2013-06-10 16:00:18

ማርሲሊያ፦ Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ


RealAudioMP3 የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት ያነቃቃው መርሃ ግብር በመቀጠል በቅርቡ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 3 ቀን እስከ ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በማርሲሊያ በበዓለም ቅዱስ ልበ ኢየሱስ የተጠናቀቀ ዓውደ ጥናት ማካሄዱ ሲገለጥ፣ የአውደ ጥናቱ መዝጊያ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክት እንዳስደመጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ በኢአማንያን ፈላስፋ ካሙና በአማኒ ፈላስፋ ሪኩዌር ጥልቅ ፍልስፍናዊ ሓሳብ ላይ በማቶከር የተካሄደው ዓውደ ጥናት በእምነትና ዓለማዊነት ሃይማኖትና ሰብአዊነት በሁለቱ ፈላስፋዎች አመለካከት ዙሪያ የተለያዩ አስተምህሮ የቀረበበት ዓውደ ጥናት እንደነበርም ሲገለጥ፣ ካሙ ወደ ባዶነት የሚመራው ኢእግዚአብሔራዊ ባህል በስነ አምክንዮ ሥር በማብራራት የሰጠው ፍልፍናዊ አስተሳሰብ እንዲሁም ሪኩዌር እምነት በስነ አምክንዮ አስደግፎ በማብራራት አለ ማመን ያለው ፍልስፍናዊ ኢአምክንዮ ትንተናው የሚያብራራ ጥልቅ አስተምህሮ ቀርቦ የሃሳብ ልውውጥ መካሄዱ ያስታወቀው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ በሰው ልጅ ዘንድ ያለው ጭንቀትና ውስጣዊ አለ መርካት፣ ሰብአዊ ፍጡር እግዚአብሔር የሚሻ መሆኑ የሚመስከር በኑባሬ የተሰጠ ባህርይ የሚል እውነት የተሰመረበተ ዓውደ ጥናት እንደነበር ብፁዕ ካዲናል ራቫዚ መግለጣቸው ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.