2013-06-11 11:31:24

ጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ እውነተኛ ምልክት ነው፤ ሁል ጊዜ ስለሚምረን ወደ እርሱ ለመቅረብ አንፍራ፤


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመል አከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው በፊት በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ባለፈው ዕለተ ዓርብ ተዘክሮ ለዋለው በዓለ ጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ የሚመለከት አስተምህሮ አቅርበዋል፣
የኢየሱስ ልብ ሓሳባዊ ምልክት ሳይሆን የእርሱ ፍቅርና ሕይወት ከሙታን ስለሚያነሳ እውነተኛና ተጨባጭ ምልክት ነው፣ ጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ በሰብአዊ አስተሳሰብ የላቀ የመለኮታዊ ፍቅር መግለጫ ነው፣ በቤተ ክርስትያን ልማድም የሰኔ ወር ለጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ የተሰጠ ነው፣ ይህ በብዙ ሰዎች የሚዘወትር በጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ የሚደረግ ጸሎትና አክብሮት የላቀውን የእግዚአብሔር ምሕረት የሚያመልክት የኢየሱስ ልብ ምልክት ታላቅ ዕሴት አለው፣ ሲሉ ጥልቅ ትርጉሙን ከገለጡ በኋላ መጠንቀቅ ያለብን ጉዳይ እውነተኛነቱንና ተጨባጭነቱን መሆኑን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ሆኖም ግን የሓሳብ ምልክት አይደለም፤ እውነተኛ ምልክት ነው፣ ለመላው የሰው ልጅ ደህንነት የሚጐርፍበት ምንጭ ሆኖ የደህንነታችን አንኳርን የያዘ ተጨባጭ ምልክት ነው፣
በተለያዩ የወንጌል ክፍሎች ከጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ ለሁሉ የሰው ልጅ ዘር የሚሆን ይቅርታና ሕይወት ይፈልቃል፣
“ነገር የኢየሱስ ርኅራኄ ስሜት ብቻ አይደለም ሕይወት በመስጠት የሰው ልጅን ከሙታን የሚያነሳ ኃይል ነው፣
ወንጌላዊው ሉቃስ በዛሬው ቃል ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከገሊላ ተነስተው ወደ ናይን በደረሱ ጊዜ አንዲት ባልዋ የሞተና አንድ ልጅ ብቻ የነበራት ድኃ ሴት ልጅዋ ሞቶ ለቀብር ሲዘጋጁ ይደርሳሉ፣ ኢየሱስም እጅግ ራራላት፣
“ይህ ርኅራኄ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር ነው፣ ምሕረቱ ነው፤ ምሕረቱም እግዚብሔር ከሰው ልጅ ምስኪንነት ጋር ሲገናኝ የሚያሳየው ርኅራኄ ነው፣ ከሥቃያችን ከኃዘናችን ጋር በሚገንኝበት ጊዜ የሚያሳየው ርኅራኄ ነው፣ ርኅራኄ የሚለው ወንጌላዊ ቃል እናት ለልጅዋ የምታሳየው ፍቅር ድንጋጤ ሆደ ባባነትን ያመልክታል፣ እግዚአብሔርም እንደዛ ያፈቅረናል፣ የዚህ ሁሉ ፍቅር የዚህ ሁሉ ምሕረት ፍሬ ምንድር ነው? ብለን የጠየቅን እንደሆነ መልሱ ሕይወት ነው፣ የእግዚአብሔር ምሕረት ለሰው ልጅ ሕይወት ይሰጣል፣
“እግዚአብሔር ሁሌ በምሕረት ዓይን ይመለከተናል፤ ይህንን እንዳንረሳው፤ ዘወትር በምሕረት ዓይን ይመለከተናል በምሕረትም ይጠባበቀናል፣ ወደ እርሱ ለመቅረብ አንፍራ! ርኅሩኅ ልብ አለውና! ውሳጣዊ ቍስሎቻችን ኃጢአቶቻችን ያሳየነው እንደሆነ ሁሌ ይቅር ይለናል፣ ሲሉ ስለ እግዚአብሔር ርኅራኄ ካስተማሩ በኋላ ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም መለስ ብለው ይህንን ጸሎት አሳርገዋል፣
“የእናት ልብ ንጹሕ ልበ ድንግል ማርያምም ይህንን የእግዚአብሔር ታላቅ ርኅራኄ ተሳትፈዋል በተለይ ደግሞ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሲሰቃይና ሲሞት፣ ከወንድሞቻችን ጋር ትሑቶች ርኅሩኆች እና ይቅር ባዮች እንድንሆን እመቤታችን ድንግል ማርያም ትርዳን ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከጸሎቱ በኋላ በዕለቱ በፖላንድ ብፅናቸው የታወጀው ሁለት ደናግሎች እናት ሶፍያና እናት ማርገሪታ ሉችያን በማስታወስ “በክራኮቭያ ከምትገኘው ቤተ ክርስትያን አብረን ለእግዚአብሔር ምስጋና እናቅረብ” ብለዋል፣
ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሕዝቡ እንደገና እንደገና እንዲህ ሲሉ አመግነዋል፣
“እግዚአብሔር ይስጥልኝ! ዛሬ ሁል ጊዜ የሚመለከተን የሚያፈቅረንና የሚጠባበቀንን የእግዚአብሔር ፍቅር የኢየሱስ ፍቅር አንርሳ፣ ሁሉ ልብ ነው ባጠቃላይም ይቅር ባይነት ነው፣ ወደ ኢየሱስ ብመተማመን እንጓዝ እርሱ ሁሌ ይቅር ይለናልና፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመል አከ እግዚአብሔር ጸሎትና ጉባኤ አስተምህሮ በኋላ በዘመናችን መገናኛ ብዙኃን ትዊተር “ባለንበት ዘመን በማባካን ባህል የሰው ልጅ ሕይወት ከሁሉ በላይ መከበርና መንከባከብ ያለበት ዕሴት መሆኑ እየተዘነጋ ነው” ሲሉ ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.