2013-05-29 16:25:30

ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ፡ ር ሊ ጳ ፍራንሲስ


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ሥርዓተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን ትናንትና ጥዋት በርካታ ምእመናን መነኲስያት እና መነኮሳን በተገኙበት ሥርዓተ ቅዳሴ አሳርገዋል።
ቅድስነታቸው በዚሁ በአዲስ ስብክተ ቅዱስ ወንጌል ሊቀ መንበር በብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላስ ተሸኝተው ባሳረጉት ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ፡ ታዋቂ ባለ ሙያ በመሆን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል አይቻልም ምክንቱም መንገዱ የመስቀል መንገድ ነውና ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ማለት ከፍተኛ ሥልጣን መያዝ ወይም መፍለግ ማለት አይደለም በማለት ሰብከዋል።
ውሉደ ክህነት ለእግዚአብሔር ያደሩ ሁሉ የክርስቶስ መንገድ ሲከተሉ አለ ማንኛውም የዓለም ማተርያላዊ ፍላጎት እሱን መከተል እንደሚጠበቅባቸውም አክለው ሰብከዋል።
ስብከታቸው በማያያዝም መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስንከተል የምንሸለመው ሽልማት ምንድን ነው ብለው የጠየቁ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ሥቃይ መሳደድ በመጨረሻም ተሰቅሎ መሞት ነበረ እና የሱ መንገድ የሚከተል እና ለሱ ያደረ እሱ ያለፈውን ሂደት መከተል እንዳለበት መዘንጋት አይገባውም ብለዋል።
የአንድ ክርስትያን ሕይወት ሁሉም ነገር ለም እና ደግ ሊሆን አይችልም መሳደድ መስዋዕት መሆን እንዳለ መገንዘብ አለብን ያሉ ፓፓ ፍራንቸስኮ የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ይሄው ነው አሉ ።የቤተ ክርስትያን ታሪክ እንደሚያስረዳን ኢየሱስ ክርስቶን መከተል እንዳ ባህላዊ ክርስትያናዊ ሂደት በመመልከት ዋንኛው መንገድ ያሳታል የውሸት መከተል ይከተላል ክርስቶስን እሱ እንዳለው እና እንደሚፈልገው መጓዝ ቀላል አይደለም የራስህን ፍላጎት ለማካበት የሚደረግ እንዳልሆነም ቅድስነታቸው አመልክተዋል።
ክርስቶስን መከተል ማለት እሱን ማፍቀር እሱ ያለፈበትን መንገድ ማለፍ ከዓለማዊ መንፈሳውነት መራቅ መንፈስ ቅዱስን መላበስ መጸለይ ማስተንተን እንደሆነም ሰብከዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ ብስራት ልባችን ውስጥ ሰፍሮ ህልናችንን መቀየር አለበት ክርስቶስን በአፍ ብቻ መውደድ እና ማድነቅ ሳይሆን ገቢራዊ ማደረግ አለብን ንጹህ ክርስትያኖች ንጹህ የክርስቶስ ተከታዮች ለመሆን ሌተ ቀን ጥረት ማካሄድ አለብን ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ።
ስለሆነም እሱ ማለት መድኅን ዓለም ክርስቶስ የተጓዘበት መንገድ መከተል እሱን መፍለግ መውደድ መንግስተ ሰማያቱ ለመግባት መልካም ስራ መስራት ትእዛዛቱን ማክበር አለብን እንጂ ለስሙ ካቶሊካውያን መጠራት የለብንም ግብር ያስፈላጋል ፡ የክርስቶስ ዱካ መከተል አለብን ካሉ በኃላ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቤተ ክህነት ምእምናት እና ምእመናንን እንዲንከባከቡ የክርስቶስ መንገድን እንድያሳዩ እና እንዲመሩ ካሉ በኃላ ስብከታቸውን አጠቅልለው በሥርዓተ ቅድሴው ለተገኙ ሁሉ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ስብከተቸዋን በዚሁ አጠቃልለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.