2013-05-29 15:59:16

ኵላዊ ኣስተንትኖ በቅዱስ ቁርባን ፊት


RealAudioMP3 በዚህ እየተኖረ ባለው የእምነት ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ሰነ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ አስተንትኖና ጸሎተ ቡራኬ በቅዱስ ቁርባን ፊት ማለትም በአንድነት በሁሉም አገሮች በሚገኙት በካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን እንደሚከበር” የአዲስ አስፍትሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቃቸው የተሰጠው ጋዜጠዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።
የተገባው የእምነት ዓመት በተለያየ መልኩ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር በሚካሄዱት ግኑኝነቶችና በሚከናወኑት ጅምሮች አማካኝነት ፍርያማ ጉዞ እያከናወነ መሆኑ የገለጡት ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ አክለውም በዚህ የእምነት ዓመት ምክንያት በጠቅላላ አራት ሚሊዮንና ሦስት መቶ ሺህ መንፈሳውያን ነጋድያን በሚፈጸሙት የተለያዩ መንፈሳዊ ጅምሮች መሳተፋቸውና እ.ኤ.አ. ሰኔ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቅት በኋላ ከአስምት ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት በቅዱስ ቁርባን ፊት የሮማ ሰዓት አቆጣጠር ማእከል ባደረገ በተለያዩ አገሮች ባለው የሰዓት ለውጥ አማክኝነት የአንድነት ኵላዊ አስተንትኖና የቡራኬ ጸሎት እንደሚከናወን አስታውቀው፦ “ሊፈጸም የተወሰነው ኩላዊ አስተንትኖና የቡራኬ ጸሎት በቅዱስ ቁርባን ፊት ‘አንድ ጌታ አንድ እምነት’ በተሰኘ ቃል የሚመራ ነው። ይህ ሊፈጸመ ተወስኖ ያለው ኩላዊ አስተንትኖና የቡራኬ ጸሎት በቅዱስ ቁርባን ፊት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆንና ስለዚህ ታሪካዊ ብሎ መግለጡ የሚሻል ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጅሶቲ አያይዘውም፦ “ስለዚህ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ጋር በማያያዝ በሁሉ አገሮች ባለው የሰዓት ለውጥ አማካኝነት በተመሳሳይ ጊዜ የሚከናወን ኵላዊ መንፈሳዊ መደብ እንደሚሆንና ይኽም ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ሙሉ ሱታፌ ለማንጸባርቅ ታቅዶና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ስለ ሁሉም በስቃይ በችግር በተለያዩ ሰብአዊና መንፈሳዊ ችግር ውስጥ ለሚገኙት በጦርነት በበሽታ በድኽነት በተለያዩ አዳዲስ የባርነት ችግር ውስጥ ወድቀው ለሚሰቃዩት ሰዎች ሕፃናት ሴቶች ከጌታ ድጋፍ እንዲያገኙ ነጻ እንዲሆኑ ጸሎት የሚቀርብበት ነው” እንዳሉና፦ “እ.ኤ.አ. ሰኔ 15ና ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. “በማመናችን ሕይወት አለን” በሚል ቃል ተመርቶ ‘Evangelium vitae-ወንጌላዊ ሕይወት’ ይኽም ቤተ ክርስቲያን የሰው ልጅ ሕይወት በተመለከተ አክብሮት የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብርና መብት ጥበቃ በማነቃቃት የምትሰጠው አስተዋፅዖ ሂደቱ ምን እንደሚመስል በሚያረጋግጥ ርእሰ ጉዳዮች ተማእክሎ የሚከናወን ‘ሁሉም ስለ ሕይወት’ የሚል ሕዝብ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከቅትር በፊት 10 ሰዓት ተኩል ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመሳተፍ የቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ መቃብር በመሳለም፣ አስተንትኖ ጸሎትና ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ማምሻውም በጎደና ኮንቺሊያዚዮነ የችቦ መብራት ያነገበ የማይሻረው የሰው ልጅ ክቡር ሕይወት ለማነቃቃት የጽሞኖ መንፈሳዊ ዑደት ይፈጸማል” እንዳሉ ጂሶቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.