2013-06-19 15:32:45

ጀነቭ፦ የካቶሊካዊትና የሉተራናዊት አቢያተ ክርስቲያን የጋራ የውይይት ሰነድ
ከግጭት ወደ ሱታፌ


RealAudioMP3 የነበረው ጥንታዊው ውህደት ዳግም ለማረጋገጥ ከግጭት ወደ ሱታፌ ለመጓዝ እንዲቻል ልዩነት ያመጣው ትውስት የሆነው ቁስል መፈወስ ያለው አስፈላጊነት ላይ ያነጣጠረ የካቶሊካዊትና የሉተራን አቢያተ ክርስቲያን የጋራው የውውይይት ድርገት “ከግጭት ወደ ሱታፌ” በሚል ርእስ ሥር የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የጋርው ድርገት በጀነቭ ያካሄደው የጋራ ውይይት ያጸደቀው የጋራው የፍጻሜ ሰንድ ትላትና በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቶበት ለንባብ መብቃቱ ሲገለጥ፣ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር ያሰሙት የክርስቲያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ዓለም አቀፍ የሉተራን አቢያተ ክርስቲያን ፈደራላዊ ማኅበር እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም. በሚዘክረው 500ኛው ዓመት የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ምሥረታ በዓል ለመሳተፍ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በይፋ ተጋብዛለች” ብለዋል።
በዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሥር የካቶሊክና የሉተራን አቢያተ ክርስቲያን የጋራው ውይይት ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ቱርክ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተጨበጠው የጋራው ስምምነት በእውነት አቢይ ድል መሆኑ አብራርተው፣ ከብዙ የዘመናት ውጣ ውረድና ልዩነት ግጭት አለ መግባባት በኋላ ይኸው ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በጋራና ለውህደት ባቀና መንፈስ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ምሥረታ ለማክበር ሲሰናዱ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ገልጠው፣ ፈደራላዊ የሉተራን አቢያተ ክርስቲያን ማኅበር ዋና ጸሓፊ ማርቲን ዩንግ 500ኛው ዝክረ ዓመት የሉተራን ቤተ ክስቲያን ምሥረታ ለሱታፌ ባቀና መንፈስ የሚመራ ከመሆኑም ባሻገር ሁሉም የጋራ ምስክርነት ይሰጡ ዘንድ የሚያሳስብ ነው። ስለዚህ የሚለያየው ሳይሆን የሚያዋህደው አንድ የሚያደርገውን ባህርይ የሚጎባላበት ወቅት ነው ብለዋል።
ብዙዉን ጊዜ ለመከፋፈል ምክንያት የሚሆነው እርሱም አለ መግባባት ሌላውን አሳስቶ መረዳት ለአንድና ለብቸኛው እምነት ዓንቀጽ የሚሰጠው ቲዮሎጊያዊ ይዞታ ትንታኔና ትርጉም በተመለከተ የተከሰተው ልዩነት ለማግለል ብሎም ለመሰረዝ በቅድሚያ የጋራው መሠረተ የሆነው እምነት በተጠናቀረው የጋራው ሰነድ ሥር ተመልክቶ የሚገኝም ሲሆን፣ ስለዚህ ሰነዱ የጋራው መሠረት የሚያጎላና በተለያየ ወቅት ጊዜው ከሚጠይቀው ጉዳይ ጋር በተዛመደ መልኩ መንፈስ ቅዱስ ባነቃቃቸው የተለያዩ የአቢያተ ክርስቲያን ማኅበራት አማካኝነት የተመሠረቱት እንቅስቃሴዎች መካከል እርቅ እንዲኖር ያለው አስፈላጊነትም የተሰመረበት ጰራቅሊጦሳዊ መልክ የሚያጎላ ሰነድ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.