2013-05-29 19:31:34

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ውንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ባለፈው ዕለተ ሮብ ባቀረብኩት አስተምህሮ በመንፈስ ቅዱስና በቤተ ክርስትያን መካከል ያለውን መተሳሰር አስምሬበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ እኛ ሁላችን ስለምንኖረውና የእርሱ አካል የሆነው ምሥጢር ምሥጢረ ቤተ ክርስትያን ላስተምር እወዳለሁ፣ ይህንን የማደርገው ደግሞ በሁለተንኛው የቫቲካን ጉባኤ እንደገለጸው ነው፣ ለዛሬ የመጀመርያውን ለመመለከት፤ ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ቤተሰብ ናት የሚለውን አር እስት እንመለከታለን፣ በእነዚህ ወራት ከአንዴ ይልቅ ብዙ ግዜ ስለ የጠፋው ልጅ ምሳሌ ተናግሬአለሁ በበለጠ ደግሞ ስለ መሓሪው አባት (ሉቃ 15፤11-32)፣ ታናሹ ልጅ የአባቱን ቤት ጥሎ ይሄዳል፣ የያዘውን ሁሉ ያጠፋልና ስሕተቱ በተረዳው ጊዜ ወደ አባቱ እንዲመለስ ይወስናል፤ ሆኖም ግን እንደ ልጅ ሊቆጠር እንደማገባው ተረድቶ እንደ ባርያ እንዲቀውበለው ያስባል፣ አባቱ ግን ሊቀበለው ከሩቅ ሮጦ ይመጣል፤ ያቅፈዋል፤ የልጅነት መብት ይሰጠዋል፤ ታላቅ ድግስም ያዘጋጃል፣
ይህ የትኛው የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው? ብለን የጠየቅን እንደሆነ፤ ለሁላችን እኛን በመሰብሰብ አንድያ የልጆቹ ቤተሰብ ለማቆም ነው፤ በዚህም እያንዳንዳችን ቅርብ መሆንና በእርሱ መፈቀራችን እንዲሰማን፤ በወንጌሉ ምሳሌ እንደተገለጠው የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል መሆን ሙቀት እንዲሰማን፣ ቤተ ክርስትያን በዚሁ ታላቅ የእግዚአብሔር ዕቅድ ትመሰረታለች፤ በአንዳንድ ሰዎች መካከል በተደረገ ስምምነት የምትቆም ድርጅት አይደለችም ነገር ግን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16 ደጋግመው እንዳሳሰቡት የእግዚአብሔር ሥራ ነው ከዚህ የፍቅር ዕቅድም ይወለዳል፣ ይህ ዕቅድም ቀስ በቀስ በታሪክ እውን ይሆናል፣ ቤተ ክርስትያን ከእግዚአብሔር ፍላጎት ትወለዳለች ሁሉንም የሰው ልጆችም ከእርሱ ጋር ሱታፌ እንዲኖራቸው ትጠራለች፤ የእርሱ ጓደኞች እንዲሆኑ እንደልጆቹ በመለኮታዊ ሕይወቱ እንዲሳተፉ ትጠራለች፣ ቤተ ክርስትያን የሚለው ቃል ከግሪክ የተወሰደ ሲሆን ኤክለስያ ማለት መሰብሰብ ሲሆን እግዚአብሔር ቤተሰቡን ይሰብስባል፤ በገዛ ራሳችም ተዘግተን እንድንቀር ከሚፈታተነን ከግላዊነት እንድንወጣ ይገፋፋናል የቤተሰቡ አካል እንድንሆንም ይጠራናል፣ ይህ ጥሪ ደግሞ በጥንተ ፍጥረታችን ይመሠረታል፣ እግዚአብሔር የፈጠረን ከእርሱ ጋር በጠለቀ የጓደኝነት ግኑኝነት እንድንኖር ነው፣ ምንም እንኳ ይህንን ከእርሱና ከመላው ፍጥረት የነበረንን ግኑኝነት ኃጢአት ያባለሻው ቢሆንም እግዚአብሔር ፈጽሞ አልተወንም፣ መላው የድህነት ታሪክ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ፍለጋንና ፍቅሩን በመስጠት እንዴት እንደተቀበለው ይገልጣል፣ አብርሃምን የብዙ ሰዎች አባት እንዲሆን ጠራው፤ የእስራኤል ህዝብን መላውን የዓለም ሕዝብን የሚቀበል ኪዳን እንዲያቆም መረጠው፣ ጊዜው በደረሰ ጊዜም ይህንን የፍቅር እና የደህንነት ዕቅዱን እውን እንዲያደርግና ከመላው የሰው ልጅ ዘር አዲስና ዘለዓለማዊ ኪዳን እንዲያቆም አንድያ ልጁን ላከ፣ ወንጌልን ስናነብ ኢየሱስ ቃሉን የተቀበሉና የሚከተሉት እንዲሁም እርሱ ያቋቋመውን ቤተሰብ የሚቀበሉ የጥቂት ሰዎች ማኅበር እንዳቋቋመ እንመለከታለን፣ በዚህም ማኅበር እርሱ ቤተ ክርስትያኑን ያሰናዳና ያቋቍም እንደነበር እንረዳለን፣
