2013-07-05 16:08:19

ቡዳፐስት፦ የኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ


RealAudioMP3 የኤውሮጳ አገሮች የብፅዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ምክር ቤት ሊቀ መንበር የቡዳፐስት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፐትሮ ኤርዶ ትላትናን በቡዳፐስት ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ መክፈቻ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፦ የኤውሮጳ ሃገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ይኸንን የኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት ጉባኤ በአቢይና በልዩ ፍላጎት የሚመለከተው መሆኑ በማረጋገጥ፣ በዓለም የክርስቶስ ህላዌ መስካሪያን የአቢያተ ክርስቲያን የበላይ መዋቅሮች ሳይሆኑ መላ የመላ አቢያተ ክርስቲያን ምእመናን በሚሰጡት ምስክርነት የሚገለጥ ነው ካሉ በኃላ የአቢያተ ክርስቲያን መዋቅሮች ለወንጌል አገልግሎት የሚል የጸኑ እሴቶች ወክለው የእነዚያ የክርስቶስ ተከታዮችና የእርሱ ፈቃድ ለሚከተሉት ሁሉ የአቢያተ ክርስቲያን ሙሉና ተጨባጭ ውህደት ለሚጠባበቁት ሁሉ ለጋራው ጥቅም ድጋፍ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
የብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ መልእክት ክርስቶስ የተስፋና የአንድነት ምንጭ መሆኑ ላይ ያነጣጠረ እንደነበርም የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ በምስራቅ ኤውሮጳ አገሮች የነበረው ሥርዓት ለማግለል ያነቃቃው የነጻነት ፍላጎትና አንድ ኅብረተሰብ የሚገነባው በጽሑፍ ከሠፈረው ጠባብ ርእዮተ ዓለም ላይ ሳይሆን በእውነት ሙላት ላይ ካለው ግንዛቤ የመነጨ መሆኑ ብፁዑነታቸ አስታውሰው፣ ስለ እውነትና ስለ ነጻነት በተመለከተ የተገባው ቃል ሊጨበጡ እንደማይቻሉም የሁሉም አገሮችና ሕዝቦች ገጠመኝ ነው፣ ቤተ ክርስቲያን በኤውሮጳ በሚል ርእስ ሥር የተደረሰው ሐዋርያዊ ምዕዳን በእኛ ውስጥና በመካከላች የክርስቶስ ተስፋ በላቀ ደረጃ እንዲነቃቃ የሚያበረታታ መሆኑ እንዳሰመሩት አስታውቀዋል።
ይኽ ጉባኤ ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሃፊ መጋቤ ኦላቭ ትቫይት በተለያዩ አቢይተ ክርስቲያን መካከል ለሚደረገው የውህደት ጥረት በጋራ ለማክበር አጋጣሚ መሆኑ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር ጠቅሰው፣ ለውህደት የሚደረገው ጥረት እያስጨበጠው ካለው ፍሬ እጅግ የላቀው ፍሬ ውህደት መሆኑ የሚያመለክት ጥረት ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።
የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛ አቢያተ ክርስቲያን በኤውሮጳ እጅግ ለዘርፈ ብዙ ቀውስና የብዙ ክስተቶች ምክንያት የሆነው ለውጥ በስፋት በሚረጋገጥበት ክልል ለሚኖረው ለማኅበርሰብ ጥልቅ ፍላጎት ምላሽ ሊሰጥ በሚችለው አገልግሎት ቀርቦ ማገልገል በሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት፦ በዚህ በምንኖርበት ኅብረተሰብ የክርስቶስ ነጸብራቅ ሆኖ መገኘት ያለው አስፍፈላጊነት በማስመር ይኽ እ.ኤ.አ. እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚዘልቀው ጉባኤ በዓለምና በኤውሮጳ የተከሰቱት ወቅታዊ ለውጦች ግምት የሰጠ ይኽ እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም. የተመሠረተው የኤውሮጳ የአቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ ቅርጽ ኅዳሴ ፈር ያስይዝ ዘንድ አደራ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.