2013-05-29 16:03:11

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በአባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ አማካኝነት የሚያቀርበው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲዖል የወረደው የተኮነኑትን ለማዳን ወይንም ሲዖልን ለማጥፋት ሳይሆን ቅኖችን ነጻ ለማውጣት ነው” የተሰኘው የካቶሊካዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ የሚያረጋግጠው አንቀጸ እምነት ማእከል በማድረግ ትላትና ባቀረቡት 28ኛው ክፍለ አፈስተምህሮ፦ “የሐዋርያት ስብከት ስለ ክርስቶስ ወደ ሲዖል መውረድ ይናገራል። የዚህ ትእምርት ትርጉም ምንድር ነው? የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቁ. 362 ‘ኢየሱስ ከሙታን ተለይቶ ነተሣ የሚሉ ተደጋጋሚ አዲስ ኪዳን ማስረጃዎች በመስቀል ላይ የተሰቀለው እርሱ ከትንሣኤው በፊት በሙታን ዓለም ቆይታ ማድረጉን ይጠቁማል’ ይኽ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሙሉ እስከ ፍጻሜው ድረስ ትብብር ማድረጉን የሚያረጋግጥ እውነት ነው። ኢየሱስ የሞትን ስቃይ ያጣጣመ ብቻ ሳይሆን ከሙታን ጋር ለመሆን የእግዚአብሔር ራእይ እንደ ሌላቸው ወደ ሙታንም ወርደዋል” ብለዋል።
“አንዳንድ የዘመኑ የቲዮሎጊያ ሊቃውንት የኢየሱስ ወደ ሙታን መውረድ የ kenosi-ገዛ እራስ የማዋረድና ዝቅ የማድረጉ የመጨረሻው ደረጃ መኖሩን የሚያረጋግጥ መሆኑ ያብራራሉ፣ በመስቀልና በሞቱ ኃጢአተኛውን ከኃጢአት ነጥቆ ለማላቀቅ ለኃጢአተኛው እጅግ ቅርብ በመሆን በሲዖል ድቅድቅ ብቸኝነት ወደ ሚኖርበት ገዛ እራሱን አወረደ” ካሉ በኋላ በመቀጠል፦ “የካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ፣ ከቁ. 632 እስ634 ድረስ ‘ወደ ሙታን ዓለም በመውረድ እዛውም በሲዖል የመድኃኔ ዓለም ድል አድራጊነትን አዲስ ብስራት ያሰማል፣ ‘ወንጌል ለሙታን እንኳ ሳይቀር ተበሥረዋል፣ (ቍ. 634) ብለዋል።
የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ፦ ኢየሱስ ‘ወደ ሲዖል የወረደው የተኮነኑትን ለማዳን ወይንም የሲዖልን ኩነኔ ለማጥፋት ሳይሆን ከርሱ ቀድመው ወደዚያ የሔዱትን ጻድቃን ነጻ ለማውጣት ነው (ቍ. 634) በማለት ጌታ ሁሉ የሰው ልጅ እንዲድን ነው ፍቃዱ ሆኖም ግን የማዳኑን እቅድ በማስገደድ ተቀበሉ አይልም። ምህረቱ በነጻነት እንጂ በግድ አይልም። ስለዚህ ይኽ ደግሞ ኩነኔ የእግዚአብሔር ሳይሆን ሰው በገዛ እራሱ ላይ የሚወስደው ውሳኔ ነው። በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.