ቤተ ክርስትያን ከየት ትወለዳለች? ብለን የጠየቅን እንደሆነ ደግሞ ወደር ከሌለው በመስቀል ከተገለጠው ፍቅሩ እንዲሁም የምሥጢረ ጥቀ ቅዱስ ቍርባንና የምሥጢረ ጥምቀት ምልክት በሆነው በጦር ተወግቶ ከተከፈተውና ደምና ውኃ ካወጣው ጎኑ እንደምትወለድ እንረዳለን፣ በእግዚአብሔር ቤተሰብ በሆነችው ቤተ ክርስትያን የሕይወት ስርዋ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ፍቅር እና አለምንም ልዩነትና መለኪያ ሁሉንም በሚያጠቃልል በጓደኞች ፍቅር እውን ይሆናል፣ ቤተ ክርስትያን የምናፈቅርበትና የምንፈቀርበት ቤተ ሰብ ነው፣
ቤተ ክርስትያን መቼ ትገለጣለች? ብለን የጠየቅን እንድሆነ ደግሞ ከሁለት ሳምንታት በፊት ክብረ በዓሉን እንዳስታውስነው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሓዋርያት ልብን በሞላው ጊዜ እና ወንጌልን ለመስበክና የእግዚአብሔር ፍቅርን ለሁሉ ለማዳረስ ወጥተው ጉዞውን እንዲጀምሩ በገፋፋቸው ጊዜ ተገለጠ፣
ዛሬም ቢሆን ለክርስቶስ እሺ ለቤተ ክርስትያን እምቢ የሚሉ አሉ፣ እነዚህም በቤተ ክርስትያን አምናለሁ በቄሶችዋ ግን አላምንም እንደሚሉ ናቸው፣ ሆኖም ግን ቤተ ክርስትያን ናት ወደ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር የምታደርሰን፤ ቤተ ክርስትያን ታላቅዋ የእግዚአብሔር ልጆች ቤተ ሰብ ናት፣ እውነት ነው በሚያራምድዋት እረኞችና ምእመናን ሰብአዊ ሁኔታዎችም አልዋት፤ ግድፈቶች ውድቀቶች ኃጢአቶች አልዋት፣ ር.ሊ.ጳጳሳትም ብዙ ጕድለቶች አሉት መልካሙ ነገር ግን ኃጢአተኞች መሆናችን ባስታወስን ግዜ ሁሌ የሚምረን የእግዚአብሔር ምሕረት መኖሩ ነው፣ አትርሱት! እግዚአብሔር ሁሌ ይምረናል፤ መሓሪና ርኅሩኅ በሆነው ፍቅሩ ይቀበለናል፣ አንዳንዶቹ ኃጢአት እግዚአብሔር የሚያስቀይም መጥፎ ነገር ይላሉ ሆኖም ግን ራስን ዝቅ በማድረግ በትሕትና ኃጢአተኛ መሆንህን ስታስታውን ከእርሱ የበለጠ ሌላ ነገር እንዳለ ማስታወስ ያስፈልጋል ይህም የእግዚአብሔር ምሕረት ነው! ይህንን እሰቡ!
እስቲ ወደገዛ ራሳችን መለስ ብለን እነኚህን ጥያቄዎች እናስተንትን! ቤተ ክርስትያንን ምንኛ ያህል አፈቅራታለሁ? ለቤተ ክርስትያን እጸልያለሁን? የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆነችው ቤተ ክርስትያን አካል ሆኖ ይሰማኛልን? እያንድንዱ ሕይወትን የሚያሳድሰውን የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማው እንደአካል አባልነትና መረዳዳት እንዲሰማው ምን አደርጋለሁ? እምነት የግል ሕይወታችንን የሚመለከት ስጦታና ኃይል ነው፤ ሆኖም ግን እግዚአብሔር እምነታችንን እንደቤተሰብ እንደቤተክርስትያን በኅብረት እንድንኖረው ይጠራናል፣ በተለይ በዚሁ የእምነት ዓመት ጌታን ማኅበሮቻችን ባጠቅላይ ቤተክርስትያናችን በእውነት የእግዚአብሔር ሙቀት እንደእውነተኛ ቤተሰብ እንድንኖረውና ለሌሎች እንድናዳረስው ሁሌ እንዲረዳን እንለምነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.