2013-06-08 10:16:37

ለእግዚአብሔር ፍቅር እክል የሚሆኑንን ጣዖቶች እናስወግድ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስ ትናንትና በቅድስት ማርታ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉት ስብከት “እያንዳንዳችን ትናንሽ ጣዖቶች አሉን ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር የሚወስደን መንገድ ለእርሱ ብቻ መሆን እንዳለበት ኢየሱስ አስተምሮናል፤ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ፍቅር እክል የሚሆኑን ጣዖቶችን እናጋልጣቸው፣” ሲሉ ለእግዚአብሔር ብቻ በሙሉ ልባችን ማፍቀር እንደለብንን ለዚህ መሰናክል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማውገድ እንዳለብን አሳስበዋል፣ በመሥዋዕተ ቅዳሴው ከቅዱስነታቸው አብረው የቀደሱ ከብራዚል የኩሪቲባ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኾዘ ቪቲ ከእስፐይን የኢቢዝያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኽዋን ሰጉራ እና ከህንድ አገር የሳጋር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቺራያት አንቶኒ ነበሩ፤ እንዲሁም የቫቲካን ሐዋርያዊ መዝገበ መጻሕት ሠራተኞችና የጳጳሳዊ መካነ ጥበብ ዘላተራን አባላት ነበሩ፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጻዌ መሠረት ለትናንትና የቀረበው ቃለ ወንጌል የማርቆስ ወንጌል 12፤28 ሆኖ “ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎ። ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ጻፊውም። መልካም ነው፥ አለ” የሚለው ክፍል ነበር፣ ቅዱስነታቸው በጸሓፊው አጠያይቅ በተመለከተ ምናልባት በመጀመርያ ጥያቄውን ሲያቀርብ ተንኰል የታከልበት ሊሆን ይችላል፣ ሊፈትነው ነበር ወይንም ባጠሙዱት ወጥመድ ሊከተው ነበር፣ ጌታ መልስ ከሰጠ በኋላ ጸሓፊው ትክክለኛቱን ለማረጋገጥ ከኦሪት ሲጠቅስ ጌታም ከመንግሥተሰማያት ሩቅ አይደለህም ሲለው “ብሐሳብ ሁሉን ነገር ታውቃለህ ነገር ግን ገና ከእግዚአብሔር መንግሥት መጓዝ ያለብህ ርቀት አለ ማለትም ይህንን በሓሳብ የምታውቀው እተግባር ላይ መዋል አለብህ” ለማለት ነው፣
“እኔ በእግዚአብሔር አምናለሁ፤ እግዚአብሔር አንድ ብቻ ነው፤ ብሎ መመጻደቅ ያብቃ፤ በቃልህ ሁሉ ጥሩ ሁኔታ ላይ አለ ሆኖም ግን ይህንን የሕይወት መንጌት እንዴት ትኖረዋለህ? እግዚአብሔር አንድ ብቻ ነው ከእርሱ ሌላ ማንም የለም ብለን መለፍለፍ እንችልለን ነገር እርሱ አንድ አምላክ እንደሆነ በማመን በተግባር መኖር እርሱን ብቻ ማምለክ ላይ ችግር ያለ ይመስላል፤ የአምልኮ ጣዖት አደጋ አለ፣ ይህንን አምልኮ ጣዖት ወደ ልባችን ያመጣው ደግሞ የዓለም መንፈስ ነው፣ ኢየሱስ ስለዚሁ የዓለም መንፈስ ጥርት ባለ መንገድ ይነግረናል፣ በመጨርሻ እራት ላይ ባሳረገው ጸሎትም አባቱን ከዓለም መንፈስ እንዲከላከልልን ይለምነዋል፣ ይህ መንፈስ ወደ አምልኮ ጣዖት ይወስደናል፣
“አምልኮ ጣዖት እጅግ ረቅቂቅ ነው፣ እያንዳንዳችን የገዛ ራሳችን ድብቅ ጣዖቶች አሉን፣ ያ ኢየሱስ ለጸሓፊው ያለው ከእግዚአብሔር መንግሥት ሩቅ ላለመሆን እያንዳንዳችን እነኚህን ድብቅ ጣዖቶች እንወቅ፣ ለዚህም አብነት የሚሆን የያዕቆብ ባለቤት ራሄል ባልዋ ጣዖቶች ይዛ እንዳትሆን በጠያቃት ጊዜ ያ ካባትዋ ቤት ደብቃ ያመጣቸውን ጣዖቶች እንደገና ከእርሱ በመጠበቅ እንደዋሸችው እኛም የምንደብቃቸው ጣዖቶች አይታጡም፣ አሁኑኑ ከተደበቁበት ቦታ አውጥተን እናውድማቸው ምክንያቱም እግዚአብሔርን ለማምለክ አንድያ መንገድ በመተማመን የተመሠረተ ፍቅር ነው፣
“መተማመን ጣዖቶችን ፈልጎ በማግኘትና በማውደማቸው ይመሠረታል፣ እነኚህ ጣዖቶች በማንነታችን በኑሮ ሁኔታዎቻችን ተደብቀው ይገኛሉ፣ እነኚህ ጣዖቶች በፍቅር ታማኞች እንዳንሆን ያደርጉናል፣ ቅ.ያዕቆብ ሓዋርያ በመልእክቱ ይህንን እንደ አመንዝራነት ጠቅሶ ሌሎችም በመዘርዘር “የዚህ ዓለም ጓደኛ የሆነ የእግዚአብሔር ጠላት ነው” ይለናል፣ ለመሆኑ የዚህ ዓለም ጓደኛ የሆነ ለምንድር ነው እንደ ጣዖት አምላኪ የሚታየውና ለእግዚአብሔር ፍቅር ታማኝ አለመሆኑን የሚገልጠው፣ ከእግዚአብሔር መንግሥት ሩቅ ላለመሆንና ወደ ፊት በመገስገስ ወደ እርሱ ለመቅረብ የቃል ኪዳን ፍቅርን የመሰለ የመተማመን መንገድ ያስፈልጋል፣
ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን ሲያጠቃልሉ ለመሆኑ ለዚህ ያህል ትልቅ ፍቅር ካሉን ትናንሽ ወይንም እጅግ ትናንሽ ያልሆኑ ጣዖቶች እንዴት በታማኝነታችን ላለመጕደል እንችላለን? ብለው ይጠይቃሉና እጅግ በሚያቅረን ክርስቶስ መተማመን ሙሉ መተማመን ሊኖረን እንዲሚያስፈልግ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ዛሬ ኢየሱስን ‘ጌታ ሆይ! አንተ እጅግ መልካም ነህ! በየዕለቱ ከእግዚብሔር መንግሥት እንዳልርቅ አስተምረኝ፣ ሁሉንም ጣዖቶች አስወግድልኝ’ ብለን እንለምነው፣ እውነት ነው! ከባድ ነው! ነገር ግን መጀመር አለብን፣ በተለያዩ መደበቂያ ቦታዎች ተደብቀው የሚገኙ ጣዖቶች በማንነታችንን በኑሮ ዘዴዎቻችን ተደብቀው ያሉ ጣዖቶች እንደ የእግዚአብሔር ጠላቶች የሚያድርገን የዓለም መንፈስ የመሳሰሉ ጣዖቶችን እናጥፋቸው፣ ዛሬ ጌታ ኢየሱስን ይህንን ጸጋ እንለምነው” ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.