2013-06-11 11:36:04

ሕይወትን በእግዚአብሔር ቃል ማንበብንና፤ ቃለ እግዚብሔርን ተቀብለን በልባችን ማኖር ከእመቤታችን ድንግል ማርያም እንማር፣


በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ባለፈው ቅዳሜ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ንጹሕ ልብ በዓል ተከብረዋል፣ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ “እንደ እመቤታችን ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ቃልን ተቀብለን በልባችን ማኖርን ከእመቤታችን ድንግል ማርያም እንማር” ሲሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሕይወትን በቃለ እግዚአብሔር ታነበው እንደነበረችና ይህም ቃሉን መጠበቅ መሆኑን አመልክተዋል፣ በቅዳሴው የተሳተፉት የዓለም ዓቀፍ ምግባረ ሠናይ ካሪታስ ኢንተርናስዮናሊስ አባላት በጠቅላይ ጸሓፊያቸው ሚሸል ተሸኝተው ነበር፣
የዕለቱ ቃለ ወንጌል ኢየሱስ ሕጻን በቤተ መቅደስ ጠፍቶ ሶስት ቀን የቆየበትን ታሪክ የያዘ ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ከወንጌሉ ያ ሊቃውንት ያሳዩት መገረምንና በስተመጨረሻም ማርያምም ይህንን ሁሉ በልብዋ ትይዘው ነበር የሚሉ ቃላትን እንዲህ ሲሉ ተንትነዋል፣
“የእግዚአብሔር ቃልን በልብ መያዝ ምን ማለት ነው? ቃሉን ተቀብዬ በአንድ ጥርሙስ አስቀምጤ እንደመጠበቅ ይሆን? አይደለም፣ ቃለ እግዚአብሔርን በልብ መያዝ ማለት ልባችን ይከፈታል፣ ይህም ልክ መሬት ዘርን ለመቀበል እንደምትከፈተው ዓይነት፣ የእግዚአብሔር ቃል ዘር ነው! መዘራትም አለባት፣ ኢየሱስም በዘርና ገበሬው ምሳሌ አንዳንዶቹ በመንገድ ይወድቃሉ የሰማይ ወፎች መጥተውም ይለቅሙታል፣ ይለናል! የዚህች ዓይነት ቃሉ አልተጠበቀም ማለት እነዚህ ዓይነት ልቦች ቃሉን እንዴት አድርገው መቀበል እንዳለባቸው አያውቁም፣ ሌሎቹ ብዙ አፈረ በሌለበት ይወድቃሉ ወዲያው ግን ይሞታሉ፣ የዚህ ዓይነት ሰዎችን ኢየሱስ ጽኑ ያልሆኑ ይላቸዋል ምክንያቱም ቃሉን መጠበቅ አይችሉም፤ በአሉ ምክንያት ስደት የተነሣ እንደሆነ ወዲያውኑ ይረሱታል፣ ኢየሱስ ምሳሌውን በመቀጠል ሌላው ዘር ደግሞ ጥሩ ባልተዘጋጀ መሬት እሾህ ባለበት ወደቀ ይህም ወዲያውኑ በእሾህ ስለታነቀ በደንብ ያልተጠበቀ ቃለ እግዚአብሔር ነው፣ እነኚህ በእሾህ የሚመሰሉ ልባቸው በሃብት በመጥፎ ልማድ የተያዙ ሰዎች ናቸው፣ ስለዚህ ቃለ እግዚአብሔር መጠበቅ ማለት ልክ እንደ ማርያም በልብ ይዞ በእርሱ ማስተንተን መጸለይ ነው፣ አንድ ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ ነው፣
“ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ እመቤታችን ድግንግል በዚህ መንፈሳዊ ሥራ ልብዋ ይደክም ነበር ይላሉ፣ ቃለ እግዚአብሔርን በልብ ለመጠበቅ በዚህ መንፈሳዊ ሥራ ይከናወናል፣ ማስተንተን ትርጉሙ መፈለግ ጌታ በዚሁ ቃሉ አሁኑኑ ምን ይለኛል፤ መል እክቱ ምን ብሎ ያለነውን ሁኔታ ቃለ እግዚአብሔርን በማነጻጸር ማሰላሰል ነው፣ ሕይወትን በቃለ እግዚአብሔር መሠረት ማንበብ ነው፣ ቃለ እግዚአብሔርን በልብ መያዝ ትርጉሙ ይህ ነው፣ ሁሌ በልብ አስቀምጦ ማስታውሱም አስፈላጊ ነው፣ ለማስተንተን ይረዳናልና፣ ከዛም ባሻገር እግዚአብሔር ያደረገልንን ሁሌ ለማስታወስ ይረዳናል፣ ስለዚህ በየዕለቱ እግዚአብሔር በቃሉ እና ባለነው ሁኔታ ምን ይለናል ብለን ማሰላሰል አለብን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.