2013-05-31 19:07:30

በዓለ ጥቀ ቅዱስ ቍርባን


በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ትናንትና የጥቀ ቅዱስ ቍርባን ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ክብር ሲዘከር በአብዛኛዎቹ ግን እፊታችን እሁድ ይከበራል፣ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና ማምሻውን የክብረ በዓሉ ቅዳሴ በቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራኖ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዳሳረጉና ከቅዳሴ በኋላ ከቤተ ክርስትያኑ እስከ ሳንታ ማርያ ማጆረ ባዚሊካ የቅዱስ ቍርባን ዑደት መርተው በእግራቸው እንደተጓዙ ተመልክተዋል፣
በሥርዓተ አምልኮው የዘመን ግጻዌ መሠረት የዕለቱ ቃለ ወንጌል የሉቃስ ወንጌል ም ዕራፍ ዘጠኝ ሲሆን ጌታ ኢየሱስ በአምስት እንጀራ ሁለት ዓሣ ከአምስት ሺ በላይ የሚሆኑ ሕዝብ ለመመገብ ያደረገው ተአምራትን የሚመለከት ነበር፣ ሓዋርያት ተጨንቀው የነበሩትም ቦታ ምድረ በዳ በመሆኑ ጌታ ሕዝቡን ተሎ እንዲያሰናበት በጠየቁበት ጊዜ ጌታ ኢየሱስም የሚበላ እናንተ ስጥዋቸው (ሉቃ 9፤13) ይላቸዋል፣ ቅዱስነታቸውም ይህን ሓረግ መነሻ በማድረግ ሦስት መሪ ቃላት በመምረጥ ሰፊ ስብከት አድርገዋል፣ ሶስቱ ቃላት ደግሞ ጌታን መከተል ሱታፌና ያለህን ነገር መከፋፈል የሚሉ ነበር፣
ከሁሉ አስቀድመን መመለስ ያለብን ጥያቄ የሚበላ የሚሰጣቸው እነማን ነበሩ? መልሱ በዕለቱ ቃለ ወንጌል መክፈቻ ላይ አለ፣ ሕዝቡ ነው፤ ኢየሱስ በብዙ ሕዝብ መካከል ነበር፤ ይቀበለዋል ይናገረዋል ያስብለታል የእግዚአብሔርን ምሕረት ያሳየዋል፤ ከእነርሱም መካከል ከእርሱ ጋር የሚሆኑና በዕለታዊ ተልእኮው የሚተባበሩት 12 ሐዋርያት ይመርጣል፣ ሕዝቡም ይከተለዋል ይሰማዋል ምክንያቱም ኢየሱስ አዲስ በሆነ መንገድ ይናገርና ይሠራ ስለነበር ነው፣ በሥልጣን ትክክለኛና ሥልጣናዊ ትምህርት ይሰጥ ነበር፣ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ተስፋን ይሰጣቸው ነበር፣ የእግዚአብሔር ገጽታና ፍቅርን ገለጠላቸው፣ ሕዝቡም በደስታ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር፣
በዛሬው ዕለት የወንጌሉ ሕዝብ እኛ ነን፤ እኛም ኢየሱን ልንሰማው ከእርሱ ጋር ሱታፌ እንዲኖረን በቅዱስ ቍርባን እንድንቀበለው እንድንሸኘውና እንዲሸኘን እንፈልገዋለን፣ ኢየሱስን እንዴት እከተለዋለሁ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፣ ኢየሱስ በጸጥታ በምሥጢረ ቍርባን ይናገራል፤ ሁሌም እርሱን መከተል ማለት ከገዛ ራስህ መውጣት ሕይወታችንን ለገዛ ራሳችን ብቻ ወስነን ከመቆም ለእርሱና ለሌሎች የሚሰጥ ስጦታ አድርገን እንስጠው.
