2013-06-26 16:00:19

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ትላንትና ባቀረቡት 32ኛው ክፍለ አስተምህሮ፦ መንፈስ ቅዱስ አካል በሁሉም አካላት ውስጥ” የሚል ያልታወቀው አምላክ ማንነት መግለጫ መሆኑ በማስታወስ፣ የካቲሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ፦ “ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ያምናሉ፦ ‘በመንፈስ ቅዱስ ማመን መንፈስ ቅዱስ ከቅዱስት ሥላሴ አካላት ውስጥ አንዱ መሆኑና ከአብና ከወልድ ጋር አንድ ኅልውና ያለው መሆኑን ማመን ነው’ (ቍ. 685)” በሌላ አነጋገር መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ጋር ብቸኛ እግዚአብሔር ነው፣ ቅዱስ ጵውሎስ ለቆሮንጦስ በጻፋት ቀዳሜ መልእክቱ ምዕ. 12 ቍ. 3 “በመንፈስ ቅዱስ ተግባር ካልሆነ በስተቀረ ማንም ኢየሱስ ጌታ ነው ለማለት አይቻለውም” በእኛ ውስጥ ላለው መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁነውና እግዚአብሔርን አባታችን ብለን ለመጸለይ የሚቻለን ሆነናል (ገላ. 4,5 ተመልከት)።
እግዚአብሔር አብ በቅዱሳት መጻሕፍት በተለያየ ምስል ይገለጣል ለምሳሌ ነቢይ ኢሳያስ ምዕ. 6, 1 በዙፋን ላይ የተቀመጠ ጌታ ሲል ይገልጠዋል ሆኖም የቅድስት ሥላሴ ሁለተኛው አካል ገዛ እራሱን በኢየሱስ ክርስቶስ መልክ ተገልጦልናል፣ ታዲያ የመንፈስ ቅዱስ ግልጸተ መልኩ ምን ይሆን? በቅዱሳት መጻሕፍት የምናገኘው የመንፈስ ቅዱስ ግልጸተ መልኩ አለ ሰብአዊ አካል ነው። ይኽም በእርግብ በነፋስ በእሳት አምሳያ ነው የሚገለጠው፣ ሆኖም ይህ የመንፈስ ቅዱስ አምሳያ ግልጸት ልክ ሰብአዊ አካል ሳይሆን እንደ አንድ መለኮታዊ ኃይል ሆኖ ነው የሚገለጠው። ይኽ ዓይነቱ የአምሳያ አገላለጥም የመንፈስ ቅዱስ ሰብአዊነት ባህርይ ነው የሚገለጸው።
በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በአንደኛ የባለቤት አካል እኔ በሚል አገላለጥ አይናገረንም፣ ስለ ገዛ እራሱ የማይነጋረ ገዛ እራሱን የማይቀስር ነው። በቀጥተኛ መንገድ መልከ አምሳያውን አይገልጥም። በአብና በወልድ መካከል ያለው ፍቅር የሆነው ሦስተኛው አካል ነው። ለገዛ እራሱ ሳይሆን ሰርገይ ቡልጋኮቭ እንደሚለውም ሁለመናው በሌሎች ውስጥ ይኽም በአብና በወልድ መካከል ነው ብለዋል።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥም መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ውስጥ ይሠራል። በብዙ ሰዎች ውስጥ ያለ አካል ነው። ነፋስን አናየውም ሆኖም ግን ነፋሱ የሚፈጥረውን እንቅስቃሴ እናያለን፣ የመንፈስ ቅዱስ ቀዳሜ ምክንያት ፍቅር ነው። የመንፈስ ቅዱስ አካላዊ መልክ የፍቅር ውጤት የሆነው ፍሬ ይዞ በሚጓዘው ማኅበረሰብ ዘንድ ነው። በሰዎች መካከል ሱታፌ በመፍጠር ይገለጣል ሲሉ ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.