2013-06-21 16:01:33

ብፁዕ አቡነ ቹሊካት፦ሥራ አጥነት ማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት ነጻነትን ለአደጋ ያጋልጣል


RealAudioMP3 ከትላትና በስትያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ግቦች ርእስ ሥር በተወያየው የጠቅላይ ጉባኤ አራተኛው መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት በዚሁ ዓለም አቀፍ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፍርንሲስ ኩሊካት፦ በዓለም ከ 250 ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ይክም ትምህርት ከማግኘት ሰብአዊ መብት ተገለው ይኽ መብት ተነፍጓቸው ሲኖሩ በእውነቱ ለመንግሥታት ለዓለም አቀፍ መሪዎች ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አቢይ ሃፍረት ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ “ወቅታዊው ለከፋ አሰቃቂ ችግር የሚያጋልጠው እየተስፋፋ ያለው ሥራ አጥነት ነው። ከዚህ ይባስም ሥራ አጥነት ለተለያዩ አዳዲስ የባርነት ሥርዓት እያጋለጠ ነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት 400 ሚሊዮን ሰራተኞች በከፋ ድኽነት ሥር ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሚገምቱ ሕፃናት የጨቅላነት እድሜያቸ ተነፍጎባቸው ለሥራ ተዳርገው ለተለያየ ባርነት ጫንቃ ተዳርገው ሌሎች በብዙ ሚሊዮን የሚገመቱም በኢንዳስትሪ የበለጸጉ አገሮች ኑሮና ምቾት ለማርካት የኑሮ ደረጃ በበለጠ አርኪ ለማድረግ በሚጠመደው ሥራ ተዳርገው አለ የሠራተኛ መብትና ክብር ጥበቃ የሚኖሩ መሆናቸው ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ቹሊካት የእደ ጥበብ ምንጣቄና የሰው ልጅ ለአዳዲስ ባርነት ያማጋለጡ ሁነት እንዴት ተያይዘው ሊሄዱ ይችላሉ፣ የበለጸገ ዓለም ብልጽግናው በሁሉም ዘርፍ መሆን እንደሚገባው ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ይኽ በዓለም የሚታየው ጸረ ሰብአዊ ተግባር በመኮነን የዓለም ፖለቲካ መንግሥታት ሁሉ የሠራተኛ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ብሎም ከሰው ልጅ ክብርና መብት ጋር የሚስተካከል ሥራ መፍጠር ይተጉ ዘንድ አደራ በማለት እንዳሳሰቡ አስታውቀዋል። ሥራ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብት ነው፣ ብሎም ቤተ ሰብ ለመመሥረት ሁነት የሚፈጥር ተግባር ነው። ስለዚህ ሥራ አጥነት፣ ብዝበዛ አልድልዎ የሰው ልጅ ከዚህ ሁሉ ክብር የሚያገል ብቻ ሳይሆን ሊገመትና ሊታሰብ ወደ ማይቻለው አስከፊ ተግባር የሚዳርግም ነው። ከዚህ አንጻር ሥራ ለሰው ልጅ ያለው አቢይ ሥፍራ ለመገመቱ እያዳግትም” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ የሁሉም በጠቅላላ የሰው ልጅ ትምህርት የማግኘት ሰብአዊ መብቱ ጥበቃና አክብሮት ማረጋገጥ ከሚለው ተግባር የሚጀምር ነው። አለ ትምህርት የማግኘት መብት ትግባሬ የዛሬው ታዳጊ ወጣት የነገው ጎልማሳ ለመሆን ቢችልም በተራቀቀው በተለያየ መልኩ እየተለዋወጠ በመሄድ ላይ ባለው የሥራ ፖለቲካ ገዛ እራሱ ከማሳተፍ መብት ተገሎ እንዲኖር ያስገድደዋል፣ ስለዚህ የኅብረተሰብ መሠረት የሆነው ቤተሰብ በመደገፍ የቤተሰብ ሚና በዓለም ማነቃቃትና ማበረታታት ለተስተካከለ የልማት ዕቅድ አቢይ ድጋፍ ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.