2013-06-19 15:36:12

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት በማድረግ የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ትላንትና አባ ኮዋልዝዪክ ባቀረቡት “ኩላዊ ፍርድ የምኅረት ፍርድ ይሆናል” በሚል ቲዮሎጊያዊ ሓሳብ ላይ በማተኮር 31ኛው ክፍለ አስተምህሮ ሥር፦ በታሪክ ሂደት ስንዴና እንክርዳድ አብረው እደሚያድጉ ሁሉ በጎ ነገር በክፉ ላይ በመጨረሻ አሸናፊ መሆኑን ለመግለጽ በዓለም ፍጻሜ የፍርድ ቀን ክርስቶስ በክብር ይመጣል” (የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህረተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 681) ሚል ቃል እናገኛለን በምንናዘዘው ተአምኖተ እምነት ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሙታንና ሕያዋንን ለመፍረድ ዳግም ይመጣል የሚል አምናለሁኝ ይኽም ክርስቶስ የህያዋንና የሙታን ጌታ ነው ‘…እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁና እዞአችሁ..(ዮሐ. 16.33)” በሚለው ቃሉ የተረጋገጠውን አንቀጽ እንናዘዛለን።
ኵላዊ ፍርድና ግላዊ ፍርድ ማለትም እያንዳንዱ የገዛ እራስ ሞት በመሞት ወዲያውኑ የሚያጋጥም ፍርድ ለያይቶ መመለከት ያለው አስፈልጊነት በዕብራውያን ምዕ. 9. 27 ለሰው አንድ ጊዜ መሞት የተገባ ነው፣ ከሞት በኋላም ፍርድ አለበት” የተጻፈው ቃል መሠረት በማድረግ አብራርተው “ዳግመ ትስብእት ብሎ ነገር የለም፣ ሰብአዊ ታሪክ አግዳሚ መሥመር ነው። መጀመሪያና መጨረሻ መነሻና ማረፊያ ያለው ነው። አንድ ሕይወት አንድ ሞት ብቻ ነው ያለው። ልዩ ፍርድ እያንዳንዳችን ከሞት በኋላ የሚያጋጥመን ነው። ኵላዊ ፍርድ ግን መላ ታሪክና መላው ትውልድ የሚመለከት ነው።”
“ፍርድ የሚሰጠው ያ በመስቀል ስለእኛ መዳን ሲል የሞተው ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ፍርዱ ምህረት ነው፣ ሆኖም ግን ‘…በዚያ ጊዜ የእያንዳንዱ ጠባይና የልቡ ምሥጢር ይጋለጣል’ (ቍ. 678 ተመል,) ኃጢአተኛውን ለመፍርድ ሳይሆን ለማንጻትና ለማዳንም ነው። የመጨረሻው ፍርድ መመዘኛውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘…ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደርጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው’ (ማቴ. 25.40)። በማለት የገለጠው፣ ሁሉ እያንዳንዱ ያደረገው ክፋት ሁሉ የሚገለጥ ሲሆን፣ አነስተኛ ለሆኑት ያደረግነው ትንሽ ነገር ሁሉ ግልጽ ሆኖ ይገለጣል” በማለት ያቀረቡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.