2013-05-31 16:21:11

የጋራው ውይይት በወንጌል ትእምርት


RealAudioMP3 እዚህ በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ፦ “ነፃ ውይይት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ። ዛሬ የሚቻል ነውን?” በሚል ርእሰ ጉዳይ የተመራ የጊዜ ምልክቶች ለይቶ ለማንበብና ለመረዳት እንዲቻል ለጋራው ውይይት ገዛ እራስ ክፍት አድርጎ መሰናዳት ያለው አስፈላጊነት የተሰመረበት ሁሉም የተለያዩ የክርስቲያን ድረ ገጾችን ያካተተ የክብ ጠረጴዛ ውይይት መካሄዱ አውደ ጥናቱን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ አመለከቱ።
ይህ አይነት የጋራው ውይይት በአሁኑ ወቅት በድረ ገጾች አማካኝነት የሚከናወን መሆኑ ያመለከተው የክብ ጠረጴዛ ውይይት በተለይ ደግሞ VinoNuovo.it በተሰኘው ድረ ገጽ አማካኝነት እየተከናወነ መሆኑና የጋራ አካፋይ የሆነውን ክብር ለመለየት ወንጌልን መኖር በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ እንደነበርም የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማጆረ አያይዘውም በተካሄደው ዓውደ ጥናት ንግግር ያሰሙት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በዚህ ማኅበር ሥር የሚታተመው Civiltà Cattolica-ካቶሊካዊ ሥልጣኔ ለተሰየመው መጽሔት ዘገባ አቅራቢና ደራሲ አባ ፍራንቸስኮ ኦከታ፦ የምንኖርበት ወቅታዊው ዓለም በድረ ገጽ በተራቀቁ አዲስ የመገናኛ ብዙኃን መሣሪያ ተጽእኖ የተሞላው በመሆኑ ድረ ገጽ መጎብኘትና ማንበብ መንሳፈፍ ተብሎ የሚገለጥ ሲሆን፣ መንሳፈፍ መእግር መጓዝ ከሚለው ተግባር እጅግ የተለየ ነው። ለመንሳፈፍ የነፋስ አቅጣጫን ማንበብና ሊደረስ የተገባው ሥፍራ ከወዲሁ መለየት አስፈላጊ ነው ስለዚህ ብሶል የሚጠይቅ ሂደት ነው። ብሶሉ ከተበላሸ የታለመው ግብ ይዛባል። ስለዚህ በዚህ በመንሳፈፍ የሚኖርብት ዓለም ያለው መኖር ለማረምና ዓላማ ያለው እንዲሆም መደጋገፍ ይገባናል” ካሉ በኋላ እንደ አብነትም የደቀ መዛሙርት በኃይለኛ ማዕበልና ነፋስ በተናወጠው የባህር ጉዞ ወቅት አብሯቸው የነበረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያንን አደገኛው ማዕበልና ኃይለኛው ነፋስ ጸጥ እንዲል እንዳዘዘውና የኢየሱስ ትስብእት በዚህ ምድራዊ ጉዞአችንም መንገድና እውነት ሕይወት ሆኖ የሚመራ ነው። ስለዚህ ማኅበረ ክርስቲያን እንደ ድረ ገጽ መረባዊ ግኑኝነት በማጽናት የእምነት ምስክርነት ሊሰጥ ተጥርተዋል እንዳሉ ማጆረ አስታወቁ።
Aleteia.org ለተሰየመው ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ጀሱስ ኮሊና በበኩላቸውም፦ ማኅበረ ክርስቲያን በክርስቲያን ድረ ገጾች አማይነት ሩቅና ቅርብ ያለው በመገናኘት በጠቅላላ ከአንድ ሚሊያርድ 200 ሚሊዮን ምሥጢረ ጥምቀት ከተቀበለው ውስጥ 450 ሚሊዮን የድረ ገጽ ተጠቃሚ ነው። ስለዚህ በዚህ አዲስ የመገናኛ ብዙኃን ስልት አማካይነትም ክርስትናን ለመኖር ተጠርተናል፣ ከሌሎች የማኅበረ ክርስትያን አባላት ጋር እንገናኛለን፣ ጽረ ገጾችን መስበክ የሁላችን ኃላፊነት ነው። አዲስ የመገናኛ ብዙኃን ቋንቋ በመጠቀም ክርስትና በዚሁ አዲስ ወቅታዊው ሁነት ወንጌልን ማበሰር፣ በድረ ገጽ ሥነ ሃሳበ ዓለም ውስጥ መዋኘት ሳይሆን ተጨባጩን ዓለም መዘንጋት የለብንም። የክርስትናው ትእዛዝ ፍቅር ነው። ይክ የፍቅር አቢዮት እርሱም የሚውዱህን ብቻ ሳይሆን ጠላጥህንም ጭምር አፍቅር የሚል ነው። ጠላት እንደምታፈቅረው ሲያውቅ ገዛ እራሱን ይከፍታል የምታወግዘው ሆነህ ስትገኝ ግን ውይይት ጨርሶ አይኖርም። ሁሉም የሁሉም ጠላት ሆኖ ነው የሚኖረው” እንዳሉ ማጆረ ገለጡ።
በመጨርሻ ንግግር ያስደመጡት ጂሊበርቶ ቦርጊ፦ “የውይይት ክብር ወይንም እሴትነቱ እኔ ተወያዩ ትምህርት እቀስማለሁ የሚለው እውነት ነው። ስለዚህ በውይይት አንዱ የገዛ እራሱን ሃሳብ በግድ ለማለት ሳይሆን ከሌላው ሊማር እንደሚችል አውቆ መቅረብ አለበት። በመወያየት መማር አለ፣ መማማር ማለት ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማጆረ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.