2013-06-05 18:04:30

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ::


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ;;
ብዙ ጊዜ ደጋግሜ እንደተናገርኩት በዛሬው ትምህርት አከባቢን የሚመለከት ጥያቄ ማንሳት እሻለሁ፣ ይህንን አርእስት እንድመርጥ ያደረገኝ ሌላ አጋጣሚ ደግሞ በዛሬው ዕለት የተባበሩት መንግሥታት ያወጁት ዓለም አቀፍ የአከባቢ ዕለት በመሆኑ ነው፣ የድርጅቱ መልእክት ለዕለቱ የምግብ ማባከንን ለማውገድና ምግብን የማውደም ሂደት እንዲወገድ አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጥ ነው፣
ስለ ተፈጥሮ ስለ አከባቢ ስናገር ኃሳቤ በቅዱስ መጽሓፍ የመጀመርያ ገጽ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ ነው፣ በም ዕራፍ ሁለት ቍጥር 15 ላይ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን በመሬት ላይ ሲያቀምጣቸው እንዲያፈሩና እንዲጠብቅዋት ነው ይላል፣ ከዚህ ጥቅስ የተነሳም መሬትን ማፍራትና መጠበቅ ምን ማለት ነው የሚል ጥያቄ ያስከትላል፣ በእውነትስ እኛ ፍጥረትን እያፈራንና እየጠበቅን ነውን? ወይንስ እየመዘመዝነውና ቸል እያልነው ነው? ማፍራት የሚለው ግሥ አንድ ገበሬ መሬቱን ብዙ ፍሬ እንዲያፈራለትና ከሌሎች ጋር ለማካፈል የሚያደርገውን እንክብካቤ! ስንት ትኵረት ፍቅርና እንዲሁም ጊዜውና ሁለመናውን እዛ ላይ የማዋል ሁኔታን ያመለክታል፣ ስለዚህ ተፈጥሮን ማፍራትና መጠበቅ በመጀመርያው የፍጥረት ታሪክ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምልክት ብቻ ሳይሆን ለእያንዳንዳችን እየተሰጠ ነው፤ ማለትም ዓለማችንን በኃላፊነት ማሳደግ ገነት እንዲሆን መለወጡ ሁሉም ሊኖሩበት የሚችልበት ቦታ እንዲሆን ማድረግ ነው፣ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛም ብዙ ስለዚህ ጉዳይ ማለት ፈጣሪ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠው ኃላፊነት የፍጥረት ሂደትንና እንቅስቃሴ መቀበል እንዳለብን ነው፣ ሆኖም ግን እኛ ብዙውን ግዜ ለመቆጣጠር ለመያዝ አንዳንዴም ለመጠምዘዝ ለመበዝበዝ እንሻለን፣ አንጠብቀውም አናከብረውም መንከባከብ ያለብን ነጻ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑንም እንዘነጋለን፣ ፍጥረትን የማድነቅ የማስተንተን የመስማት ዝንባሌያችንን እያጠፋን ነው፤ በዚህም ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ “እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ጋር ያለው የፍቅር ታሪክ ሂደትን ማንበብ አለብን” ብለው ያቀረቡትን ጥሪ ልንቀበል አንችልም፣ ይህ ለምን ሆነ? ብለን የጠየቅን እንደሆነ ከእግዚአብሔር ርቀን ስለምንገኝ እርሱ የሚሰጠንን ምልክቶች ልናነብ አንችልም በዚህም አስተሳሰባብችን አግድማዊ ሆነዋል፣
ሆኖም ግን ማፍራትና መንከባከብ በእኛና በተፈጥሮ እንዲሁም በሰው ልጅና በፍጥረት መካከል ያለውን ግኑኝነት ብቻ አይመለክትም! የሰው ልጆች ከሰው ልጆች ያለውን ግኑኝነትም ይመለከታል፣ አር እስተ ሊቃነ ጳጳሳት ስለሰውልጅ ኤኮሎጂ ከአከባቢ ኤኮሎጂ ጋር ጥብቅ ትሥስር እንዳለው ተናግረዋል፣ ባለንበት ጊዜ የቀውስ ዘመን እንኖራለን! ይህንን ብተፈጥሮና አከባቢ እናየዋለን ከሁሉ በላይ ግን በሰው ልጆች እንመለከተዋልን፣ የሰው ልጅ በአደጋ ላይ ነው ያለው፤ ይህም እርግጥ ነው፣ የሰው ልጅ ዛሬ በአደጋ ነው ያለው፣ የሰው ልጅ ኤኮሎጂ የአስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ የአደጋው ችግር የላይ ላይ ሳይሆን እጅግ ጥልቅ በመሆኑ እንዲሁም የምጣኔ ሃብት ብቻ ሳይሆን የግብረገብነትና ስነሰው ወይም አንትሮፖሎጂካዊ ነው፣ ቤተ ክርስትያንን ይህንን ብዙ ጊዜ አስምረበታለች፤ ብዙ ሰዎች አዎ እውነት ነው ይላሉ ሆኖም ግን የአስተዳደር ሁኔታዎች እንደቀድሞዋቸው ይቀጥላሉ ምክንያቱም የሚገዙና የሚያስተዳድሩ ሕጎች ግብረገብነት የጎደላቸው የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች ናቸውን፣ ዛሬ ዓለማችንን የሚገዛ የሰው ልጅ ሳይሆን ገንዘብ ነው፣ ገንዘብ እያዘዘ ነው፣ እግዚአብሔር አባታችን ግን መሬትን እንድንጠብቅ እንጂ ገንዘብን ለመጠበቅ አላዘዘንም፣ ገዛ ራሳችንን መጠበቅ ነው ማለት ወንዶችንና ሴቶችን እንድንጠብቅ ነው የታዘዝነው፣ ግዴታችን ይህ ነው፣ ሆኖም ግን ወንዶችና ሴቶች ለአትርፍ ባይነት ስግብግብነት ጣዖቶች እየተሰው ናቸው፣ ይህም የማባካን ባህል እንለዋለን፣ አንድ ኮምፕዩተር ከተበላሸ ታላቅ ትራጀዲ ነው ሆኖም ግን ድህነት ጭንቀት እና ወደ ደንበኛ ኑሮ ሊመለሱ ሲሉ በዚህ አዘቅት የሚቀሩ የሰው ልጆች ግን ግምት አይሰጣቸውም፣ ለምሳሌ እዚህ አጠገባችን ባለው የኦቶቭያኒ ጐዳና በክረምት አንድ ሰው በሌሊት ብርድ ሲሞት አይወራም፣ በብዙ የተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሕጻናት የሚቆረስ የሚላስ አጥተው ሲሰቃዩ የሚያወሳቸው የለም፣ እንዲህ ብሎ መቀጠል የለበትም ሆኖም እነኚህ ነገሮች እንደልማድ ሆነው ማንም ልብ ብሎ አይመለከታቸውም፣ ቤት የሌላቸው በጐዳና በብርድ ሲሞቱ ወሬ አይደለም በተቃራኒው በዓለም ታላላቅ ከተሞች ባንኮች ባንዱ አስር ነጥብ ዝቅ ያለ እንደሆነ እንደ አንድ ድራማ ይወራል፣ በዚህም የሰው ልጆች እንደ ጥራጊ ቆሻሻ ወደ ጐድፍ ይጣላሉ፣
ይህ የማባከን ባህል ሁሉንም የሚያጋባ በኅብረተሰባችን አስተሳሰብ ገብተዋል፣ የሰው ልጅ ሕይወት እና ገዛ ራሱ የሰው ልጅ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዕሴቶች መሆናቸው እና መንከባከብ የሚገባቸው መሆኑ ተተወ፤ በተለይ ደግሞ ድኃ አካለ ጎዶሎ ረብ የሌለው እንደ በማኅጸን ያለ ሕጻን ወይም ያረጀ ሽማግሌ ዋጋ ቤስ ሆነው የሚታዩበት ዘመን ነው፣ ይህ የማባከን ዘመን ምግብን ስናባክንና ወደ ጐድፍ ስንጥል ምንም እንድማይሰማን አድርጎናል፣ ሆኖም ምግብ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ባለማዳረሱ ብዙ በረሃብ የሚስቃዩ ቤተሰቦች አሉ፣ በቀድሞ ጊዜ አያቶቻችን ከተረፈ ምግም ርፍራፊ እንኳ እንዳይጣል ይጠነቀቁ ነበር፣ ያለው ሁሉን የማካበትና ተጠቅሞ የመጣል ልማድ ግን የሚያስፈልገንና የማይስፈልገንን ሰብስበን በመጨረሻ መግብን ወደ መጣል አድርሶናል፣ የምግብ ዋጋ እና ዕሴት በገንዘብ ከሚተመነው በላይ የሕይወት ዋስትና ነው፣ ምግብን መጣል እንደ ከድኃ ማእድ በረሃብ ከሚሰቃይ እጅ ወስዶ መጣል መሆኑን እናስታውስ፣ ሁላችሁን ስለምግን ማባከንና መጣል ልታሰላስሉና በየትኛው መንገድ ከተራቡ የዕለት ምግብ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጋር በአጋርነት ልንካፈለው እንድምንችል መንገድና ዘዴ እንድትቀይሱ ይሁን፣
ከጥቂት ቀናት በፊት በበዓለ ጥቀ ቅዱስ ቍርባን ኢየሱስ በአምስት እንጀራና በሁለት ዓሣ እንዴት አድርጎ ከአምስት ሺ ሰዎች በላይ እንድመገበ የሚገልጥ ተአምር በወንጌል አንብበናል፣ የወንጌሉ መደምደምያም ሓረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ “ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከሕዝቡ የተረፈውን ፍርፋሪ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሱ” (ሉቃ 917)ይላል፣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ምንም እንዳይጣል ያዛቸዋል! የሚባክን የለም! የአሥራ ሁለቱ መሶብ ጉዳይ ደግሞ አለ፤ ለምን 12 መሶብ? ትርጉሙስ ምን ይሆን፧ 12 የነገደ እስራኤል ቍጥር ነው፣ በምሳሌም ሁሉንም የዓለም ሕዝቦች ያመልክታል፣ ይህ የሚያስተምረን ደግሞ ምግብ በሚገባ በእኩልነት ለሁሉም ከቀረበ ማንም ከሚያስፈልገው ሊቀር አይችልም፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ማኅረሰብ በቦታው የሚገኙትን ችግረኞችና ድሆች አውቆ ያለውን ቢካፈል የሚያስፈልገው ምግብ የሚጎድለው ማንም ባልተገኘም ነበር፣ የሰው ልጅ ኤኮሎጂና የአከባቢ ኤኮሎጂ አብረው ነው የሚጓዙት፣ሁላችን ይህን ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ ግዴታ እንዲሁም ለሁሉም ሰው ትኩረት መስጠትና የማባከን ባህልን አጥፈትን ምንም ምግም ሳንጥል የአጋርነትና የመገናኘት ባህል ለመገንባት በቍምነገር እንወስን፣







All the contents on this site are copyrighted ©.