2013-06-19 15:28:42

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በጽናት በትዕግሥትና በደስታ ኢየሱስን ማወጅ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሰነ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሮማ ሰበካ ዓመታዊ ጉባኤ አገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎ ስድስተኛ የጉባኤ ኣዳራሽ በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ማስጀመራቸው ሲገለጥ፣ ይኽ ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክት ምዕ. 1. 16 እኔ በወንጌል ቃል ኣላፍርም” በሚል ርእስ ሥር እዲካሄድ ያነቃቃውም እሳቸውም ይኸንን የሮማ ሰበካ ምሉእ ጉባኤ በዚሁ ርእስ ሥር ዙሪያ በሚያቀርቡት ትምህርተ ክርስቶስ ለማስጀመር እንደሚሹ ቀደም በማድረግ በማሳወቃቸውን ምክንያት መሆኑ የተካሄደው ጉባኤ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ ገለጡ።
ቅዱስነታቸው ያሰሙት ሥልጣናዊ ምዕዳን በሮማ ሰበካ ጳጳስና በሰበካው ምእመናን ውሉደ ክህነት መካከል ተወያይነት መንፈስ የተካነው ሆኖ የሚማርክ በሰበካ ሮማ የሁሉም ምእመናን ሱታፌ የሚያነቃቃ መሆን እንዳለበት የቅዱስ ጳውሎስ ዱካ የተከተለ እንደነበር የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አክለውም፦ “ነቢይ ሕዝቅኤል እግዚአብሔር ድንጋያማው ልብ ወደ ስጋዊ ልብ እንደሚለውጥ ይናገራል፣ ይኽ አነጋገር ምን ማለት ይሆን? የሚያፈቅር ልብ፣ በሌላው ስቃይና ደስታ የሚሳተፍ ርህሩህ የኅብረተሰብ የሕይወት ቁስል የገዛ እራሱ በማድረግ የሚጓዝ በተለያየ ምክንያት ተገዶ ከማእከላዊ የከተማ ክልል ተገሎ ከሚኖረው የከተማ ዳርቻ ነዋሪ ሕዝብ ጋር አንድ የሆነ፣ ስግብግብነት እራስ ወዳድነት አንዱ ከሌላው የሚነጥለው የግንብ አጥር የሚያገል ማለት ነው። ይኽ ፍቅር ከድጋያማነት ወደ ሥጋ ከተለወጠው ሰብአዊ ልብ የሚመነጭ ነው። ይኽ ዓይነቱ አቢይ ጸጋ ነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
“በከተማ ሮማ የተለያየ ችግር በተሞላው ሁነት በቀቢጸ ተስፋ ተነክሮ የሚኖር ሕዝብ አለ፣ እነዚህን በቀቢጸ ተስፋነት የሚኖሩት በአቢይና ጥልቅ በተለያዩ የተሳሳተ መንገድ እርሱም ከአልኮል መጠን ከአዳንዛዥ እጽዋት ሱሰኝነትና ከአመጽ ምርጫ ለመውጣት ከሚጣጣሩበት ብቸኝነት በሚያንጸባርቀው ዝምታ ተውጠው የሚኖሩትን በጽሞና የሚያስብ ሰው አይጠፋም፣ በሐዘን ተውጦ አለ ተስፋ የሚኖር ስንቱ ነው። እኛ ለዚህ ሕዝብ በቃልና በሕይወት በነጻነታችን ደስተኞች በመሆናችን ላይ በጸና ምስክርነት ክርስቲያናዊ ተስፋ ማቅረብ ይኖርብናል፣ ጉዲፈቻ ሳንሆን አባት ያለን ከመሆኑ ካለው እርግጠኝነት የሚመነጭ ደስታ የምንኖርባት ከተማ አስባም ይሁን ሳታስበውም በምትኖረው አደገኛ ሁነት አማካኝነት ከምታቀርብልን እርዳኝ ከሚለው ተስፋ የሚመኝ መጻኢን በእማኔና በተረጋጋ መንፈስ ለመመልከት የሚሻ ለምታቀርብልን ጥያቄ ችላ ማለቱ ይቻለናልን? እኛ ፈጽሞ ችላ ማለት አንችልም” ካሉ በኋላ አክለው ይኽ ወደ እኛ ቢጠዎች ማለት ወደ ድኾች መሄድ ማለት ሲሆን፣ ወደ ሌላው መሄስድ መጽዋች ወይንም የጎዳና ተዳዳሪ መንፈሳውያን መሆን አለብን ማለት አይደለም በሚሰቃየው ሰው ዘንድ ወዳለው ወደ ሚሰቃየው የክርስቶስ አካል መሄድ ማለት ነው። ይኽ በሚሰቃየው በተናቀው ያለው የሚሰቃየው የክርስቶስ አካል ሥነ እውቀት ሥነ ባህል የማያውቀው ነው። ወደዚሁ ኢየሱስ ነው መሄድ ያለብን፣ ስለዚህም ነው ወደ ከተማ ክፍለ ዳርቻ መሄድ የሚለው ቃል ለመጠቀም የምወደው፣ ባህላዊ ሥነ እወቀታዊ ቍሳዊ ድኽነት የሚታይበት ክፍል ነው። ወደዚያ እንሂድ፣ እዛ በመሄድም የወንጌል ቃል በቃልና በሕይወት ምስክርነት እንዝራ። በትእግሥትና በጽናት ምን ማድረግ ይኖርብናል? ከገዛ እራሳችን አጥር መውጣት ከገዛ እራስ ማኅበርሰብ መውጣት ይኽም ወደ ሌሎች ወደ ተናቁት ወደ ሚሰቃዩት የሚመራን ለእነርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ናዝራዊ አማካኝነት ለሰው ልጅ የተገለጠው የአብ ምኅረት ለማበሰር የሚያበቃን ነው። ከኢየሱስ የተለገሠልንን ጸጋ እናውጅ። ይኽ ጥሪ ሊያስደነግጠን አይገባም ይኽ ሰማዕትነት ማለት ነው። ሰማዕትነት ዕለት በዕለት ለመመስከር መታገል ማለት ነው። ጌታ ከእያንዳንዳችን የደም ሰማዕትነትን ይጠይቃል፣ ሆኖም ግን ዕለት በዕለት የሚኖር ሰማዕትነትም አለ፣ እርሱም ዕለት በዕለት እኛ አብሳሪዎች እንድንሆን የማይሻው የክፋት መንፈስ የሚቃወም ምስክርነት ማቅረብ ማለት ነው።”
“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ አትፍሩ! ወደ ፊት እንበል። በኢየሱስ ጸጋ ሥር መሆናችን ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን እንንገር፣ የእርሱ ጸጋ ዋጋ የሚጠይቅ ሳይሆን መቀበልን ብቻ ነው የሚሻው። ወደ ፊት እንበል” ብለው ሐዋርይዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.