2013-06-12 16:32:34

የ ር ሊ ጳ ፍራንሲስ ስብከት ፡ .


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር ጥዋት እንደሚፈጽሙት ሁሉ ትናታና ጠዋታም በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ከሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ጌርሃርድ ሉድቪሽ ሙለር በሁባሬ ሥርዓተ ቅዳሴ ፈጽመዋል።ቅድስነታቸው በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት አንድ ሃብታም ቤተ ክርስትያን የምታርጅ ሕይወት አልባ ቤተ ክርስትያን ነች ብለዋል።
ቅዱስ ወንጌል በነፃ እና በቀላሉ መስበክ ቀዳሚ ዓላማ ቤተ ክርስትያን መሆን እንዳለበትም ፓፓ ፍራንሲስ በተጨማሪ ሰብከዋል።መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቱን ሄዱ እና የእግዚአብሔር መንግስትን ማለት መንግስተ ሰማያትን ስበኩ ብሎ ማለቱ በምስታወስም ራሱ የመሰረታት ቤተ ክርስትያን ዒላማም ይህ መሆኑ ነው ሲሉ ሰብከዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ።በማያያዝም ሐዋርያዊ ስብከት በነፃ መሰጠቱ እና በነፃ የተቀበልነው በነፃ መስጠት ይጠበቅብናል ይሉና ስብከታቸው በመቀጠል ቅዱስ ጰጥሮስ በባንክ ሂሳብ አልነበረው ቀረጥ የመክፈል ነገር ሲመጣ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓሳ እንድያጠምድ እና ገንዘቡ ዓሳ ውስጥ ፈልጎ ቀረጡን እንዲከፍል ጠየቀው ብለዋል።ስለዚህ ሃብታም ቤተ ክርስትያን ቶሎ የምታርጅ እና ሕይወት የሌላት ቤተ ክርስትያን መሆንዋ አውስተው ሃብታም ቤተ ክርስትያን ሃብትዋ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል እና የመንግስተ እግዚአብሔርን መንገድ መምራት ነው ብሎዋል ።
መንግስተ እግዚአብሔር መንግስተ ሰማያት ምንም የማይከፍለበት ነፃ መሆኑ የሰበኩ ፓፓ ፍራንስሲ ስለሆነም ቤተ ክርስትያን ድሃ እና ከድሆች የምትጓዝ ቤተ ክርስትያን መልካም መሆኑ አመልክተዋል። ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሰባኪ ቅዱስ ወንጌል ድሃ እና ማራኪ ህዝበ እግዚአብሔርን ሰባኪ መሆን አለባት ምክንያቱም እግዚአብሔር በምሕረቱ በኩል ድህነታችን በነፃ እንደሰጠን አስታውሰዋል።የቤተ ክርስትያን ሀብት ክርስቶስ የሰው ልጅን ከሐጢአቱ አገላግሎ ህዝበ እግዚአብሔርን ወደ መንግስተ ሰማያት ለመምራት የተሰጣት ስጦታ እና ጸጋ ነው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቃል ።እዚህ መጠቀስ ያለበት ጉዳይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ባላፈው ወርሃ መጋቢት ቤተ ክርስትያን ድሃ እና ከድሆች እና ከሕብረተ ሰብ ከተገለሉ ማሕበረ ሰቦች ጋር መራመድ እንዳለባት ማውሳታቸው ጠቅላላ የዓለም ነገር እርግፍ አድርጎ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር የሆነውን ዓቢይ የቤተ ክርስትያን አባት ፍራንቸስካዊ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ስም መምረጣቸው አይዘነጋም ።
ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ትናትና ጥዋት በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እና ብሳአም ኡት ስብከት ቤተ ክርስትያን ngo የመንግስት ያልሆነ ተቋም እንዳልሆነች እና ቤተ እግዚአብሔር እና የህዝበ ክርስትያን መሪ መሆንዋ ግልጽ አድርገዋል ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቤተ ክርስትያን ውስጣዊ አስራር በተለይ መንፈሳውነት እና ማቴርያላዊ በሚመልከቱ ጉዳዮች ስር ነቀል ለውጥ ያደርጋሉ ተብለው እየተጠበቁ መሆናቸውም አይዘነጋም።








All the contents on this site are copyrighted ©.