2013-07-03 15:43:31

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ትላንትና “ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ሥራና ያላት ሁሉ ጸጋዎችም ከእግዚአብሔር አሳቢነት የተለገሰች ነች” በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ ባቀረቡት 33ኛው ክፍለ አስተምህሮ ስለ ቤተ ክርስቲያን በማስመልከት፦ በቤተ ክርስቲያን አምናለሁኝ በማለት ተአምኖተ ሃይማኖት እንደግማለን፣ ሆኖም ይህ ኑዛዜ ምን ማለት ነው? የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ እንደሚያመለክተውም ቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ማደናገር እንደማያስፈልግ በቁጥር 750 ይገልጥልናል፣ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ሥራ ነች፣ በጠቅላላ የተቀበለቸው ጸጋ (ቃል ቅዱሳት ምሥጢራት ማኅበረሰብ…) የእግዚአብሔር አሳቢነትና መልካምነት የሰጣት ጸጋ ነው” ብለዋል።
“ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ብርሃን ውጭ ሌላ ብርሃን የላትም ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል በስተቀረ ሌላ ኃይል የላትም፣ ይኽ ሲባል ከአንድ ቤተ ክርስቲያናዊ ተቋም ማኅበርና መስተዳድር ውጭ የፈለግነውን እናደርጋለን ማለት አይደለም፣ ምንም’ኳ ቅድስት ሥላሴ ለመወሰ የማይቻልና በማንኛውም ዓይነት ተቋም ለመወሰን ባይቻልም፣ የተሰገወው እግዚአብሔር በሰዎችና በቤተ ክርስቲያን ተቋማት አማካኝነት የሚሠራው ነው” ሲሉ አብራርተዋል።
“ቤተ ክርስቲያን የሚል ቃል ትርጉሙ ጉባኤ (የተጠራ ጉባኤ) ማለት ነው፣ ሆኖም ጥሪው የአንድ ብቸኛው የሰብአዊ አይነት ማኅበር አባል እንድትሆን የሚጋብዝ ማለት ሳይሆን የሕዝበ እግዚአብሔር አባል ለመሆን መጠራትን የሚያመለክት ነው። ስለዚህ ጠሪው እግዚአብሔር ጉባኤውም የእግዚአብሔር አብ ነው። በሥጋዊ ትውልድ ሳይሆን በውኃና በመንፈስ ተወልዶ አባል የሚከወንበት ማለትም በክርስቶስ በማመንና በመጠመቅ አባል የሚከወንበት ማለት ነው” (ቁ. 782 ተመልከት) ብለዋል።
አባ ኮዋልዝዪክ በመቀጠል ይላሉ፦ “የቤተ ክርስቲያን መሠረት ያኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አዲስ ቃል እያበሰረ ደቀ መዛሙርት በመጥራት፣ ምሥጢረ ጥምቀትና ቅዱስ ቁርባን በማቆም ያጸናትም ነች፣ ይኽ ተግባር በክርስቶስ ስቃይና ትንሣኤ ላይ የሚጸናም ነው። ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የመሠረተ ብቻ ሳይሆን እርሱ እራስ የሆነባት ምሥጢራዊ አካል ነች፣ ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ (መቅደስ) ተብላም ትገለጣለች፣ ‘መንፈስ ቅዱስ የምሥጢራዊው አካል ነፍስ የሕይወቱ በልዩነቱ ውስጥ ላለው አንድነቱ የስጦታዎቹምና የተሰጥኦዎቹም ጭምር ስፋት ነው’ (ቍ. 809 ተመልከት)።
ተጨባጭ ለሆነቸው ቤተ ክርስቲያን እራስ “…እኔ እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፣ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክስቲያኔን እሠራለሁ፣ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም’ የመንግሥተ ሰማያትን በክፈቻ እሰጥሃለሁ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰምያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ. 16፣ 15-19) በተሰኙት ቃለ ኢየሱስ የተመረጡት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በምድር የክርስቶስ ኅየንተ መሆናቸው አብራርተው ያቀረቡት አስተምህሮ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.