጠቁት የአገሪቱ ዜጎች የምትሰጠው ድጋፍ ላይ ባተኮረ ርእስ ሥር ውይይት መካሄዱ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፣ ቤተ ክርስቲያን በዚያች አገርች ለወጣቶች በሚደረገው ሕንጸት ወጣቱ ከተለያዩ የወንጀል ቡድኖች ወጥመድ ለማላቀቅ በወንጀል ተግባር እንዳይሰማሩ፣ ለቤተሰብ ለሁሉ ሰው ለተሟላ ሰብአዊ ሕንጸት በሚደረገው ጥረት ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አስተዋጽኦ የጎላ እውቅና የሰጠ ግኑኝነት ከመሆኑም ባሻገር በዚሁ ዘርፍ የቤት ክርስቲያን አስተዋጽኦ ቀዳሜና ወሳኝ መሆኑ እንደተሰመረበትም አስታውቀዋል።
በመጨረሻም የትሪኒዳድና ቶቦጋ ደሴት ርእሰ ብሔር ለቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. የዚያችን ካሪቢያን አገር ልዩ ከብረት የተሰራ ከበሮ ገጸ በረከት እንዳቀረቡላቸው የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመልክቶ፣ ርእሰ ብሔሩ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተሰናብተው ከቅድስት መንበር የውጭ ጉኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ጋር መገናኘታቸው አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.