2013-06-26 15:58:02

በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቃልና ተግባር የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ለተለያየ አደጋ ለሚጋለጡት ለቀደምት ተወላጅ በላቲን አመሪካ


RealAudioMP3 በፐሩ በምትገኘው በአረኪፓ ከተማ ጳጳሳዊ የውሁድ ልብ ምክር ቤት ማኅበር የሆነው በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ መልካም ፈቃድና ውሳኔ መሠረት የተቋቋመው Populorum Progressio-የአሕዛብ እድገት ምክር ቤት አዘጋጅነት ስለ ላቲን አመሪካ ቀደምት የአገር ተወላጆችና የአፍሮ ላቲን አመሪካውያን ጉዳይ ማእከል አድርጎ የተካሄደው የዚሁ መሥተዳድር ምክር ቤት ዓመታዊ ጠቅላይ ጉባኤ ትላንትና መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ የተካሄደው ጉባኤ ለቀደምት የላቲን አመሪካ ተወላጆችና የክፍለ ዓለሟ አፍሮ ላቲን አመሪካውያን እርባና 170 የተለያዩ እቅዶች መወጠኑ ለማወቅ ሲቻል በተካሄደው ጉባኤ ጳጳሳዊ የውሁድ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራሕና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ተኻዶ ሙኞዝ መሳተፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ አቡነ ተኻዶ ሙኞዝ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተወጠኑት እቅዶች የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃልና ተግባር የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ለተለያየ አደጋ ለሚጋለጡት ለቀደምት ተወላጆችና ለአፍሮ ላቲን አመሪካውያን በላቲን አመሪካ የሚመሰክሩ መሆኑ ገልጠው፣ ሊወጠኑ ከታለሙት 200 ውስጥ በገንዘብ እጥረት ምክንያት 170 ብቻ ምክር ቤት እንዳጸደቀው ጠቅሰው፣ እቅዶቹ በምንም ተአመር መንፈሳዊና ሰብአዊ ሰብአዊ የማይዘነጋ መሆኑ ካብራሩ በኋላ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እግዚአብሔር ፍቅር ነው በተሰየመው አዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት የሰው ልጅ አቢይ ስቃይ እግዚአብሔር መዘንጋትትና የእግዚአብሔር ህላዌ መርሳት ነው በማለት የገለጡት ሃሳብ Populorum Progressio-የአሕዛብ እድገት ምክር ቤት በልቡ ውስጥ ያሰፈረው መሪ ቃል ነው። ስለዚህ የሚወጠነው የግብረ ሠናይ እቅድ ያንን መሪ ቃል መሠረት በማድረግ ተወጥኖ የሚተገበር ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ አዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.