2013-06-12 18:24:30

ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ወንሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! RealAudioMP3
ዛሬ የምንመለከተው ትምህርት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስትያንን ለመግለጽ የተጠቀመው ሓረግ ማለትም “ሕዝበ እግዚአብሔር” (ብርሃነ አሕዛብ ቍ 9፤ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ቍ 782 ተመልከት)፣ ይህንን ሳደርግ ደግሞ እያንዳንዳችን ሊያሰላስላቸው በሚችሉ አንዳንድ ጥያቄዎች በማቅረብ ነው፣



          ሕዝበ እግዚአብሔር መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ከሁሉ አስቀድመን ማወቅ ያለብን እግዚአብሔር በልዩ መንገድ የአንድ ሕዝብ ብቻ ወገን አይደለም፤ ምክንያቱም የሚጠራንና የሚሰብሰበን እንዲሁም የሕዝብ አባሎች እንድንሆን የሚጠራን እርሱ ነው፣ ይህም ጥሪ አለምንም ልዩነት ለሁሉም የሰው ዘር የሚቀርብ ነው፣ የእግዚአብሔር ምሕረት “የሁሉ ሰዎች ደኅንነትን ይፈልጋልና” (1ጢሞ 2፤4)፣ ኢየሱስ ለሐዋርያት እንዲሁም ለኛ ልዩ ጽንፈኛ የብልጦች ቡድን እንድናቆም አይጠይቅም፣ ኢየሱስ የሚለው “ሂዱና የመላው ዓለም ሰዎች የኔ ደቀ መዛሙርት አድርግዋቸው ይላል” (ማቴ 28፤19)፣ ቅዱስ ጳውሎስ በሕዝበ እግዚአብሔር ማለትም በቤተ ክርስትያን “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” (ገላ 3፡28) ይላል፣ ዛሬ ከእግዚአብሔር እና ከቤተ ክርስትያን የራቀ ሆኖ የሚሰማውን ፍርሃት የሚሰማውን ወይንም ግድየለሽ የሆነው ሊለወጥ የማይችል ሆኖ የሚሰማውን ሳይቀር እግዚአብሔር የሕዝቡ አካል እንድትሆን አንተንም እየጠራ ነው ይህንን ደግሞ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ያደርገዋል ብየ ልነግራቸው እሻለሁ፣ እርሱ የዚሁ ሕዝብ የእግዚአብሔር ሕዝብ አካል እንደሆን ይጠራናል፣
          የዚህ ሕዝብ አባል እንዴት ይሆናል? በሥጋዊ ልደት ሳይሆን በአዲስ ልደት ነው፣ በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለመግባት ከላይ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ ያስፈልጋል (ዮሓ 3፡3-5 ተመልከት) ይለዋል፣ እኛ ከዚሁ ሕዝብ ጋር የምንቀላቀለው በጥምቀት እና ከእግዚአብሔር በሚሰጠን የክርስቶስ እምነት ነው፣ ይህ እምነት በመላው ሕይወታችን መመገብና ማደግ አለበት፣ ወደ ገዛ ራሳችን ተመልሰን ይህንን በጥምቀቴ የተቀበልኩት እምነት ለማሳደግ ምን አደርጋለሁ? ይህንን እኔ የተቀበልኩትና ሕዝበ እግዚብሔርም ይዞት ያለ እምነት እንዴት አሳድገዋለሁ? ብለን እንጠይቅ፣
          ሌላው ጥያቄ! የሕዝበ እግዚአብሔር ሕግ ምንድር ነው? የሚል ነው፣ መልሱም የፍቅር ሕግ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ በተወልን አዲስ ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር ማፍቀርና ጓደኛህን እንደገዛራስህ አድርገህ ማፍቀር ነው (ዮሐ 13፡34)፣ ይህ ፍቅር ፍሬ አልባ ስሜታዊ የማይጨበት መሆን የለበትም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ አንድያ የሕይወት ጌታ ማወቅ፤ ሌሎች ሰዎችንም ከመከፋፈል ከውድድር ካለመግባባት እና ካለ ለኔ ብቻ እንደ ወንድሞች መቀበል ነው፣ እነኚሁ ሁለተ ነገሮች አብረው ነው የሚጓዙት፣ ይህንን አዲስ ሕግ ራሱ ምግባረ ሠናይና ፍቅር የሆነው በሕይወታችን ሁሌ በሚሠራ መንፈስ ቅዱስ በተጨባጭ በተግባር ለመኖር መጓዝ አለብን፤ በጋዜጦች በተለቪዥን የተመለከታችሁ ብዙ በክርስትያን መካከል የሚካሄዱ ውግያዎች ይታያሉ፣ ነገር ግን ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? በሕዝበ እግዚአብሔር መካከል ስንት ውግያ እየተካሄደ ነው! በተለያዩ ቀበሌዎች በሥራ ቦታዎች ስንድ የቅናት ውግያዎች ይካሄዳሉ! በቤተሰብም ሳይቀር ውሳጣዊ ውግያዎች አሉ! ይህንን የፍቅር ሕግ በይበልጥ ለመረዳት እንድንችል ጌታን እንለምነው! እርስ በእርሳችን እንደወንድማሞች መፋቀር ምኑን ያህል ደስ ያሰኛል! ዛሬ አንድ ነገር እናድርግ! ደስ የሚሉንና ደስ የማይሉን ሊኖሩ ይችላሉ! አብዛኛዎቻችን የተቀየምነው ሰው ይኖረናል! ስለዚህ መጀመርያ ለጌታ እንዲህ እንበለው! ጌታ ሆይ! ከእገሌ ከእገሊት ጋር ተቈጥቼ ነበር አሁን ለእርሱ ለእርስዋ እጸልያለሁ እንበል! በዚሁ የፍቅር ሕግ ስላስቀየሙን ሰዎች መጸለይ ጥሩ እርምጃ ነው፣ እናደገዋለን ወይ! ዛሬ ይህንን እናድርግ፣
          ሕዝበ እግዚአብሔር ምን ተልእኮ አለው? ለመላው ዓለም የእግዚአብሔር ተስፋና ደኅንነት ማዳረስ ነው፣ ሁላችንን ከእርሱ ጋር ጓደኞች እንድንሆን የሚጠራን የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት ለመሆን ነው፣ ሊጡን በሙሉ የሚያቦካ እርሾ መሆን ነው፤ ጨው በመሆን ጣዕም መስጠትና ከሙስና መጠበቅ ነው፣ ለሁሉ የሚያበራ ብርሃን መሆን ነው፣ እላይ እንደጠቀስኩት ጋዜጣ ስንቃኝ በዓለማችን ስንት ክፋት እንዳለ እንገነዘባለን! ሠይጣን እየሰራ ነው! ነገር ድምጼን ከፍ አድርጌ እግዚአብሔር ከእርሱ ያይላል! እናንተ ይህንን ታምናላችሁን? እግዚአብሔር ኃይል መሆኑን፣ እስቲ አብረን እንበለው! እግዚአብሔር ኃያል ነው! ለምን ኃያል መሆኑን ታውቃልችሁን? ምክንያቱም እርሱ ጌታ ነው፣ አንድያ ጌታ ካለ እርሱ ሌላ ጌታ የለም፣ ሌላ ነገርም ለመጨመር እሻለሁ! እኛ የወንጌል ብርሃንን ከሁሉ በላይ ደግሞ በአኗኗራችን የሰጠን እንደሆነ በክፋት የሚገለጠው ጨለማ ሊለወጥ ይችላል፤ ለምሳሌ እዚህ ሮም ውስጥ በኦሊምፒክ ስታድዩም ወይም በቦነስ አየርስ ስላለው የሳን ሎረንዞ ስታዩም በአንድ ጨለማ ሌሊት አንድ ሰው ብርሃን ያበራ እንደሆነ ወዲያውኑ ይታያል ነገር ከስልሳ ሺ በላይ የሚሆኑ ታዛቢዎች እያንዳንዳቸው ብርሃናቸውን ያበሩ እንደሆነ ስታድዩሙ በብርሃን ያሸብርቃል፣ ሕይወታችን የክርስቶስ ብርሃን እንድትሆን እናድርግ፣ በአንድነት ለመላው ዓለም የወንጌል ብርሃንን እንሰጥ፣
          የዚሁ ሕዝበ እግዚአብሔር ዓላማ ምንድር ነው?ዓላማቸው የእግዚአብሔር መንግስት ነው፣ ይህም መጀመርያ በዚህ ምድር በእርሱ የተጀመረ ነው፤ ሕይወታችን የሆነው ክርስቶስ ዳግም እኪመጣ ድረስ ደግሞ በእርሱ መጕላትና ፍጽምና ላይ ይደርሳል (ብርሃነ አሕዛብ 9)፣ ስለዚህ ዓላማው ከጌታ ጋር ሙሉ ሱታፌ ማድረግ ነው፣ ወደር የሌለው የፍቅሩ ደስታን በምናጣጥምበት ሙሉ ደስታ በሚሰጠው በመለኮታዊ ሕይወት ውስጥ ገብቶ ከጌታ ቤተሰብ መሳተፍ ነው፣