አንድ እርምጃ ወደፊት እንሂድ፤ ኢየሱስ ሐዋርያትን ለሕዝቡ የሚበላ እናንተ ስጥዋቸው ሲል በምን መሠረት ነው? በመጀመርያ በወንጌል እንደተገለጠው ሕዝቢ በበረሃ ስለነበር ሲሆን የሐዋርያት መፍትሔ እያንዳንዱ ለገዛ ራሱ እንዲያስብ መጠለያ የሚያገኝበትና ምግብ የሚያገኝበት ሁኔታ ለማፈላለግ ጌታ እንዲያሰናብታቸው የሚል ሓሳብ ነው፣ እኛም ብዙ ጊዜ የዚህ ዓይነት ፈተና ያገጥመናል፣ የሌሎች ችግር ፍላጎት ጨርሰን እግምት ውስጥ አናስገባም፣ ስናሰናብታቸው “እግዚአብሔር ይርዳህ” እንላለን፣ የኢየሱስ መለስ ግን ተቃራኒው ነበር፣ እናንተ የሚበላ ስጥዋቸው ይላል፣ ሐዋርያትም ምንም እንደሌላቸው አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ ብቻ እንዳለ አልያም ሊገዙ መሄድ እንዳለባቸው ይነግሩታል፣ ኢየሱስ ግን ሓምሳ በሓምሳ ቍጭ እንዲያሰኝዋቸው ይነግራቸዋል፣ ዓይኑን ወደ ሰማይ በማንሳት ባርኮ ቈርሶ ይሰጣቸዋል፤ ሁላቸውም ይጠግባሉ፣ የቀረው ርፍራፊም 12 ቅርንጫት ይሞላል፣
ዛሬ ማምሻውን በምናሳረገው በዚሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ በቅዱስ ቍርባን አከባቢ በጌታ ማዕድ ተቀምጠን እንገኛለን፣ ጌታ አሁንም ቅዱስ ሥጋው ይሰጠናል፣ ይህም ሥጋ ለደህንነታችን በቀራንዮ የተሰቀለ ቅዱስ ሥጋው ነው፣ ቃሉን በመስማት እና ሥጋውና ደሙን በመስጠን ከማንኛ ስብስብ ማኅበር እንድናቆም ያደርገናል፤ ማኅበረ ክርስትያን፤ የተባበረ፤ የተወሃሃደ፤ አንድ ሆነናል፣ ቅዱስ ቍርባን የሱታፌና የውህደት ምሥጢር ነው፣ ከግላዊነት ወደ ማኅበር በማሻገር ጌታን አንድ ሆነን እንድንከተል ያደርገናል፣ በእርሱ ያለንን እምነት በአንድነት ለመግለጥ ያስችለናል፣ ቅዱስ ቍርባንን እንዴት እቀበለዋለሁ?፡በሕይወቴስ እንዴት እኖረዋለሁ፧ እውነት እንደሚገባ ከጌታ ጋር አንድ በመሆን ከሌሎች ጋር በመተሳሰር እኖረዋለሁን? ብለን ራሳችን እንጠይቅ፣
የመጨረሻ ነጥብ የዳቦዎቹ ተአምር ከየት መጣ? ብለን የጠየቅን እንደሆኑ ስጡ ከሚለው የኢየሱስ ት እዛዝ ነው፣ መስጠት መካፈል ያስፈልጋል፣ ሐዋርያቱ ምኑን ይከፋፈላሉ?፡ያ የነበራቸውን ትንሽ ነገር ከሌሎች ጋር ይከፋፈላሉ፣ አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣን፣ ሆኖም ግን መላው ሕዝቡን ያጠገበው እነኚህ በጌታ እጅ ሲባረኩ ነው፣ አለምንም ነገር ሕዝቡን በቡድን በቡድን እንዲቀመጥ አድርጉ ሲባሉ በጌታ ቃል ተማምነው ሕዝቡን አኖሩት፤ ይህም የሚያስተምረን ነገር ካለ በቤተክርስትያን ይሁን በኅብረተሰብ አጋርነት የሚለው ቃል ልንጠቀምበት ነው፤ ያለህን ነገር ለእግዚአብሔር በማቅረብ ተአምር ልታይ ትችላለህ፣ መስጠት መከፋፈል መተባበር ካለ ሕይወታችን ፍሬ ያለው ሊሆን ይችላል፣ ጌታ ሥጋውና ደሙ ሲሰጠን የእግዚአብሔር አጋነትን እናጣጥማለን፣ ጌታ በልጁ መሥዋዕተ እጉናችን ይሆናል ቅርባችን ነው፣ በቀራንዮ መሥዋዕት ትሕትናን ለብሶ ኃጢአታችን ጥፋታችን ግላዊነታችን እና ሞትን ያሸንፋል፣ ስጋው በመስጠት ሕይወታችን ይካፈላል፣ መንገዳችንን ይከተላል፣ እኛንም መንገዱን እንድንከተል ይጠይቀናል፣ ያለንን ትንሽ ነገር እንካፈል፣ ጌታ ሊያሳድገው ነው፣ ዛሬ የቅዱስ ቍርባን ዑደትና ስግደት ስናካሄድ ጌታ እኒድልወጥን እንፍቀድለት፤ እንዲመራን እንተወው፤ ያለንን ትንሽ ነገር ለመስጠት ፍርሃት እንዳይሰማን ይርዳን፣ ቅዱስ ቍርባን እንዲለወጠን እንጸሊ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.