2013-06-07 16:58:20

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንሲስ የቤተ ክርስትያን አካዳሚ ተማሪዎች ተቀብለው አነጋግረዋል።


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቫቲካን የቤተ ክህነት ጳጳሳዊ አካዳሚ ማሕበረ ሰብ አባላት ተቀብለው አነገግረዋል። ማሕበረ ሰቡ አካዳሚው የቅድስት መንበር ዲፕሎማቶች የሚማሩበት እና የሚነጹበት ተቋም እንደሆነ ይታወቃል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የመጪው ግዜ ዲፕሎማቶች ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ የቅድስት መንበር ዲፕሎማት መሆነ የግል ዒላማ መበልጸግ ወይም የሙያ ታዋቂ ግለሰብ ለመሆን አየደለም ፡ ይህ የስጋ ደዌ በሽታ ወይም ለምጥ ነው ያሉት ቅድነነታቸው የውስጥ ነፃነት እና አርነት ያስፈልጋል ብለዋል። የውስጥ ዓቢይ ነፃነት ምን ማለት ነው ብለው የጠየቁ ፓፓ ፍራንቸስኮ ከየግል ፕሮጀክት ነፃ መሆን ማለት እንደሆነ ገልጠዋል።
የቅድስት መንበር ዲፕሎማት ማለት ሐዋርያዊ ወኪል የተለያዩ ባህሎች ማወቅ ማስተናገድ ለዓለም ከቀረቡ ሰዎች ጋር መወያየት እና መነጋገር መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አመልክተዋል።
የሐዋርያዊ ወኪሎች ዲፕሎማቶች ዋነኛ ዒላማ ዜና ሰናየ ቅዱስ ወንጌልን መወከል የቤተ ክርስትያን ማሕበራዊ ዶክትሪን እና አቋም ማስከበር እንደሆነ ያምለከቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፡ ይህ ሁሉ ራስህን ሳይሆን ተልእኮውን ማስቀደም የሚጠይቅ መሆኑ አሳስበዋል።
በምያያዝም አስቀድሞ እንደጠቀስኩት ታዋቂ ባለ ሙያ ለመሆን እና ራስህን ከፍ ማደረግ እኔ በበኩሌ የስጋ በሽታ ደዌ ወይም ለምጥ ወይም ቁምጥና ነው እና
በማለት የቅድስት መነበር ሐዋርያዊ ወኪል ዲፕሎማት ለመሆን በቅድስት መንበር የቤተ ክህነት ጳጳሳዊ አካዳሚ በመማር ላይ ለሚገኙ ካህናት ገልጠዋላቸዋል።የመጪው ግዜ ሐዋርያዊ ወኪሎች ከሁሉም ነፃ በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ግዜው ሲደርስ በስራ ሲሰማሩ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንን በቁራጥነት እና አስተዋይነት እንዲወክሉ አጽንኦት ሰጥተው ጠይቀዋል።ካህናቱ መነፈሳውነት እና ጸለኦት እንድያዘወትሩ በሙያቸው የእግዚአብሔር ፍቅር እና ምህረት እንደሚወክሉ መዘንጋት እንደማይገባቸውም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አክለው ገልጠዋል።የቅድስት መንበር ዲፕሎማት ማለት ሐዋርያዊ ወኪል ሆነው ያገለገሉ እና ኃላም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰየሙ ከ50 ዓመታት በፊት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የተመለሱ ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ አብነት እንዲከተሉ ፓፓ ፍራንቸስኮ አሳሰበዋል።
ሐዋርያዊ ተልእኮው መንፈሳዊ ተልእኮ መሆኑ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ እንደሆነም አክለው ገልጠዋል።መንፈሳውነት ያልተላበሱ ሐዋርያዊ ወኪል በተሳሳተ መንገድ እየተጓዙ መሆናቸው ተረድተው በጸሎት እና አስተንትኖ እንዲጠመዱ ፓፓ ፍራንቸስኮ በአጽንኦት ጠይቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.