ውድ ወንድሞችና እኅቶች! በእግዚአብሔር አብ ታላቅ የፍቅር ዕቅድ የቆመች ቤተ ክርስትያን መሆን ሕዝበ እግዚአብሔር መኖር ማለት ለመላው የሰው ልጅ የእግዚአብሔር እርሾ መሆን፤ ዓለማች ብዙ ጊዜ አጥፋትው ለጉዞዋ የሚሆኑ አዳዲስ ኃይሎችና ተስፋዎችና ብርታት የሚሰጥዋት መልሶች እየተጠባበቀ ላለችው የእግዚአብሔር ደኅንነትን መስበክና ማዳረስ ነው፣ ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ምሕረትና ተስፋ ቦታ በመሆን እያንዳንዱ ባለቤት የተፈቀረ ይቅር የተባለ እንደ ወንጌል መልካም ሕይወት ለመኖር ብርታት የሚያገኝበት ቦታ መሆን አለበት፣ እያንዳንዱ ተቀባይነት ያገኘበት የተፈቀረበት ይቅር የተባለበትና ብርታት ያገኘበት ቦታ ሆኖ እንዲሰማው ግን ቤተ ክርስትያን ክፍት መሆን አለባት ምክንያቱም መግባት እንዲችሉ፣ እኛም ከውስጥዋ ወጥተን ወንጌልን ለምስበክ እንድንችል የቤተ ክርስትያን በሮች ክፍት መሆን አለባቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.