2013-06-19 15:26:01

የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሰኔ 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ዕለተ ረቡዕ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአጸደ ቅዱስ ጲጥሮስ ከውጭና ከውስጥ የተወጣጡ ከ 50 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ባቀረቡት ሥልጣናዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ጌታችን ከመከፋፈልና በመካከል ሊከሰት ከሚችለው ጥላቻና የእርስ በእርስ ትግል ነጻ ያወጣን ዘንድ እንጠይቀው” በማለት የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን ምን ማለት መሆኑ ሲገለጥ፦ “በክርስቶስ አንድ መሆን ማለት ነው” ካሉ በኋላ ሁሉም ክርስቲያኖች ለሱታፌና ለውህደት እንዲተጉ ማሳሰባቸው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
ቤተ ክርስቲያን የሰብአዊ ማኅበር የግብረ ሰናይ ማኅበር የባህል የፖለቲካ ማኅበር ማለት አይደለችም፣ በታሪክ የምትጓዝና የምትሠራ ሕያው አካል ነች” ከሚለው ጥልቅ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች በጻፋት ቀዳሜ መልእክት ሕያው አካለ ክርስቶስ በሚለውን የቤተ ክርስቲያን ትርጉም ዙሪያ ያቀረቡት ሥልጣናዊ ተንታኝ ትምህርተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሕያው ተጨባጭ አካል ነች። እራስ ከተቀረው የሰውነት አካል ከተለየ መላ አካል አይኖርም፣ በቤተ ክርስቲያንም እንዲህ ነው። ሁላችን የተዋሃድን መሆን አለብን፣ ዘወትር ከኢየሱስ ጋር የተሣሰርን መሆን ይገባናል፣ እርሱ የሕያውነት ምንጭ ነው። ኢየሱስ በእኛ ውስጥ ይሠራ ዘንድ ልንፈቅድለት ይገባናል፣ በቃሉ ይመራን ዘንድ በቅዱስ ቁርባን ህላዌው እየመገበ ባለንጀራችን ለማፍቀር በሚያበቃን የፍቅሩ ኃይል አማካኝነት ያነቃቃናል።”
“የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን ከክርስቶስ ጋር የተወኃደ እንደ ክርስቲያን የሚያኖረን መለኮታዊ ሕይወት ከእርሱ መቀበል ማለት ነው። ይኽ ማለት ደግሞ የአንድነትና የሱታፌ የውህደት መሣሪያ ከሆኑት ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ከብጹዓን ጳጳሳት ጋር ህብረት ውህደትና ሱታፌ ማለት ነው። ግለኝነት እኔነት መከፋፈልን በማግለል በብዙሁነት የእያንዳንዱ ጸጋ በማስማማት ለመኖር የሚያበቃ መሣሪያ ነው” ብለዋል።
ቅዱስነታቸው አንድነት የላቀ መሆኑም ሲያብራሩ፦ “በሚከፋፍለው የርእስር በእርስ ግጭት በሚያነቃቃው መንገድ አንጓዝ። ያለን ልዩነትና ብዙህነት ሥር አንድነት ሊኖረ ይገባል። ዘወትር የክርስቶስ የሆነው ውህደት ሊኖረን ይገባል። አንድነት የላቀ ነው። ጸጋ ነው። ስለዚህ ጌታ አንድነት እንዲሰጠን ከመከፋፈል ፈተና ከእርስ በእርስ ግጭት ከእኔ ባይነት ከሃሜትና አሉ ባልታ ፈተና ነጻ ያወጣን ዘንድ ጌታን እንለምነው” ብለው ይኸንን የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለማቅረብ ወደ አጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከመምጣቸው በፊት ከወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መጋቤ ጋር የጧት ጸሎት አብረው ጌታ ውህደት አንድንነት እንዲሰጥ ስለ አንድነት በጋራ መጸለያቸው ገልጠው፦ “እኛ ካቶሊኮች በመካከላችን አንድነት ከሌለን እንዴት ከሌሎች ማኅበረ ክርስቲያንና አቢያተ ክርስቲያን ጋር ውህደት እንዲኖርን እንጸልያለን፣ ስለዚህ ውህደት በቅድሚያ በቤተሰብ ውስጥ። ስንቱ ቤተ ሰብ እርስ በእር ይጋጫል ይከፋፈላል? እርስ በእርሳችን እንተሳሰብ…ቤተሰብ የሁሉም ድጋፍ የአቢያተ ክርስቲያን የመንግሥት ድጋፍ ያሻዋል፣ በቤተ ሰብ ገጽ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል ታትሞ ይገኛልና” ካሉ በኋላ አያይዘውም፦ “ሁሉም ሕይወት በሁሉም መልኩና ደረጃው ለማነቃቃትና ለመከላከል የሕይወት ወንጌል እንዲያስተናግድና እንዲመስከር አደራ እላለሁ። ክርስቲያን ለሕይወት እሺ የሚል ለሕያው እግዚአብሔር እሺ የሚል ነው” በማለት ያሰሙትን ሥልጣናዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አጠናቀው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት መሸኛታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.