2013-06-03 17:34:46

የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ በዓል እንድንለወጥ ይጠይቀናል፤


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት በዕለቱ በመላው ዓለም የተከበረውን የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ በዓለ ቅዱስ ቍርባን አመልክተው “የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ በዓል እንድንለወጥ ይጠይቀናል፤ በገዛ ራሳችን ከመዘጋት ወጥተን ያለንን ጥቂት ነገር ከሌሎች ጋር እንካፈል” ሲሉ ለገዛ ራሳችን ብቻ ከማሰብና ከስግብግብነት ተገላግለን በአጋርንትና በለጋስነት እንድንኖር አሳስበዋል፣ በሲርያ ላይ ተከስቶ ያለው ሁኔታም እጅግ እንዳሳሰባቸው ስለሲርያ ሰላምና ዕርቅ እንደሚጸልዩ በማመልከት በሚካሄደው አፈና ተጠልፈው ላሉ ሰዎችም ነጻ እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል፣ እንዲሁም በላቲን አመሪካ በሚታወቀው የደቡብ አሜሪካ አህጉር ሰላምን ዕርቅ ጸሎት እንዲደረግ አሳስበው በሰላም ተል እኮ እያሉ ስለሞቱት የጣልያን ወታደሮችም እንጸልይ ብለዋል፣
“ይህ የሚያሰቃይ የጦርነት ሁኔታ አሰቃቂ ትራጀዲዎች ይዞ ይጓዛል፣ ሞት ውድመት በምጣኔ ሃብትና ብተፈጥሮ ላይ ወደር የሊለው ጉዳት እያደረሰ ሲሆን ሌላው አሰቃቂው ሁኔታ ደግፎ ሰውን አፍኖ ይዞ መሰርወር ነው፣ እነኚህን ነገሮች በኃይል ሳወግዝ በጸሎት ቅርበቴንና በአፈናው የጠፉ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው አጋርነቴን እገልጣለሁ፣ ለአፋኞቹ ሰብ አውነት ደግሞ ሰዎችን ነጻ እንዲለቁ እማጠናለሁ፣ ለምናፈቅራት ሲርያ እንጸልይ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘው በዓለም ውስጥ ብዙ የግጭት ሁኔታዎች እንዳሉ አመልክተዋል፣ ነገር ግን ብዙ የተስፋ ምልክቶችም አሉ ለምሳሌ ያህል ባለፉት ቀናት በደቡብ አመሪካ አገሮች መካከል የተደረጉ የዕርቅና የሰላም ስምምነቶች መጥቀስ ይቻላል፣ እነዚህን ስምምነቶች በጸሎቶቻችን እንድንሸኛቸውም አሳስበዋል፣
ይህንን ከማለታቸው በፊት ግን የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ በአምስት እንጀራና ሁለት ዓሣዎች ከአምስት ሺ በላይ ያጠገበው የኢየሱስ ተአምር ላይ በማትኰር አስተምረዋል፣
የወንጌሉ ጥቅስ ከሉቃስ ወንጌል ሲሆን ም ዕራፍ 9 ከቍ 12-17 ነበር፤ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ ይከተል ነበር፤ ቦታውም በረሃ ነበር፣ ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ አሥራ ሁለቱም ቀርበው። በዚህ በምድረ በዳ ነንና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት። በማለት ሐዋርያት የሰጡትን መፍትሔ ብዙ ችግር የማይፈጥረና መደረግ የነበረበት ነበር፣
“የኢየሱስ አሳብ ግን ከሐዋርያቱ ሓሳብ እጅግ የተለየ ነበር፣ ይህም ከአባቱ ጋር ካለው ፍጹም አንድነትና ለሕዝቡ ከበረው ርኅራራኄ የመነጨ ነው፣ ይህም የሚያመለክተን ኢየሱስ ለእኛ ሁላችን ያለው ርኅራኄን ነው፣ ኢየሱስ ችግሮቻችን ይሰማል፤ ደካማነትችን ያያል፤ ምን እንደሚያስፈልገን ደግሞ ያውቃል፣ አምስቱን ዳቦ ባየ ጊዜ አሳቢነቱን ያሳያል፤ ከዛው ትንሽ እንጌራ እግዚአብሔር ለሁሉም የሚበቃ ነገር ሊያመጣ ይችላል፣ ኢየሱስ በሰማያዊ አባቱ ላይ ታላቅ መተማመን ነበረው፣ ለእርሱ ሁሉም እንደሚቻለው ያውቃልና፣
ለዚህም ነበር ኢየሱስ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው ያላቸው እንዲሁም በየክፍሉ አምሳ አምሳውን አስቀምጡአቸው ያላቸው፣
ለምን በአምሳ ቡድን ብለን የጠየቅን እንደሆነ እንደአጋጣሚ የሆነ አይደለም፣ ይህ ቡድን የሆነ የሰዎችስብስብ አይደለም፤ ነገር ማኅበር ይሆናሉ በእግዚአብሔር እንጀራ የሚመገብ ማኅበር ሆነዋል፣ ከዛም ኢየሱስ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ፥ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረካቸው ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛርሙርቱ ሰጠ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፥ ከእነርሱም የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ወሰዱ። እርግጥ ይህ ቅዱስ ቍርባንን ያመለክታል፣
“እየውላችሁ ተአምሩ! ከማባዛት ይልቅ በእምነትና በጸሎት እውን የሆነ መከፋፈልን ያመልክታል! ሁላቸው ተመግበዋል፤ ትርፍም ነበር፤ ይህ ምልክት ለሰው ልጅ የእግዚአብሔር ኅብስተ ሕይወት የሆነ ኢየሱስን ያመልክታል፣
ሐዋርያቱ ግን ሁኔታውን ሁሉ አይተው ትርጉምን ሊረዱት አልቻሉም ምክንያቱም ልክ እንደሕዝቡ በሁኔታው ግርምት ተደንቀው ቀሩ፣ እንደገና ለሁለተኛ ግዜ ከሰብ አዊ አስተሳሰብ ሊወጡ አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር አስተሳሰብ የአገልግሎት የፍቅርና የእምነት መሆኑን አልተረዱም፣
“የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ በዓል በእግዚአብሔር አሳቢነት አምነን እንድንለወጥ ጥሪ ያቀርብናል፤ ያለንን ጥቂት ነገር ከሌሎች ጋር መከፋፈልን እንድናውቅ እንጂ በገዛ ራሳችን ተዘግተን እንዳንቀር፣ እመቤታችን ድንግል ማርያምን በዚሁ ለውጥ እንትረዳን እንለምናት፣ በቅዱስ ቍርባን አምልኮ የምናቀርብለት ኢየሱስን በእውነት እንድንከተል ትርዳን ብለው ካስተማሩ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.